#UPDATE
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (የፍትህ ማናጂንግ ዳይሬክተር) ከእስር መፈታቱን ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ከደቂቃዎች በፊት አሳውቋል።
ከዚህ በተጨማሪ የፍትህ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ምስጋን ዝናቤም ከእስር መፈታቱ ተሰምቷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

በኢትዮጵያ የሶስት ቀን የሥራ ጉብኝት ያደረጉት የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ልዑካቸው ዛሬ ወደ ኤርትራ ተመልሰዋል።
ከፕሬዜዳንቱ እና ልዑካቸው ጋር በልዩ ልዩ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ካተኮረ ውይይት መደረጉን ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አሳውቀዋል።

TIKVAH-ETHIOPIA
“እኔ የምሰራው ሕዳሴው ግድብ ላይ ነው፤ ግድቡ ደግሞ የሁሉም ነው” - ወ/ሮ ሮማን ገ/ሥላሴ በህወሃት ሪፖርት እንዲያደርጉ ከተባሉት አመራሮች መካከል የሕዳሴው ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሮማን ገ/ስላሴ ጥሪውን እንዳላዩት እና እንዳላነበቡት ለአል ዓይን ተናግረዋል፡፡ “እኔ የምሰራው ሕዳሴው ግድብ ላይ ነው፣ ግድቡ ደግሞ የሁሉም ብሔር ፣ የሁሉም ሕዝብ…
ዶ/ር አረጋዊ በርሄ የሕዳሴው ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት በወ/ሮ ሮማን ገ/ስላሴ ቦታ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE
- የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በአዳማ ኢንደስትሪ ፓርክ ያስመረተውን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ተረከቧል።
- የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ተረክበው ለየክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች እና ተወካዮች አስረክበዋል።
- በወረዳና ከዚያ በታች ያሉ ትምህርት ቤቶች ጥቅምት 9/2013 ዓ/ም ትምህርት እንዲጀምሩ ይደረጋል። በቦታዎች ርቀትና በተለያዩ ምክንያቶች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ያልደረሳቸው ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንዳይጀምሩ ማሰስቢያ ተሰጥቷል።
- እስከ ጥቅምት 30/2013 ዓ/ም ሁሉንም ትምህርት ቤቶች ትምህርት ለማስጀመር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከተቀመጡት መስፈርቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የማስክ አቅርቦት ስራ በሁሉም ትምህርት ቤቶች እየተከናወነ ነው።
- በሃዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ የተመረተው ማስክም ወደየትምህርት ቤቶች የማድረስ ስራ እየተሰራ ነው።
#MoE
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

ችሎት!
ዛሬ ረፋድ በአዳማ ምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌው በተከሰሱበት ህገ ወጥ ጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ሶስት የዐቃቤ ህግ ምስክሮች የምስክር ቃላቸው ተሰምቷል።
ፍርድ ቤቱ የሰማውን ምስክርነት መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ የተፈቀደላቸው የ100 ሺህ ብር ዋስትናን ተከትሎ ለምን እንዳልተፈቱ የጠየቀ ሲሆን የቢሾፍቱ ፖሊስ ሃላፊ ቀርቦ እንዲያብራራ የታዘዘውን ትዕዛዝ ተመልክቷል።
በትዕዛዙ የቢሾፍቱ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ተቀይሯል መባሉን ተከትሎ ተወካይ ወይም የክፍል ሃላፊ ለምን እንዳልቀረቡ በቀጣይ ቀጠሮ ቀርበው እንዲያብራሩም ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ግለሰቡ በህገወጥ ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ክስ በተፈቀደላቸው የ100 ሺህ ብር ዋስትና መሰረት ከእስር እንዲፈታቸው ፍርድ ቤቱ አዟል። (ኤፍቢሲ)

በጋምቤላ ክልል ሰኞ ትምህርት ይጀምራል !
በጋምቤላ ክልል በጎርፍ አደጋ ጉዳት ከደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች በስተቀር 257 ትምህርት ቤቶች የፊታችን ሰኞ መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራቸው እንደሚጀምሩ የጋምቤላ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።
አቶ ሙሴ ጋጄት (የቢሮው ኃላፊ) ለኢዜአ ከተናገሩት ፦
- ኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከል የፊታችን ሰኞ ትምህርት እንዲጀመር አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል።
- የመማር ማስተማር ሥራው በ257 ትምህርት ቤቶች ይጀምራል።
- በክልሉ በኑዌር እና በአኝዋክ ዞኖችና በኢታንግ ልዩ ወረዳ ተከስቶ በነበረው የጎርፍ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው 86 ትምህርት ቤቶች ግን ትምህርት መስጠት የሚጀምሩት በሂደት ነው።
- ጉዳት የደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች በተቻለ ፍጥነት ተስተካክላው ሥራ እንዲጀምሩ እተሠራ ነው።
- በትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጠው የማስክ ድጋፍ እንዳለ ሆኖ የውኃና ሌሎች የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለማሟላት እየተሰራ ይገኛል።
- በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕፃናትን ጨምሮ ከ173,000 በላይ አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ቢሮው እየሠራ ነው።

በሰሜን ወሎ ዞን ከ286 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል!
ከነሐሴ 28/2012 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል ሰሜን ውሎ ዞን የተከሰተው የበረሃ አንበጣ መንጋ በሰብል ፣ በእንስሳት መኖ እና በቁጥቋጦ ላይ የከፋ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡
እስከ መስከረም 27 ቀን 2013 ድረስ በተመዘገበው የጉዳት መጠን 286 ሺህ አርሶ አደሮች አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አብመድ የዞኑን አስተዳደሪ ወልደትንሳኤ መኮንንን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
ሥርጭቱን በፍጥነት መከላከል ካልተቻለም ድጋፍ የሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎች ቁጥር ይጨምራል ተብሏል፡፡
የአንበጣ መንጋው በዞኑ ከተከሰበት ጊዜ አንስቶ አርሶ አደሩ ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ እየተከላከለ መሆኑን ተገልጿል።
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ሥርጭት ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ግን እየከበደ መጥቷል።
ሰብል በደረሰባቸው አካባቢዎች የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የክልሉ ልዩ ኃይል፣ የፖሊስ ሠራዊት አባላትን እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር ለመሰብሰብ እየተሠራ ነው። (AMMA)

ዛሬ ጠዋት ሁለት መቶ ዘጠና ሰባት (297) የኢትዮጵያ ዜጎች ከሳዐዲ አረቢያ (ጅዳ) ወደ ሀገራቸው በሰላም ተመለሰዋል። ከዛሬዎቹ 297 ተመላሾች መካከል ሃያ አምስቱ (25) ህጻናት እንደሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፅዮን ተክሉ አሳውቀውናል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE
በዛሬው ዕለት 357 የኢትዮጵያ ዜጎች ከሳኡዲ አረቢያ ሪያድ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል። ከዛሬዎቹ ተመላሾች መካከል 262 ሴቶች ሲሆኑ 95ቱ ህጻናት ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዛሬው ዕለት 357 የኢትዮጵያ ዜጎች ከሳኡዲ አረቢያ ሪያድ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል። ከዛሬዎቹ ተመላሾች መካከል 262 ሴቶች ሲሆኑ 95ቱ ህጻናት ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ተመራቂ ተማሪዎቻቸውን ለመቀበል እና የተቋረጠውን ትምህርት በጥንቃቄ ለማስቀጠል ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ።
ተማሪዎቻቸውን ለመቀበል ዝግጅት እያደረጉ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ዛሬ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ስላደረገው ዝግጅት እንደሚከተለው አሳውቆናል ፦
- ከወዲሁ የተመራቂ ተማሪዎች የዶርም ድልድል ተጠናቋል ፣ የተመደቡበት የመኝታ ቁጥር በቴሌግራም በኩል እንዲደርሳቸው ተደርጓል። በአንድ ዶርም 2 ተማሪ ብቻ ይኖራል።
- በዋናው ጊቢ ዛሬ ተማሪዎች በሚመላለሱባቸው ዋና ዋና መንገዶች ላይ የፀረ ተህዋስ ኬሚካል ርጭት ተካሂዷል።
- በቀጣይ የፀረ ተዋህስ ኬሚካል ርጭት በተማሪዎች ማደሪያ፣ መማሪያ ክፍሎች፣ መመገቢያ አዳራሾች፣ ማንበቢያ ስፍራዎች፣ ቢሮዎች ይካሄዳል።
- ግቢ ውስጥ ከእጅ ንክኪ ነፃ የሆነ የእጅ መታጠቢያ በየቦታው እንዲቀመጥ ተደርጓል።
- በ1 ክፍል ውስጥ ከ25 ያልበለጠ ተማሪ ይማራል፣ በእያንዳንዱ ወንበር ላይ የተማሪዎች ስም ይፃፋል ፣ ተማሪዎች ስማቸው ከተፃፈበት ወንበር ሌላ መቀመጥ አይችሉም።
ቲክቫህ ላለፉት አመታት ሲያደርግ እንደቆየው የሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የመግቢያ ቀናትን እና አሁን ደግሞ የኮቪድ-19 የጥንቃቄ ዝግጅቶቻቸውን እየተከታተለ ለወላጆች እና ለተማሪዎች ያሳውቃል።

በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ህንጣሎ ወረዳ አንበጣ መንጋን ለመከላከል የሚያስችሉ ሁለት ዘመናዊ ማሽኖች የኬሚካል ርጭት እያከናወኑ ነው።
"ካኖን ስፕሬየር" የሚባሉት እነዚህ ዘመናዊ ማሽኖች በግል ድርጅት አማካኝነት ከቻይና በአውሮፕላን እንዲመጡ የተደረጉ ናቸው።
በአሁን ሰዓት በስራ ላይ የዋሉት 2ቱ ማሽኖች አመርቂ የሆነ ስራ እንደሚሰራባቸው የሚጠበቅ ሲሆን ሌሎች ማሽኖችም በመምጣት ላይ እንደሚገኙ ከድምፂ ወያነ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
በሌላ በኩል በትግራይ ክልል የአንበጣ መንጋ ለመከላከል እየተሰሩ የሚገኙ ህዝብን ያሳተፉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸው ተገልጿል።
የተለያዩ ድርጅቶች ፣ በውጭ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ፣ የመንግስት ተቋማት፣ ባለሃብቶች በቁሳቁስና በገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ካኖን ስፕሬየር" የሚባሉት እነዚህ ዘመናዊ ማሽኖች በግል ድርጅት አማካኝነት ከቻይና በአውሮፕላን እንዲመጡ የተደረጉ ናቸው።
በአሁን ሰዓት በስራ ላይ የዋሉት 2ቱ ማሽኖች አመርቂ የሆነ ስራ እንደሚሰራባቸው የሚጠበቅ ሲሆን ሌሎች ማሽኖችም በመምጣት ላይ እንደሚገኙ ከድምፂ ወያነ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
በሌላ በኩል በትግራይ ክልል የአንበጣ መንጋ ለመከላከል እየተሰሩ የሚገኙ ህዝብን ያሳተፉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸው ተገልጿል።
የተለያዩ ድርጅቶች ፣ በውጭ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ፣ የመንግስት ተቋማት፣ ባለሃብቶች በቁሳቁስና በገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
አትሌቶቻችን በሰላም ገብተዋል !
የ24 ኛው የአለም ግማሽ ማራቶን የኢትዮጵያ ልዑክ ፖላንድ ግዲኒያ በሰለም የደረሰ ሲሆን ሁሉም አትሌቶቻችን የኮሮና ቫይረስ ተመርምረው ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ24 ኛው የአለም ግማሽ ማራቶን የኢትዮጵያ ልዑክ ፖላንድ ግዲኒያ በሰለም የደረሰ ሲሆን ሁሉም አትሌቶቻችን የኮሮና ቫይረስ ተመርምረው ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ውሏል" - ዶ/ር ይናገር ደሴ (የብሄራዊ ባንክ ገዥ)
ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ካሉት ሶስት የቢሮ ህንፃዎች መካከል በአንደኛው ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉን የባንኩ ገዥ ዶ/ር ይናገር አሳውቀዋል።
ዶክተር ይናገር ደሴ የእሳት አደጋው በፍጥነት መቆጣጠር በመቻሉ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ለetv ተናግረዋል።
የእሳት አደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ካሉት ሶስት የቢሮ ህንፃዎች መካከል በአንደኛው ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉን የባንኩ ገዥ ዶ/ር ይናገር አሳውቀዋል።
ዶክተር ይናገር ደሴ የእሳት አደጋው በፍጥነት መቆጣጠር በመቻሉ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ለetv ተናግረዋል።
የእሳት አደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION📣 በምዕራብ ሀረርጌ ውስጥ ወጥ የሆነ ትልቅ የማሽላ ምርት የሚገኘው ከጉባ ቆርቻ ወረዳ ፣ ኦዳ አነኒ የሚባል ቀበሌ ነው። ዘንድሮ ጥሩ ዝናብ አግኝተው ትልቅ ምርት ይጠብቁ ነበር ፤ ነገር ግን የአምበጣ መንጋ መጥቶ ወሮባቸዋል፤ ይኸው ሁኔታ እጅግ ሀዘን ውስጥ ከቷቸዋል። የመንጋው እዛው ወረዳ ላይ የተለያዩ ቀበሌዎችንም ወሯል ፣ ኦዳ ዲማ ፣ እና ወደ ቆላማው ያሉትን ቀበሌዎች እጅጉን ጎድቷቸዋል።…
#UPDATE
አንበጣ መንጋው ዛሬ በጉባ ቆርቻ ወረዳ ያሉትን 22 ቀበሌዎች እና ሁለት ከተሞችን በሙሉ አዳርሷል።
የማሽላ እና ቦቆሎውን ጨርሶ ወደ ቦሎቄ ፣ ስንዴ ፣ ገብስ እና ባቄላ ተላልፏል።
የወረዳው አመራሮች ሁኔታው ከአቅማችን በላይ ሆኗል እያሉ ነው።
አውሮፕላንም ይሁን ድሮን ተልኮ ለአካባቢው ህዝብ ሊደረስለት እንደሚገባ የቲክቫህ አባላት መልዕክት አስተለፈዋል።
የአንበጣ መንጋው ጫትንም ወደ መብላት ዞሯል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አንበጣ መንጋው ዛሬ በጉባ ቆርቻ ወረዳ ያሉትን 22 ቀበሌዎች እና ሁለት ከተሞችን በሙሉ አዳርሷል።
የማሽላ እና ቦቆሎውን ጨርሶ ወደ ቦሎቄ ፣ ስንዴ ፣ ገብስ እና ባቄላ ተላልፏል።
የወረዳው አመራሮች ሁኔታው ከአቅማችን በላይ ሆኗል እያሉ ነው።
አውሮፕላንም ይሁን ድሮን ተልኮ ለአካባቢው ህዝብ ሊደረስለት እንደሚገባ የቲክቫህ አባላት መልዕክት አስተለፈዋል።
የአንበጣ መንጋው ጫትንም ወደ መብላት ዞሯል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ATTENTION📣
ምዕራብ ሀረርጌ ጭሮ ከተማ አንበጣ መንጋው ከቁጥጥር ውጪ እየሆነብን ነው ሲሉ በአካባቢው የሚኖሩ የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምዕራብ ሀረርጌ ጭሮ ከተማ አንበጣ መንጋው ከቁጥጥር ውጪ እየሆነብን ነው ሲሉ በአካባቢው የሚኖሩ የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#UPDATE
ዛሬን ጨምሮ ለ4 ቀናት በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ጉባ ቆርቻ ወረዳ የመንግስት መስሪያ ቤቶች መዘጋታቸውን የወረዳውን አመራሮችን ዋቢ በማድረግ 'ኢትዮጵያ ኢንሳይደር' ዘግቧል።
መስሪያ ቤቶች የተዘጉት በወረዳው ሁሉም ቀበሌዎች ላይ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ነው።

በትግራይ ክልል ያጋጠመውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ ባለሃብቶች፣ የግል እና የመንግስት ተቋማት በርካታ ድጋፎችን እያደረጉ ይገኛሉ። በሌላ በኩል ደግሞ የትግራይ ልማት ማህበር (TDA) gofundme በመክፈት በኢንተርኔት ባደረገው የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ዳይስፖራዎች ባደረጉት የገንዘብ ድጋፍ እስከ ዛሬ ጥዋት ድረስ ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ…
#UPDATE
የትግራይ ልማት ማህበር gofundme በመክፈት በኢንተርኔት እያደረገ በሚገኘው የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ከ19,000,000 ብር በላይ እገዛ ማድረግ ችለዋል።
በሌላ በኩል ኤርትራውያን በgofundme አማካኝነት በትግራይ ክልል ለተከሰተው የአንበጣ መንጋ መከላከል የሚውል እገዛ እያደረጉ ይገኛሉ ፤ እስካሁን (በአንድ ቀን) ከ600,000 ብር በላይ መሰብሰቡ ተገልጿል።
በተጨማሪም ዛምቢያ ውስጥ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ለአንበጣ መንጋ መከላከል ድጋፍ እንዲውል የ46,200 ብር እገዛ ማድረጋቸውን ለማውቅ ችለናል።
በሀገር ውስጥ እና በውጭ እየተደረገ የሚገኘው ድጋፍ አሁንም ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።