TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
❗️ዛሬ እንጂ የዛኔ ምርጫ የላችሁም❗️

እናንተ ግጭትን ለማብረድ ከመሞከር ይልቅ በተነሳው እሳት ላይ ቤንዚን እየጨመራችሁ ያላችሁ ግብዞች ሆይ!!

ይህ እውነት የተፃፈው ለእናንተ ነው፡፡ በዚህ ርኩሰት ተግባር ከቀጠላችሁ…

እንዲመጣ እየወተወታችሁት ያላችሁት ክፉ ቀን ቢመጣ እንዲህ እንዳሁኑ ፌስቡክ ላይ ተጥዳችሁ #መዘብዘብ አይታሰብም። ያኔ ምኞታችሁ ዛሬን በህይወት መክረም ብቻ ይሆናል።

ያኔ አይደለም እንደልባችሁ #ወጥታችሁ መግባት ይቅርና ሱቅ ደርሶ መመለስ ቅንጦት ሊሆንባችሁ ይችላል፡፡ ምክንያቱም እንዲነድ ያቀጣጠላችሁት እሳት ወላፈን. .. ከቤታችሁ ወጣ እንዳላችሁ ሊበላችሁ ይችላል። ለነገሩ እያቀጣጠላችሁት ያለው እሳት.....ከቤታችሁም ሆናችሁ ከሰል አድርጎ ሊያስቀራችሁ ይችላል።

ያኔ ሀገሪቱ በትናንሽ ባለጠመንጃ መንግስታት የምትመራ ስለምትሆን እንደልብ የምትተቹት መንግስት አይኖራችሁም። ይህ ነገር አሁን አይገባችሁም።

እናንተን ምናልባት የሚገባችሁ…⬇️

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህፃናት በመድሃኒትና በምግብ እጦት #ሲያልቁ ያዩ እናቶች... ልጆቻቸውን ለማትረፍ ወደ ስደት በሚያደርጉት ጉዞ የአውሬና የሽፍታ ሲሳይ ሆነው ሲቀሩ ያኔ ይገባችኋል።

አስፓልቶች በታንክ ታርሰው..... ከተማይቱ በህንፃ ፍርስራሽ ተሞልታ በዘሩ ምክንያት በየቀኑ በየጎዳናው የሞተው ቀባሪ ያጣ አስከሬን ሽታው አገሩን ሲሞላው ያኔ ይገባችሁ ይሆናል።

እመኑኝ ....ዛሬ ላይ ለተፋችኋት እያንዳንዷ #ብጥብጥ ቀስቃሽ መልእክታችሁ መፈጠራችሁን #እስክትረግሙ ዋጋ ትከፍልባታላችሁ። ለኃጥዓን የወረደው ለፃድቃን ይተርፋል እንደሚለው ቅዱስ መፅሃፉ ዳፋችሁ ለሁሉም ሲሆን ያኔ ይገባችሁ ይሆናል ።

ያ እንዲመጣ የምትፈልጉት ቀን ሲመጣ. .. #ክልላችሁ ወይም #ከተማችሁ አያድናችሁም። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የላካቸው ሰላም አስከባሪ #ወታደሮችም ከመጣባችሁ መዓት ፈፅሞ ሊያስጥሏችሁ አይችሉም ።

ምናለፋችሁ ዛሬ እንደዋዛ #እያቀጣጠላችሁት ያላችሁት እሳት ለጎረቤት ሃገራትም ይተርፋልና ክልሌ መሸሸጊያዬ ብላችሁ #እንዳታስቡ

ዛሬ በሀገር ሰላም በድንገት በህዝቦች መካከል የተፈጠሩ ግጭቶችን ላጋጋላችሁበት አንድ ቀን #በቁጭት እና #ፀፀት የደም እምባ እያነባችሁ በህይወታችሁ ዋጋ ትከፍሉበታላችሁ፡፡

አሁን እንጂ የዛኔ ምርጫ የላችሁም፡፡ ስለዚህ ያች እንድትመጣ እየጠራችኋት ያለችው ቀን ሳትመጣ፣ በዚች በመልካሟ በዛሬዋ ቀን ላይ ሳላችሁ ምርጫ አላችሁና አስቡበት።

ልቦና ይስጠን!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ጠብቅልን!

©ቂርቆስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia