የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች የተሻለ ዝግጅት እንዲኖራቸው መሥራት እንደሚገባ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አሳስቧል።
በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ጌታቸው ቢያዝን ለክልሉ ቴሌቪዥን (አማራ ቲቪ) ከተናገሩት የተወሰደ፦
- የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሀገር ዓቀፍ ፈተና በተሟላ መልኩ አስፈላጊውን ቅጽ (ፎርም) አልሞሉም ሆኖም የግል ተፈታኞችን ጨምሮ ከ90 ሺህ በላይ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
- ትምህርት ቤቶች በተለይ 8ኛ እና 12ኛ ክፍሎች ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲሠሩ ለማድረግ ጥረት ተደርጓል።
- አብዛኛው በሚባል መልኩ የአማራ ክልል ተማሪ ገጠር አካባቢ እንደመኖሩ በሚፈለገው ልክ ጥረቱ ውጤት አስመዝግቧል ማለት አይቻልም።
- ተማሪዎች የመማሪያ መጻሕፍቶቻቸው በእጃቸው ስላሉ እንዲያነብቡ፣ የ11ኛ ክፍል ትምህርቶችን መልሰው እንዲከልሱና ወላጆች ለልጆቻቸው አጋዥ መጻሕፍትን እንዲገዙላቸው መልእክት ተላልፏል።
- ሀገር አቀፍ ፈተናው በኢንተርኔት በመታገዝ በቀጥታ (ኦንላይን) እንደሆነ ከዚህ ቀደም ተገልጿል ፤ ተማሪዎች “ታብሌት” ተሰጥቷቸው እንዴት ጥያቄዎችን መሥራት እንዳለባቸው ከቴክኖሎጂ ውጤቱ ጋር የመለማመጃ ጊዜ ይኖራቸዋል።
- ሀገር አቀፍ ፈተናው መቼ እንደሚሰጥ በትምህርት ሚኒስቴርም ይሁን በሀገር ዓቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ ይፋ አልተደረገም።
- ትምህርት ከተጀመረ የመጀመሪያዎቹ 45 ቀናት ለ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎች የክለሳ ጊዜያቸው ይሆናል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ውሃ የያዘው የሀረማያ ሃይቅ!
ሀረማያ በውሃ እንደተሞላ አንዲቆይ ምን ይደረግ?
የሀረማያ አካባቢ አርሶ አደሮች በሚሰሩት የመስኖ ስራ ብዙ የውሃ ብክነት እንዳለ የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ስለዚህም የአካባቢው አርሶ አደሮች ውሃ ቆጣቢ የመስኖ ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀሙ ኀብረተሰቡን ማስተማር እና ግንዛቤ ማስጨበጥ የመፍትሄው አካል መሆን እንዳለበት ያሳስባሉ።
"ይህ ሀይቅ ባለቤት የሌለው ከሆነ ተመልሶ ይደርቃል ፤ ይህ መታወቅ አለበት" ብለዋል የሀረማያ ዩኒቨርስቲ ሀይድሮሊክና የውሃ ሃብት መሀንዲስ የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ኢንጂነር ተሾመ ስዩም።
ከዚህ ሌላ ሀረማያ ሀይቅ ድንበር የሌለው እንደመሆኑ መጠን ሀይቁ እንዲቆይ በማካለል ህብረተሰቡ በአግባቡ እንዲጠቀምበት ማድረግ ያሻል።
የሀረማያ ሀይቅ በሕይወት እንዲቆይ ለማድረግ የተፋሰስ ልማትን ማካሄድ ያስፈልጋል ፣ እየታጠበ ወደ ሀይቁ የሚገባውን አፈርን ለመቆጣጠርና ውሃ በስርዓቱ ወደ ሀይቁ እንዲፈስ ለማድረግ አስራ አምስት ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የተፋሰስ ልማት መሰራት እንደሚያስፍልግ ባለሙያዎች ይመክራሉ።
ይኹን አንጂ እስከዛሬ የተሰራው የተፋሰስ ልማት በቂ እንዳልሆነ ረዳት ፕሮፌሰሩ ገልፀዋል።
ችግኞች መትከልና መንከባከብን አከታትሎ መስራትን እንደሚጠይቅ የሚናገሩት እኚህ ምሁር "ሀይቁ አዋሳኝ አካባቢዎች አፈር ታጥቦ እንዳይገባ ሳር መትከል ላይ መስራት በጣም ወሳኝ መሆኑን ይናገራሉ።
ፅሁፉ ከBBC የአማርኛው አገልግሎት የተወሰደ ነው።
📸 Amanuel Ethicha

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ነባሮቹን የብር ኖቶች በአዲስ የመቀየር ሥራ ትላንት በይፋ ጀመሯል!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዘዳንት አቶ አቤ ሳኖ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ በመገኘት አዲሱን የብር ኖቶች ሥርጭት አስጀምረዋል፡፡
አዳዲስ የብር ኖቶችን በመጠቀምም የመጀመሪያዎቹ ሆነዋል፡፡ በትላንትናው ዕለት የተጀመረው አዳዲስ የብር ኖቶችን የማሰራጨት ሥራ በጥቂት ቀናት ወደ ክልሎች ማሰራጨት እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ገልፀዋል፡፡
ይህ ከፍተኛ የሆነ ዝግጅት የሚጠይቅ የብር ኖቶችን የመቀየር ሥራ በተሟላ መልኩ ተጠናቅቆ በመጀመሩ ደስታ እንደተሰማቸው ዶ/ር ይናገር አክለው ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዘዳንት አቶ አቤ ሳኖ በበኩላቸው ህብረተሰቡ አሮጌውን ብር በመመለስና አዳዲሶችን የብር ኖቶች በመውሰድ ብሩን የመቀየር ሂደት እንዲያቀላጥፍ አሳስበው፤ ከአምስት ሽህ ብር በላይ መቀየር የሚፈልግ ተጠቃሚ ነባር የባንክ ደብተር ከሌለው አዲስ መክፈት እንደሚጠበቅበትም ገልፀዋል፡፡
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ዛሬ ጠዋት ዘጠና አራት (94) አትዮጵያውያን ወገኖች ከሊባኖስ (ቤሩት) አዲስ አበባ ከተማ መግባታቸውን ሰምተናል። 9ኙ የአእምሮ ህመምተኞች በመሆናቸው በጤና ባለሞያዎች ታጅብው ነው የመጡት። እዚህም ሲደርሱ የጤና ሚኒስቴር ተረክቦ ወደ ጤና ማእከል ወስዷቸዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!
በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት እነ አቶ እስክንድር ነጋ በጠየቁት የዋስትና መብት እና የዐቃቤ ሕግ ምላሽ ላይ መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለመስከረም 12 ተለዋጭ ቀጠሮ ያዘ።
አቶ እስክንድርን ጨምሮ 7 ሰዎች የእርስ በርስ ግጭት መቀስቀስ እና በሽብር ወንጀል በዚህ ችሎት ክስ እንደተመሰረተባቸው ይታወሳል።
ይህን ተከትሎም በአካል ካልተገኙት 6ኛ እና 7ኛ ተከሳሾች በስተቀር ሌሎቹ አምስቱ ተከሳሾች በአካል በችሎት ተገኝተው ክሱ ተነቦላቸዋል።
የክስ መነበብን ተከትሎ በአራት ጠበቆች የተወከሉት አምስቱ ተከሳሾች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ለፈርድ ቤቱ ጥያቄ አቅርበዋል።
ዓቃቤ ሕግ በተለይ አቶ እስክንድር ነጋ በሽብር ወንጀል ተሳትፈዋል በሚል የተከሰሰ በመሆኑ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ እስከ 25 ዓመት የሚያስቀጣ በመሆኑ እና ድርጊቱም የሰው ህይወት የጠፋበትና ከ187 ሚሊዮን ብር በላይ የወደመበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሌሎቹም ተከሳሾች በተመሳሳይ መልክ የተከሰሱበት ጉዳይ ዋስት መብት የሚያስከለክል በመሆኑ ሕጉን በመጥቀስ ሕጉ የዋስትና መብትን ይከለክላል በማለት ተቃውሞ አቅርቧል።
ችሎቱ በዋስትና መብት ላይ የተነሳውን ክርክር የግራ ቀኙን መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠትና የመጀመሪያ የክስ መቃወሚያ ለመቀበል ለመስከከረም 12፣ 2013 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል። (ኢቲቪ)

በትግራይ ክልል ምርጫ ባይቶና አንድ ወንበር ማግኘቱ መገለፁ ይታወሳል ፣ ዛሬ ፓርቲው በሰጠው መግለጫ ወንበሩን ሊረከብበት የሚያስችል የሕገ አግባብ አለመኖሩ ገልጿል፡፡
ባይቶና በምርጫው ያገኘው 93,945 ድምፅ አንድ ወንበር ሊያስገኝለት የሚችል ሕጋዊ የቁጥር ስሌት አለመኖሩን ፣ ይልቁንስ የቀረው አንድ ወንበር ለህወሓት እንደሚገባ ፓርቲው ጠቁሟል፡፡
ከዚህ ውጭ ባይቶና በምርጫው ሂደት በርካታ ሕገ-ወጥ ተግባራት መፈፀማቸውን ጠቅሶ አውግዟል።
- በምርጫው ዕለት የባይቶና ታዛቢዎች በፖሊስ ከምርጫ ጣብያዎች እንዲወጡ ተደርጓል፣
- እጩዎች ታስረዋል፣ ዛቻ ደርሷቸዋል፤
- ህዝብ አማራጭ ፓርቲ እንዳይመርጥ በገዢው ፓርቲ ታችኛው መዋቅር ማስፈራራት ተፈፅሟል፣
- ለምረጡኝ ቅስቀሳ የተከራያቸው መኪና ባለቤቶች ታስረዋል የሚሉና ሌሎች ቅሬታዎች ከባይቶና ተነስተዋል፡፡
በዚህ ሁሉ ችግር መካከል ባይቶና ፓርቲ ቀላል የማይባል ድምፅ ማግኘቱ እና "የመጪው ግዜ ፓርቲ" መሆኑ አሳይቷ ሲሉ የፓርቲው ቃል አቀባይ አቶ ክንፈገብርኤል ገብረዮሐንስ መናገራቸውን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

በድሬዳዋ በህገ-ወጥ መንገድ ሲቀሳቀሱ የነበሩ የብር ኖቶች ተያዙ!
በድሬደዋ የፀጥታ አካላት በጋራ ባካሄዱት የክትትልና ቁጥጥር ስራ በህገ -ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የሀገርን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት የገንዘብ ኖቶች መያዛቸው ተገለፀ።
ገንዘቡ በቁጥጥር ስር የዋለው ትላንት መስከረም 6/2013 ዓ/ም ሲሆን ከህበረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማ መሰረት ባደረገ ክትልል መሆኑን ድሬ ፖሊስ አስታውቋል።
ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ መታየት መጀመሩም ተገልፃል።
በቁጥጥር ስር ከዋሉት የብር ኖቶች ውስጥ በዋነኝነት፦
-ዘጠኝ መቶ አርባ አርት ሺ አንድ መቶ አስር (944,110) የኢትዮጽያ ብር
-አንድ ሺ ሁለት መቶ ሀምሳ (1250) የአሜሪካን ዶላር
-አንድ መቶ ስልሳ አምስት (165)የሳውዲ ሪያል
-ሰባት መቶ አርባ አምስት (745) ዩሮ ሲሆኑ ከእነዚህ ጋር አብሮም ከዘጠኝ በላይ የሚሆኑ ሀገራት የተለያየ መጠን ያላቸው የብር ኖቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የፕ/ር ክንደያ ገ/ሂወት ከሃላፊነት መነሳት አፈፃፀም ዙርያ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞችና ማህበረሰብ የተነሱ ለቲቫህ ኢትዮጵያ የተላኩ ጥያቄዎች!
ሰሞኑ መቐለ ዩኒቨርሲቲን ላለፉት ሰባት (7) ዓመታት ፕሬዚዳንት ሆነው ያገለገሉት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሂወት የስልጣን ጊዜያቸው በመጠናቀቁ ኃላፊነቱ እንደተነሳላቸው የሚገልፅ ደብዳቤ ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ደርሷቸው ነበር።
የአንድ የዩኒቨርሲቲ መሪ የስልጣን ዘመን ሲጠናቀቅ ህግን የተከተለ መንገድ የመቀየር/የማስቀጠል አካሄድ እንዳለ ይታወቃል።
የፕሮፌሰር ክንደያ መነሳት በዚህ ረገድ ሲጠበቅ የነበረ እና እራሳቸውም ለቦርድ አሳውቀው ውሳኔ ሲጠብቁ የነበረ ጉዳይ ቢሆንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጉዳዩን ከሰሞኑ የፈፀመበት አካሄድ ግን ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና የተለያዩ ወገኖች የሚከተሉት ሃሳቦችን አስነስቷል ፦
- ተቋሙን የሚመራው ቦርድ ያልተወያየበት እና ውሳኔ ያልሰጠበት በመሆኑ የከፍተኛ ትምህርት መመርያ ይጥሳል፣
- በቅርብ አመታት በወጣው እና በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች በተተገበረው የዩነቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች አመራረጥ መመርያ ጋር ተያይዞ የፕሬዚዳንቱ የአግልግሎት ዘመን ማለቅ አስመልክት የወጣ የውድድር ማስታወቅያና የተካሄደ ውድድር አለመኖሩ፣
- የስንብት ደብዳቤውን የፃፉት የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ሚኒስቴር እና ስልጣናቸው በምክር ቤት ያልፀደቀ በመሆኑ ውሳኔውን ማስተላለፍ የማይችሉ ናቸው።
ሁኔታው ለነዚህ ጥያቄዎች የጠራ ምላሽ በማይሰጥ ሂደት በመፈፀሙ በርካቶች ድርጊቱ ከመዋቅራዊ አሰራር ይልቅ የትግራይ ክልል መንግስት ካካሄደው ምርጫ እና በምርጫው በታዛቢነት ከተሳተፉ የተቋሙ አጋር ተመራማሪዎች ጋር የተያያዘ በማእከላይ መንግስት የተሰጠ ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው ብለውታል።
@tikvahethiopiaBot

በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል የተከሰተውን ግድያ እና መፈናቀል አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ !
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia