TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፍርድ ቤት የአሥራት ጋዜጠኞች ላይ የተከፈተው መዝገብ ላይ ለመበየን ቀጠሮ ሰጠ!

በዋስትና እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው በኋላ ሲቪል በለበሱ ግለሰቦች በድጋሜ ታስረው ከሀጫሉ ግድያ በኋላ አመፅ አስነስተዋል በሚል ሌላ የምርመራ መዝገብ የተከፈተባቸው በላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብርና ምስጋናው ከፈለኝ ለመስከረም 7/2013 ዓ/ም ለብይን ተቀጠሩ።

የአሥራት ጋዜጠኞች በድጋሜ የተከፈተባቸውን መዝገብ ከቀደመው ጉዳይ የተለየ አይደለም ብለው በመከራከራቸው ፍርድ ቤቱ የፖሊስና የፍርድ ቤቱን መዝገብ መርምሮ በድጋሜ የተከፈተባቸው መዝገብ ከቀደመው የተለየ ስለመሆን አለመሆኑ ለመበየን ለዛሬ ቀጠሮ ይዞ ነበር።

የቀደሙት የፖሊስና የፍርድ ቤት መዝገቦች ከቀጠሮው ቀደም ብለው በድጋሜ ከተከፈተባቸው መዝገብ ጋር እንዲያያዙ አራዳ መጀመርያ አንደኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ፖሊስ መዝገቦቹን ያያያዘው ዛሬ ጠዋት መሆኑን ተናግሯል።

በዚህም ምክንያት ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት እንዳልቻለ ተገልፆአል። ፍርድ ቤቱ የአሥራት ጋዜጠኞች ሌላ መዝገብ የተከፈተባቸው ባለፈው ዋስትና ባገኙበት ተመሳሳይ ጉዳይ ነው ወይንስ አይደለም የሚለውን ለመበየን ለመስከረም 7/2013 ዓ/ም ከሰዓት ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ አስራት ቴሌቪዥን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ካርድ ተመሳስለው የተከፈቱ ገፆችን እያዘጋ ነው!

የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል የ50 ሚዲያዎች ፣ ፖለቲከኞች ፣ ጋዜጠኞች ፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሌሎችም እውነተኛ እና አስመሳይ (impersonating) ገጾችን ዘርዝሮ ለፌስቡክ ሰጥቶ ነበር።

ካርድ (CARD) በዚህ ሂድት ውስጥ በኢሳት ሥም የተከፈቱ 58 ፣ በኢትዮ 365 ሥም 32፣ በኦኤምኤን (OMN) ሥም 27 ፣ በአስራት ቲቪ 25 አስመሳይ ገጾችን አግኝቶ ለፌስቡክ ሪፖርት አድርጓል።

ካርድ ዝርዝሩን ለፌስቡክ ከሰጠ በኋላ እስካሁን ፦

- 13 የኢሳት ፣
- 11 የኢትዮ 65
- 5 የኦኤምኤን (OMN) እና 6 የአስራት ቲቪ አስመሳይ ገፆች #እንዲወገዱ ተደርጓል።

አስመሳይ ገጾች በእውነተኞቹ ድርጅቶች ወይም ሰዎች ሥም የተሳሳተ መልዕክት እያስተላለፉ ለተዛባ መረጃ መሥፋፋት አስተዋፅዖ እያደረጉ ስለሆነ ሁላችሁም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ጥንቃቄያችሁን አጠናክሩ ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
274 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ከሳኡዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ!

በሳኡዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ ውስጥ በተለያየ ችግር ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ሁለት መቶ ሰባ አራት (274) ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ዛሬ መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ/ም ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

ኢትዮጵያዊያን ዜጎቻችን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳ/ጄኔራል አቶ መስፍን ገ/ማርያምን ጨምሮ ከተለያዩ መ/ቤቶች የተወከሉ ባለሙያዎች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጨማሪ መረጃ ፦

በሳምንት ልዩነት ውስጥ ከሶስት መቶ (300) የማይበልጡ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራችን ይመለሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
600,000 ብር በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ ተያዘ!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ድንበር አካባቢ 600 ሺህ ብር በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የተገኘ ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ለኢዜአ አስታውቋል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሳ ሃሚድ እንደገለፁት ፦

- ግለሰቡ ገንዘቡን ሲያዘዋወር የተገኘው ትናንት በአሶሳ ዞን ሱዳን ጠረፍ በሆነችው ኩርሙክ ከተማ ውስጥ ነው፡፡

- ግለሰቡ 600 ሺህ ብር በሞተር ብስክሌት ጭኖ ሲጓዝ የጸጥታ ኃይሎች ባደረጉት ፍተሻ በቁጥጥር ስር ውሏል።

- በቁጥጥር ስር የዋለው ተጠርጣሪው ለፖሊስ በሰጠው ቃል ገንዘቡን ለወርቅ ግዥ እያንቀሳቀስኩ ነው ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ትምህርት ለማስጀመር ዝግጅት ተጠናቋል!

በአ/አ ከተማ አስተዳደር የ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመንን ለማስጀመር የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ለፋና ብሮስካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቋል።

ከትምህርት ቢሮው የተገኘ መረጃ ፦

- ከነሐሴ 20/2012 ዓ/ም ጀምሮ የግል ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን የመዘገቡ ሲሆን፤ በመንግሰት ትምህርት ቤቶች ከመስከረም 5 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎችን የመመዝገብ ስራ እያከናወኑ ነው።

- ትምህርት የሚጀምሩ ተማሪዎች ጤንነታቸው ተጠብቆ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉም ከወላጆች ፤ መምህራንና ርዕስ መምህራን ጋር ውይይት ይደረጋል።

- በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት የቅኝት ስራ በማከናወን ምን ያህል የመማሪያ ክፍል እና የተማሪዎች መገልገያ ቁሳቁስ እንዳለ ጥናት ተደርጓል።

- ሁሉም ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ተቀብለው ማስተማር ከመጀመራቸው በፊት የጸረ-ቫይረስ ኬሚካል ርጭት እንዲካሄድ ይደረጋል። ከጤና ባለሙያዎች ጋርም በቅርበት እየተሰራ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የጤና ሚኒስቴር ትምህርት ለመጀመር የሚስችል ሁኔታ መኖሩን ሲያረጋግጥልን ትምህርት እንጀምራለን" - ዶ/ር ኢንጂ. ጌታሁን መኩሪያ የትምህርት ሚኒስትር

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ስርጭት ያለበት ደረጃ ተገምግሞ ትምህርት ለመጀመር የሚያስችል ሁኔታ መኖሩን የጤና ሚኒስቴር ማረጋግጫ ሲሰጥና መንግስት ውሳኔ ሲያሳልፍ ትምህርት እንደሚጀመር የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ከትምህርት ገበታ ውጪ ያሉ ህፃናት በከፍትኛ ሁኔታ እየተጎዱ በመሆኑ ለእነሱ ቅድሚያ እንደሚሰጥም ነው ያብራሩት፡፡

ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ለ6 ወር ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ህፃናት ከዚያ በፊት ለሁለት አመታት ያክል ይዘውት የነበረውን እውቀት ሊያሳጣቸው ይችላል፡፡ በዚህ ምክንያት ለህፃናት ቅድሚያ ለመስጠት እቅድ ተይዟል፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው ህፃናት በኮሮና ቫይረስ የመያዝና የማስተላለፍ ባህሪያቸው ከሌሎቹ የቀነሰ በመሆኑ ድርጅቱ የሚያስቀምጣቸውን የቫይረሱን መከላከያ መንገዶች ሙሉ ለሙ በመተግበር ትምህርት ለመጀመር ጥረት ይደረጋል፡፡

በትምህርት አከፋፈት ዙሪያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታበተስፋፋባቸው እንደ አዲስ አበባ ባሉ ትላልቅ ከተሞች ትምህርት በ3 ፈረቃ ለመጀመር እቅድ ተይዟል፡፡

ከትላልቅ ከተሞች እርቀው የሚገኙና የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ስጋት በሌለባቸው አካባቢዎችም የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንግዶችን በመተግብር ትምህርት እንደሚጀመር የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Irreecha2013

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በተገኙበት ሲከበር የነበረው የኢሬቻ በዓል ዘንድሮ የኮቪድ -19 ወረርሽኝን ከግምት ባስገባ መልኩ እንደሚከበር አባገዳዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 ቀን 2013 ዓ.ም የሚከበር መሆኑንና የሆረ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል ደግሞ መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚከበር አባገዳዎቹ ገልጸዋል፡፡

በበዓሉ ላይ የሚሳተፉ ሰዎች ቁጥር በሽታውን (ኮሮና ቫይረስ) ለመከላከል በሚያመች መልኩና የጤና ባለሙያዎች በሚሰጡት ምክር መሰረት የሚወሰን መሆኑ ተገልጿል፡፡

የገዳ ስርዓት ባለቤት የሆነው የኦሮሞ ህዝብ የአባ ገዳዎችን ጥሪና የጤና ባለሙያዎቸን ምክር ተከትሎ በዓሉን እንዲያከብር አባገዳዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ፣ ኢቲቪ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TikvahFamilyBulen በቡለን ወረዳ በተፈፀመ ጥቃት የሰዎች ህይወት መጥፋቱን እንዲሁም በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የቤኒሻነጉል ጉሙዝ ክልል ቡለን ወረዳ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት አሳውቀል። የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የጤና ባለሞያዎች እንደተናገሩት በሚሰሩበት የጤና ተቋም ጉዳት ደርሶባቸው የመጡ የፀጥታ ኃይል አባላት ስምንት (8) የሚደርሱ እና በርካታ ነዋሪዎች አሉ። ከነዋሪዎች መካከል…
"ከአንድ ሳምንት በኋላ እስካሁን ድረስ የአባቴን አስከሬን አግኝቼ ለመቅበር አልቻልኩም" - አቶ ኃይሉ አዲሱ

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአንድ ሳምንት በፊት በቤኒሻንጉል ክልል ቡለን ወረዳ እየተፈፀመ ስላለ ጥቃት ከቡለን ቲክቫህ አባላት የተላከውን መረጃ ማካፈሉ የሚዘነጋ አይደለም።

በወቅቱ ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉ አባላቶቻችን አልገለፁም ነገር ግን በጥቃቱ ህይወታቸው ያለፈ ነዋሪዎች መኖራቸው ፣ የፀጥታ ኃይል አባላት መገደላቸውን፣ እንዲሁም ብዙ ሰዎች መቁሰላቸውን አሳውቀው ነበር።

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በዛሬው ዕለት BBC በአካባቢው ጥቃት ሰለባ ከሆኑና ቤተሰቦቻቸውን ያጡ የአካባቢው ነዋሪዎችን አነጋግሮ በድረ ገፁ ሰፋ ያለ ዘገባ ይዞ ወጥቷል ፤ በማስፈንጠሪያው ገብታችሁ አንብቡ : https://telegra.ph/Bulen-09-16

PHOTO : የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
600,000 ብር በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ ተያዘ! በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ድንበር አካባቢ 600 ሺህ ብር በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የተገኘ ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ለኢዜአ አስታውቋል።  የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሳ ሃሚድ እንደገለፁት ፦ - ግለሰቡ ገንዘቡን ሲያዘዋወር የተገኘው ትናንት በአሶሳ ዞን ሱዳን ጠረፍ…
ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ህገ-ወጥ ገንዘብ በቁጥጥር ስር ዋለ!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ተጨማሪ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ለኢዜአ አስታወቀ፡፡

የክልሉ ፓሊስ ባደረገው ክትትል ትላንት ምሽት ደንጎሮ ኬላ በተሽከርካሪ ውስጥ በማዳበሪያ ተጠቅጥቆ ሊያልፍ የነበረ 770 ሺህ ብር በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል፡፡

እንዲሁም ዛሬ ማለዳ ደግሞ ማንኩሽ ኬላ ላይ ሌላ 300 ሺህ ብር እንዲሁ በሻንጣ ለማሳለፍ ሲሞከር በተደረገ ፍተሻ በቁጥጥር ስር እንደዋለ አስታውቀዋል፡፡

ገንዘቡን ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሁለት (2) ግለሰቦችም በፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆናቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoH

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 1 ሺህ 311 የጤና ባለሙያዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል።

በነገው ዕለት የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሕሙማን ደህንነት ቀንን አስመልክቶ ዛሬ ጤና ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የሚኒስቴሩ የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ያዕቆብ ሰማን ተከታዩን ብለዋል ፦

- ኮሮና ቫይረስን በመከላከል ሥራ ግንባር ቀደም የሆኑ የሕክምና ባለሙያዎች ላይ መጠነ ሰፊ ችግር አስከትሏል።

- 1 ሺህ 311 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ 700 የሚሆኑት ደግሞ አገግመው ወጥተዋል፤ ቀሪዎቹ በህክምና ተቋማት ይገኛሉ።

- ሁለት የሕክምና ባለሙያዎችም ለሞት ተዳርገዋል።

- ነገ ለሁለተኛ ጊዜ በአገሪቱ የሚከበረው የሕሙማን ቀን ቫይረሱ የተገኘባቸው ወገኖቻቸውን ሌት ተቀን እያገለገሉ ላሉ ባለሙያዎችና አጋሮቻቸው ክብርና ምስጋናን በመስጠት ይከበራል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ በብድር እና በስጦታ ውሎች ላይ የሚከተለውን ማሳሳቢያ እና ቅድመ ሁኔታ አውጥቷል!

1. የስጦታ ውልን በሚመለከት ፦

• የአሰራር ማሻሻያዎች እስኪደረጉ ድረስ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀ ንብረትን በስጦታ የማስተላለፍ ውል አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ከነገ መስከረም 7 ጀምሮ አይሰጥም።

2. የሽያጭ እና የብድር ውልን በሚመለከት ፦

• የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል እንዲሁም የብድር ውሎችን ሰነድ አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ለማግኘት የሽያጭ ዋጋ ወይም የብድሩ ገንዘብ በባንክ በኩል ብቻ ማለትም ከሻጭ ወይም ከአበዳሪ የባንክ ሒሳብ ብቻ ተቀናሽ ተደረጎ ወደ ገዥ ወይም ተበዳሪ የባንክ ሒሳብ መተላለፍ (transfer) የተደረገ ሲሆን ብቻ ነው፡፡

Via abyassinaialw /Elias Meseret/
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መስከረም 6/2013 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 119 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 18 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 31 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 16 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Harari

በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 503 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 11 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#DireDawa

ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 85 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 18 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 398 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 49 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1,141 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 24 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል (ከወልዲያ ሆስፒታል በአስክሬን ምርመራ)

#Sidama

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 90 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 23 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1,402 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 228 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 488 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 40 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBOT
የመስከረም 6 ሀገር አቀፍ የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 8,355
በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ - 738
ከበሽታው ያገገሙ - 677
ህይወታቸው ያለፈ - 10

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia