TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

በወላይታ ሶዶ፣ ቦዲቲ፣ አረካ ለ4ኛ ቀን የንግድ እና ትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንደቆመ ነው። በወላይታ ዞን ካለፉት ቀናት የተሻለ መረጋጋት ይታያል። አሁንም የፀጥታ ኃይሎች በየአካባቢው በስፋት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። የወላይታ የቲክቫህ አባላት እንዳሳወቁት ዛሬም የዳታ ኢንተርኔት አገልግሎት አልተከፈተም።

PHOTO : TEMESGEN
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢሶዴፓ መግለጫ!

በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄ በማንሳት የሚንቀሳቀሰው የዞኑ አመራር እና ሕዝብ በሕገ መንግስቱ ድንጋጌ መሠረት ተገቢ መልስ በሰላማዊ አግባብ ሊሰጠው ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ /ኢሶዴፓ/ ጠየቀ።

ኢሶዴፓ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ በዞኑ ለተነሳው ሕገ-መንግሥታዊ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ በመስጠት፣ ጥያቄውን በማንገብ ምላሽ ለመሻት የተንቀሳቀሱትን የወላይታ ዞን አመራር አካላትን እና በጉዳዩ ሳቢያ የታሰሩትን ሁሉ በመፍታት፣ ለተከሰተው ችግር ሰላማዊ መፍትሄ በአስቸኳይ እንዲፈልግ አሳስቧል።

አስተዋዩና ሰፊው የወላይታ ሕዝብ ጉዳዩን በወትሮ ጥበቡ በትዕግስት በመያዝ ፣ የሰላማዊ መፍትሄ አካል እንዲሆን ኢሶዴፓ ጥሪ አድርጓል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በወላይታ ዞን የተፈጠረው አለመረጋጋት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ ባህር ዳር ከተማ ይገኛሉ።

በሀዋሳ ከተማ የተጀመረው የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ተጠናቋል።

ዶ/ር አብይ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ 5 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል የታቀደው ዕቅድ ሙሉ በሙሉ መሳካቱን ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ዶ/ር አብይ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ባካሄደው የሁለት ቀናት ውይይት ማጠናቀቂያ ላይ መገኘታቸውን በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

በወልቂጤ ከተማ የ55 ሰዎች ናሙና በመውሰድ በድንገት በተሰራ የኮቪድ-19 ምርመራ አንድ የ29 ዓመት አሽሽከርካሪ በቫይረሱ መያዙን በደረሰን መረጃ ለማረጋገጥ ችለናል።

የወልቂጤ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳያስ ናስር እንዲህ አይነት ምርመራ በቀጣይም እንደሚቀጥል አሰታውቀዋል።

አቶ ኢሳያስ ህብረተሰቡ በከተማው እየተስተዋለ ከሚገኘው መዘናጋት በመውጣት ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ (ርቀት መጠበቅ ፣ ማስክና ሳኒታይዘር መጠቀ) አጥብቀው አሳስበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኦነግ 6 አመራሮቹን ለጊዜው ማገዱን አስታውቋል!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ በይፋዊ ፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ አቶ አራርሶ ቢቂላ ፣ አቶ ቶሌራ አዳባና አቶ ቀጄላ መርዳሳን ጨምሮ ስድስት ከፍተኛ አመራሮቹን #ለጊዜው ማገዱን አስታውቋል፡፡

በእግዱ ተካተዋል የተባሉ አመራሮች ነሐሴ 4 ቀን የድርጅቱ አመራሮች ጋዜጣዊ መግለጫ በሂልተን ሆቴል መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

የድርጅቱ ሊቀ መንበር አቶ ዳዎድ ኢብሳ በበኩላቸው የተሰጠው መግለጫ የፓርቲያቸው እውቅና እንደሌለውና እርሳቸውም ስለ መግለጫው መረጃ እንደሌላቸው ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።

ከዚህም አስቀድሞ የፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር በአቶ አራርሶ ቢቂላ የተመራው ስብሰባ በኀላ በተነሱ ጉዳዮችና ልዩነቶች ላይ የፓርቲው የህግና ቁጥጥር ኮሚቴ እንዲያጣራ መወሰኑን አመራሮቹ ገልጸው ነበር።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ATTENTION

ነቀምቴ፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሞጆ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ!

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 2,272 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አንድ መቶ ስምንት (108) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ከነዚህ መካከል፦

- 27 ከአዳማ
- 20 ከነቀምቴ
- 16 ከሞጆ
- 12 ከቢሾፍቱ
- 7 ከቡራዩ ይገኙበታል።

በኦሮሚያ ያለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በእጅጉ እየጨመረ በመሆኑ ወረርሽኙ ከቁጥጥር ውጭ ወጥቶ ለመቆጣጠር ፈተናው እንዳይበረታ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የእነ አቶ እስክንድር ነጋ የፍርድ ቤት ውሎ!

ዛሬ በዋለው ችሎት አቃቤ ሕግ ያቀረበውን የሰው ምስክሮች ግማሾቹ ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው ግማሾቹ ደግሞ በዝግ ችሎት እንዲመሰክሩ ብይን መሥጠቱን ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አሳውቌል።

እነ አቶ እስክንድር ነጋ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ ከዚህ በኋላ የክርክሩ አካል መሆን እንደማይፈልጉ ስለዚህም በሁሉም ስምምነት ጠበቆቻቸውን #ማሰናበታቸውን ፣ ከዚህ በኃላ በግዳጅ ካላቀረቡን በስተቀር አንከራከርም ፣ አንቀርብምም ማለታቸውን ፓርቲው በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ገልጿል።

ፍረድ ቤቱ ምስክሮችን በነሃሴ 8/2012 ዓ/ም እንዲቀርቡ አዟል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 6/2012 ዓ/ም - ወላይታ ዞን!

ዛሬ በወላይታ ዞን ወረዳዎች እና የተለያዩ ከተማዎች ሰላማዊ ሰልፎች ሲደረጉ እንደነበር የወላይታ ዞን ቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።

ሰልፈኞቹ ፥ 'የታሱሩት የዞኑ መሪዎች ይፈቱ፣ ያለ ህዝብ ፍላጎት ከኃላፊነታቸው ሊነሱ አይገባም፣ በንፁሃን ላይ የተፈፀመውም ግድያ እናወግዛለን፣ የሰው ህይወት ያጠፉ ተጣርቶ ለፍርድ ይቅረቡ' ሲሉ ጠይቀዋል።

በቦዲቲ፣ በዴሳ፣ ጉኑኖ መንገዶች ተዘግተው እንደነበር የሰዎችም እንቅስቃሴ ተገቶ መቆየቱን አባላቶቻችን ገልፀዋል።

ዛሬም መስሪያ ቤቶች ፣ባንኮች ዝግ ሆነው ውለዋል፤ የትራንስፖርትና የንግድ እንቅስቃሴ፣ እንዲሁም የዳታ ኢንተርኔት አገልግሎት እንደተቋረጠ ነው።

ዛሬ ከሰዓት ከሰሞኑን የነበረው ውጥረት እየረገበ በነበረባት ወላይታ ሶዶ ከተማ ግብርና ኮሌጅ አከባቢ የሰው ህይወት ማለፉና ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።

በሌላ በኩል ከሰሞኑን በቁጥጥር ስር የዋሉት የዞኑ አመራሮች ፣ ምሩናን እና አክቲቪስቶች ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተሰምቷል ፤ ሂደቱ ለሚዲያዎች ዝግ እንደነበር ተነግሯል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የዓለም ጤና ድርጅት ሩሲያ ስራ ላይ ለማዋል ያዘጋጀችው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ውጤታማነትና ትክክለኛነት ላይ ከሩሲያ ጋር ውይይት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።

ድርጅቱ ከሩሲያ የጤና ዘርፍ ባለሥልጣናት ጋር በጉዳዩ ላይ በቅርበት እየተነጋገረ እንደሚገኝ ገልጿል።

በሩሲያ የተዘጋጀው ክትባት ለክትባት ዝግጅት የሚያስፈልጉ ሁሉም መስፈርቶች ማሟላቱን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ቃል አቀባይ ታሪክ ገጃሳሬቪክ በጄኔቫ መናገራቸውን ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ ኢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 943 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 14,540 የላብራቶሪ ምርመራ 943 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ23 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 338 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 25,118 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 463 ደርሷል ፤ እንዲሁም አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 11,034 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 216 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- 1 ከመተከል ዞን ጉባ ወረዳ
- 2 ከአሶሳ ዞን አሶሳ ወረዳ

#Harari

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 670 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 15 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የሁለት ሰዎችም ህይወት አልፏል።

አጠቃላይ በሀረሪ ፦
- 366 በቫይረሱ የተያዙ
- 14 ሞት
- 78 ያገገሙ

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 586 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 66 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ ትላንት 39 ሰዎች አገግመዋል።

አጠቃላይ በትግራይ ፦
- 1,252 በቫይረሱ የተያዙ
- 10 ሞት
- 697 ያገገሙ

#DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 250 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 36 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። 10 ከጅቡቲ ተመላሾች በለይቶ ማቆያ የነበሩ ሲሆኑ፤ 26 ከማህበረሰቡ በተወሰደ ናሙና የተገኙ ናቸው።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 4,086 የላብራቶሪ ምርመራ 70 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ከነዚህ መካከል

- 25 ከባህር ዳር
- 13 ከምዕራብ ጎንደር ዞን
- 12 ከሰሜን ሸዋ ዞን
- 7 ከደ/ጎንዳር ዞን
- 6 ከሰ/ወሎ ዞን
- 3 ከምስ/ጎጃም ዞን
- 3 ከደሴ ከተማ
- 1 ከማዕ/ጎንድር

#Sidama

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 252 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 14 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፤ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል። በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 6 ሰዎች ከሀዋሳ ይገኙበታል።

#CARD #TIKVAH
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በሀገር አቀፍ ደረጃ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ 943 ሰዎች መካከል 612 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከተማ ናቸው።

ከፍተኛ ኬዝ ከተመዘገበባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ክፍለ ከተማዎች መካከል አራዳ (124)፣ ቦሌ (84)፣ ጉለሌ (80) በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።

በተጨማሪ በ24 ሰዓት በሀገሪቱ ከተመዘገበው ሃያ ሶስት የሟቾች ቁጥር 18 ከአዲስ አበባ ከተማ ናቸው ፤ 13 ሰዎች ከአስክሬን ምርመራና 5 ሰዎች ከጤና ተቋም መሆናቸውን የከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ መረጃ ያሳያል።

#CARD #TIKVAH
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያና ጎረቤት ሀገራት የኮቪድ-19 ስርጭት !

በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ በአጠቃላይ 76,587 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።

ከኤርትራ ውጭ በ6ቱ ሀገራት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የ1,904 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተረጋግጧል ፤ በአጠቃላይ 40,210 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በኢትዮጵያና በጎረቤት ሀገራት ያለውን የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ ከ CARD ጋር በመተባበር ባዘጋጀነው ምስል ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia