TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀረሪ

በሐረሪ ክልላዊ መስተዳድር ስር በሚገኘው #ጅኔላ_ወረዳ በአካባቢው የሚኖሩ ከስልሳ በላይ ቤቶች ከሌላ አካባቢ መጡ በተባሉ አካላት ጥቃት ተፈፀመባቸው።

የተወሰኑ ነዋሪዎች በሁኔታው በመስጋት ቤታቸውን ጥለው ስለመውጣታቸው ጀርመን ራድዮ ደረሰኝ ባለው መረጃ ጠቁሟል።

ጥቃት ፈጻሚዎቹ ወደ ነዋሪዎቹ መኖሪያ ቤት በመዝለቅ የተለያዩ ንብረቶች ሰባብረዋል ተብሏል። በስፍራው የተገኘው የDW ዘጋቢ የአንዳንድ መኖርያ ቤት አጥሮች ፈርሰው፣ አንዳንዶችም በስለት (ባንጋ) መቆራረጣቸውን ታዝቧል። የውሀ መስመር እና የመብራት ቆጣሪ የተሰባበረበት መኖርያ ቤትንም ተመልክቷል።

ጥቃቱ የተፈጸመው “የአካባቢው መሬት የእኛ በመሆኑ ልቀቁ በሚሉ አካላት” መሆኑን የሚናገሩት ተጎጂ ነዋሪዎች በድርጊቱ ማዘናቸውን ለጀርመን ራድዮ ገልጸዋል። “አሁንም ችግራችንን #አውጥተን ለሚዲያ #ለመናገር እንሰጋለን፤ ህይወታችንም ያሳስበናል፤ ምን ዋስትና አለን” ሲሉ ስማቸውን ለመግለፅ የፈሩ ነዋሪ ተናግረዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ ኃላፊ “ግጭቱ መኖርያ ቤቶቹ ከተገነቡበት ቦታ የይገባኛል ጥያቄ ጋር በተያያዘ የተፈጠረ” መሆኑን ተናግረዋል። እንደ ኃላፊው ገለጻ በግጭቱ የሰው ህይወት ላይ የደረሰ ነገር ባይኖርም በጥይት የተመታ አንድ ሰው ግለሰብን ጨምሮ አራት ሰዎች ተጎድተዋል። በጥይት ተመቷል የተባለው ግለሰብም በሆስፒታል ህክምና እየተከታተለ እንደሚገኝም አስረድተዋል። በግጭቱ በስልሳ አንድ መኖርያ ቤቶች ላይ ጥቃት ሲደርስ ዝርፊያና ንብረት ማውደም ተፈፅሟልም ብለዋል።

ህብረተሰቡን የማወያየት ስራ እየተሰራ መሆኑ እና የተፈጠረው ሁኔታም #ተረጋግቷል ቢባልም ችግሩ መሰረታዊ መፍትሄ ያላገኘ በመሆኑ በነዋሪዎች አንድ አሁንም ስጋቶች እንዳሉ ናቸው።

#የመከላከያ_ሰራዊት አባላት ግጭቱን ለማረጋጋት በአካባቢው ሲዘዋወሩ የጀርመን ራድዮ ዘጋቢ የተመለከተ ሲሆን ነዋሪዎች ዱላ፣ ስለታም ነገሮች (መቁረጫ ባንጋ) ይዘው አካባቢያቸውን ሲጠብቁ አስተውሏል። ሐኪም ጋራ እየተባለ በሚጠራው በዚህ አካባቢ የተፈጠረው ሁኔታ ባለመረጋጋቱ ከ150 በላይ ነዋሪዎች በየዕለቱ የአካባቢውን ሰላም ለመጠበቅ ተሰባስበው በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸው ታውቋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ (አማርኛው አግልግሎት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia