TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 57 ደረሰ!

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርመራ ውስጥ 30 (24 ከጤና ተቋም እና 6 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን በሁለት (2) ናሙናዎች (1 ከጤና ተቋምና 1 ከማህበረሰቡ) የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። ሁለቱም የአዲስ አበባ ነዋሪ የነበሩ ሴትና ወንድ ኢትዮጵያውያን ናቸው።

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸውና ህይወታቸው የለፈ ሰዎች ቁጥር ሃምሳ ሰባት (57) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#OROMIA

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 215 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 15 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

- 3 ሰዎች ከጉጂ (የ1 ዓመት ህፃን ሴት፣ የ42 ዓመትና የ54 ዓመት ወንድ) ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌላቸው፤ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው።

- 2 ሰዎች ከሰበታ (የ47 ዓመት ወንድና የ32 ዓመት ሴት) ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌላቸው፤ ወንዱ ከማህበረሰቡ የተገኘ ሴቷ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላት።

- 7 ሰዎች ከቡራዩ (የዕድሜ ክልላቸው ከ21-37 ውስጥ ይገኛል) ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የላቸውም፤ 3 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው፣ የተቀሩት ከማህበረሰቡ የተገኙ።

- 2 ሰዎች ከለገጣፎ (የ14 ዓመት ወንድና የ21 ዓመት ሴር )፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌላቸው፤ ከማህበረሰቡ የተገኙ።

- 1 ሰው ከሱሉልታ (የ40 ዓመት ወንድ)፤
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

#AMHARA

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው ምርመራ 524 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 23 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

20 ሰዎች በምዕ/ጎንደር ዞን በሚገኙ ለይቶ ማቆያ ማዕከላት ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ (የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው) ናቸው።

2 ሰዎች በጎንደር ከተማ በሚገኘው ማራኪ ለይቶ ማከሚያ ማዕከል የነበሩ እንዲሁም 1 ሰው በሰ/ወሎ ዞን በሚገኘው ላልይበላ ለይቶ ማቆያ ማዕከል የነበረ።

በፆታ አኳያ 21 ወንድና 2 ሴት ናቸው ፤ የእድሜ ክልላቸው ከ16 እስከ 22 ዓመት ውስጥ ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TIGRAY

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 219 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 9 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።

ከዘጠኙ መካከል 6 የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ 3 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ናቸው።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 44 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 426 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 2 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

ታማሚ 1 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ የካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ የሌለው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው።

ታማሚ 2 - የ36 ዓመት ኢትዮጵያዊ የካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ያለው የረዥም ርቀት አሽከርካሪ ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው ነው።

#AFAR

በአፋር ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 47 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተካሄደው የላብራቶሪ ምርመራ 147 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 11 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።

#DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ አስተደር 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጧል። በቫይረሱ የተያዙት የ33 እና የ23 ዓመት ወጣቶች ናቸው። ሁለቱም በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉና አንደኛው ግለሰብ ቀደም ሲል በቫይረሱ ተይዞ በህክምና ማዕከል ውስጥ ካለ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ያለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከጅቡቲ ተመላሽ ነው።

#HARARI

ባለፉት 24 ሰዓት በሐረሪ ክልል 53 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 1 ሰው በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠው። በቫይረሱ የተያዘው የ4 ወር ህፃን ወንድ ሲሆን የድሬ ጠያራ ወረዳ ነዋሪ ነው።

#tikvah
#ATTENTION

በአዲስ አበባ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2,479 ደርሷል!

በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ሰኔ 7/2012 ዓ/ም ድረስ በተደረጉ የላብራቶሪ ምርመራዎች 2,479 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት ቫይረሱ የተገኘባቸው 111 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 2 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ፣ 14 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን የተቀሩት 95 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው ናቸው።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው አንድ መቶ አስራ አንድ (111) ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦

• አዲስ ከተማ - 18 ሰዎች
• ቦሌ - 14 ሰዎች
• ጉለሌ - 18 ሰዎች
• ልደታ - 16 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 19 ሰዎች
• የካ - 2 ሰዎች
• አራዳ - 13 ሰዎች
• ቂርቆስ - 5 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 5 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 1 ሰው
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 0

አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 2,479 ሰዎች ክፍለ ከተማ እንደሚከተለው ቀርቧል ፦

• አዲስ ከተማ - 553 ሰዎች
• ቦሌ - 407 ሰዎች
• ጉለሌ - 282 ሰዎች
• ልደታ - 252 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 235 ሰዎች
• የካ - 142 ሰዎች
• አራዳ - 142 ሰዎች
• ቂርቆስ - 139 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 129 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 77 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 121 ሰዎች

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በሕብረተሰቡ ውስጥ ባለው የቫይረሱ ስርጭት ምክንያት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከዕለት ዕለት በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ነው።

በመሆኑም እኛ ወይም የምንወደው ሰው ቀጥሎ በቫይረሱ የሚያዘው ሰው ልንሆን እንደሚችል በመገንዘብ ከመቼውም ግዜ በላይ በመጠንቀቅ ስርጭቱን ማቆም እንችላለን።

በዚህ ወረርሽኝ አንዳችን ለአንዳችን ዘብ በመቆም የኮሮና ቫይረስ የመከላከያ ዘዴዎችን በመተግበር አንዳችን ስንዘናጋ ሌላችን ካስታወስን ህይወት ልናተርፍ እንችላለን። በመሆኑም የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን አንዱን ዘዴ ከሌላው ሳናማርጥ በሙሉ መተግበር ይገባናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከአ/አ ወደ ወላይታ ዞን የገባው የኮቪድ-19 ታማሚ!

ባለፉት 24 ሰዓት ዉስጥ በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ በሽታ (COVID-19) ላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ የኮሮና ቫይረስ በሽታ እንዳለበት የተረጋገጠበት አንድ ዕድሜው 20 የሆነ ግለሰብ ትክክለኛ ባለሆነ መንገድ ተደብቆ ህብረተሰቡን ለአደጋ ሊያጋልጥ በሚችል መልኩ ቤተሰቦቹ ወደሚገኙበት ወላይታ ዞን ገብቷል።

ግለሰቡ ወደ ወላይታ ዞን ከገባ በኋላ በህብረተሰቡ ትብብርና በመንግስት በኩል በተደረገ ክትትል እንዲያዘ ተደርጎ ወደ ህክምና ማዕከል እንዲገባ ተደርጓል።

ግለሰቡ ወደ ወላይታ የመጣበትን ተሸከርካሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚመለከታቸው አካላት ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመተባበር ክትትል እያደረጉ የሚገኝ በመሆኑ ህብረተሰቡ የተለመደውን #ትብብሩን እንዲያደርግ የደቡብ ክልሉ ጤና ቢሮ ጥሪውን አስተላልፏል።

የኮሮና ቫይረስ ከተስፋፋባቸዉ የሀገሪቱ ክልሎች የሚመጡ የክልሉ ነዋሪዎች ራሳቸውን ከቫይረሱ ይበልጥ በመጠበቅ ለራሳቸው፣ ለቤተሰባቸው ፣ ብሎም ለአጠቃላይ ማህበረሰቡ ያላቸው ፍቅርና አክብሮት እንዲገልፁና ቫይረሱን በጋራ በመከላከል መደጋገፍ እንዲኖር ቢሮው ጥሪውን አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በቻይና የተገኙት 57 የኮቪድ-19 ታማሚዎች...

በቻይና 57 አዲስ በኮሮና ቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል። ይህም ከሚያዝያ ወር አጋማሽ ወዲህ በአንድ ቀን የተመዘገበ ከፍተኛ ቁጥር መሆኑን #BBC አስነብቧል።

የቻይና ብሔራዊ ጤና ኮሚሽን 38ቱ ከማህበረሰቡ ውስጥ የተገኙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ሰላሳ ስድስቱ (36) በቤጂንግ የተገኙ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

ከትናንት አንስቶ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የተያዙ አዳዲስ ሰዎች መገኘታቸውን ተከትሎም በአንዳንድ አካባቢዎች ከቤት ያለመውጣት #ገደብ እንደገና ተጥሏል፡፡

አብዛኞቹ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙት 'ከገበያ ቦታዎች' ጋር በተገናኘ ነው፡፡ በዚህም በአቅራቢያው ያሉ አስራ አንድ (11) የመኖሪያ መንደሮች እንዲዘጉ ተደርገዋል፡፡ ነዋሪዎቹ መውጣት የሚፈቀድላቸው መሰረታዊ ግዥ ለመፈጸም ብቻ ነው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኢትዮጵያና ጎረቤት ሀገራት...

በኢትዮጵያ ፣ ኬንያ ፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ በአጠቃላይ 22,787 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።

ከኤርትራ ውጭ በስድስቱ (6) ሀገራት የ765 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ በአጠቃላይ 7,969 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።

በኢትዮጵያና በጎረቤት ሀገራት ያለውን የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ ከ CARD ጋር በመተባበር ባዘጋጀነው ምስል ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ስርጭት በእጅጉ እየጨመረ ይገኛል ፤ ከምን ጊዜውም በላይ ጥንቃቄዎች ሊጠናከሩ ይገባል። ከፍተኛ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች የተመዘገቡባቸው 5 ክልሎች የሚከተሉት ናቸው ፦

• ሱማሌ ክልል በቫይረሱ የተያዙ 221፣ ሞት 1፣ ያገገሙ 47

• አማራ ክልል በቫይረሱ የተያዙ 198፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 39

• ኦሮሚያ ክልል በቫይረሱ የተያዙ 194፣ሞት 7፣ ያገገሙ 26

• ትግራይ ክልል በቫይረሱ የተያዙ 122፣ ሞት 1፣ያገገሙ 10

• አፋር ክልል በቫይረሱ የተያዙ 47 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 33

ከላይ በተዘረዘሩት አምስቱ (5) ክልሎች ውስጥ የተደረጉትን አጠቃላይ የላብራቶሪ ምርመራዎችን የተመለከትን እንደሆነ ሱማሌ ክልል 4,365 ፣ አማራ ክልል 4,966 ፣ ኦሮሚያ ክልል 13,640 ፣ ትግራይ ክልል 5,399 እንዲሁም አፋር ክልል 1,711 ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አእምሮአችንን እንጠብቅ!

(በዶ/ር ቤዛዊት ፀጋዬ)

ኮቪድ-19 የለመድነውን የኑሮ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ቀይሮታል። ይህ ሲሆን ታድያ በሽታው በቀጥታ ከሚያመጣው ጉዳት በተጨማሪ በተለያየ መልኩ ሊገለፅ የሚችል ጭንቀት ይህም ቀጣይነት የሚኖረው ስነ-ልቦናዊ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።

ምልክቶች:-

1. ስለራስና ስለ ቤተሰብ/ወዳጅ ጤና አጥብቆ ማሰብ
2. የአመጋገብ እና የእንቅልፍ ሁኔታ እና ሰዓት መቀያየር
3. ከዚህ በፊት የነበሩ የጤናም ሆነ የአእምሮ ችግሮች መባባስ
4. አልኮል፣ሲጋራና ሌሎች አደንዛዥ ዕፆችን መጠቀም መጀመር/ይበልጥ መጠቀም

መፍትሄ:-

1. በማህበራዊ ሚዲያዎችና መሰል ሚዲያዎች ላይ የምናጠፋውን ሰዐት መገደብ፤ የምንሰማቸውን ዜናዎችና መረጃዎች መምረጥና ከተሳሳቱ ምንጮች መራቅ

2. መርዳት:-በምንችለው ነገር ሁሉ ከምናውቀው መረጃን ማጋራት ጀምሮ አቅም የሌላቸውን ማገዝ በዚህ ግዜ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ ሰዎችን መርዳት ለሰጪው እርካታን፤ የራስ መተማመንንና የአዕምሮ እድገትን ይጨምራል።

3. የሰውነታችንን ጤና መጠበቅ:- ይህን ማድረግ ለሚሰማን ስሜትም ሆነ ለአእምሮአችን አስፈላጊ ነው። አመጋገባችንን ማስተካከል ፣ የምንተኛበትንና የምንነሳበት ሰዓት ተመሳሳይ ማድረግ፣የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

4. ከወዳጅ፣ ከዘመድ፣ከጓደኛ ጋር በስልክም ሆነ በተለያየ መገናኛ ዘዴዎች መገናኘት (እርቀታችን የአካል እንጅ እራሳችንን ማግለል የለብንም)

ይህ ወረርሽኝ የተፈጠረው በእኛ ላይ ብቻ ሳይሆን በምድር ላይ ባለ የሰው ዘር በመሆኑ ከመጨነቅ፣ ከመደንገጥ እና ከመሽበር ይልቅ ከወረርሽኙ ለመትረፍ ማድረግ ያለብን ጥንቃቄ ካደረግን የገጠምንን ችግር በአሽናፊነት እንወጣዋለን።

በእርግጠኝነት ነገ የተሻለ ቀን ይመጣል!
@tikvahethiopia
በኳታር ተጥለው የቆዩ እገዳዎች እየተነሱ ነው!

በኳታር መንግስት የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት ተጥሎ የቆዩ እገዳዎች ቀስ በቀስ እየተነሱ ነው። በዛሬው እለት የመጀመሪያ ደረጃ (First Phase) ውሳኔዎች ተግባራዊ መሆን ጀምረዋል።

በዚህም መሰረት፦

- ከጁምዓ ጸሎት በስተቀር በሌሎቹ ቀናት መስጊዶች በከፊል ክፍት መሆን ጀምረዋል።

- 20 ከመቶ የሚሆኑ የተለያዩ ተቋማት ሰራተኞች ወደ ስራ ገበታቸው ይመለሳሉ።

- ትልልቅ የገበያ አዳራሾች (Malls) እና ማዕከላት በከፊል (እስከ 30% አቅም) ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት (8:00 AM to 8:00 PM) ክፍት ይሆናሉ። ሆኖም እነዚህ ማዕከላት ቅዳሜ እና አርብ ዝግ ይሆናሉ።

- የግል የህክምና ማዕከላት (እስከ 40% አቅም ያላቸው) ክፍት ይሆናሉ።

- 8 የመዝናኛ ፓርኮች ጠዋት ከንጋቱ 10፡00 ሰዓት እስከ 3፡00 ሰዓት (4፡00 AM – 9:00 AM) እና ከሰዓት በኋላ ከ 10፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4፡00 ሰዓት (4:00 PM – 10:00 PM) ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ክፍት ይሆናሉ።

#EthiopianEmbassyDoha
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኳታር የምትኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ከዛሬ ጀምሮ የመጀመሪያው ደረጃ እገዳ መነሳቱን ሰምታችኃል። ሊወሰዱ የሚገባቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች በፍፁም እንዳትዘነጉ ለማስታወስ እንወዳለን ፦

- የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ (Mask) መጠቀም

- EHTERAZ የሞባይል መተግበሪያን በስልክዎ ላይ መጫን

- ከሰዎች ጋር ያለዎትን አካላዊ ርቀት መጠበቅ

- ከቤትዎ ሲወጡ እና ሲመለሱ እጅዎን በአግባቡ መታጠብ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia