TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም በሶማሊያ መዲና ሞቆዲሾ የተፈፀመውን የአሸባሪዎች ጥቃት አወገዙ፡፡ ዶ/ር ወርቅነህ ለሶማሊያ አቻቸው አህመድ ኢሴ አዋድ በላኩት መልዕክት በተሰነዘረው አሰቃቂ የሽብር ጥቃት 53 ንፁኃን ሶማሊያውያን ህይወታቸውን ማጣታቸውን እንዲሁም ከ 100 በላይ የመቁሰል አደጋ በመድረሱ የተሰማቸውን ጥለቅ #ሀዘን ገልጸዋል፡፡ ይህ አሰቃቂና ጭካኔ የተሞላበት የሽብር ጥቃት የፈጸሙ አካላት በጥብቅ አውግዘው ጥቀቱ አሸባሪነት ከሶማሊያም አልፎም የአካባቢው ስጋት መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም ለሶማሊያ ፌዴራል መንግስትና ህዝብ #መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

ምንጭ፦ ዋልታ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ🔝ቅዳሜ ዕለት አርሲ ነጌሌ በደረሰው #የመኪና_አደጋ ህይወታቸው ያለፈ ኢትዮጵያዊያን የቀብር ስነ ስርዓት በየ ትውልድ አካባቢያቸው ተፈፀመ። ዛሬ በሀዋሳ ከተማ በነበረ የቀበር ስነ ስርዓት እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የተገኘ ሲሆን በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ የቀድሞው የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ #ደሴ_ዳልኬን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ተገኝተው ነበር።

🔹ቅዳሜ ማለዳ በደረሰው አደጋ የ6 ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን አምስቱ ከሀዋሳ ተነስተው ወደ አዲስ አበባ ሲያቀኑ የነበሩ ናቸው። ጉዟቸውም ከሀገር ውጭ ቆይተው ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ የሲዳማ ሙሁራንን ለመቀበል ነበር።

በድጋሚ ለሟች ቤተሰብ፣ ወዳጆች በሙሉ TIKVAH-ETH #መፅናናትን ይመኛል!

©አስረስ(ሀዋሳ TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ልጇን አጣች‼️

ትላንት ምሽት አዲስ አበባ ደንበል አካባቢ በደረሰው #የመኪና_አደጋ የAAiT መምህር የሆኑት አቶ #ሳምሶን_ዋለልኝ ህይወታቸው አልፏል።

እንደወጣን እየቀረን ነው...

•TIKVAH-ETHIOPIA ለወዳጅ፤ ዘመዶች እንዲሁም ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ #መፅናናትን ይመኛል!

#ነብስ_ይማር!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር በደረሰው የአውሮላን አደጋ የተሰማቸውን #ሀዘን ገለፁ፡፡ ፕሬዚዳንቱ በደረሰው ጉዳት ከልብ ማዘናቸውን እና ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች #መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

በተጨማሪም...

የኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢህአዴግ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት፣ የአማራ ክልል መንግስት ፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና በውጭ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች በአዘደጋው ተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቦይንግ ኩባንያ በዛሬው እለት የተከሰከሰውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ መንስኤ ለማጣራት የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ #መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ ኩባንያ በደረሰው አደጋ የተሰማውን ሀዘን ገለፀ ሲሆን በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች #መፅናናትን ተመኝቷል፡፡ በሚቀርብለት ጥያቄ መሰረት #የአሜሪካን_ብሄራዊ_ትራንስፖርት የደህንነት ቦርድ አቅጣጫን ተከትሎ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ #የቴክኒክ_ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱን ነው ያስታወቀው፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መላው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት #በወገኖቻችን ሞት የተሰማንን #ጥልቅ_ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦች ለወዳጅ ዘመዶች በመላ #መፅናናትን እንመኛለን!!

ነብሳቸውን በገነት ያኑርልን!
@tsegabwolde @tikvahehiopia
መላው TIKVAH-ETHIOPIA ቤተሰብ አባላት በአርቲስት #ተዘራ_ለማ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን እየገለፁ ለመላው ቤተሰቦቹ፣ ወዳጆቹ እና ለስራ አጋሮቹ #መፅናናትን ይመኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ATTENTION

ሀገራችን ኢትዮጵያ በየዕለቱ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎችን ቁጥር መቁጠር ከጀመረች በርካታ ሳምንታት አልፈዋል።

የ3 ቀናት ሪፖርት ብቻ ብንመለከት በአጠቃላይ ሰላሳ (30) ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው አልፏል።

በዚህ አስከፊ በሽታ የምትወዷቸውን ሰዎች ከአጠገባችሁ ያጣችሁና የተነጠቃችሁ ወገኖቻችን በሙሉ #መፅናናትን እንመኝላችኃለን።

አሁንም ስልቹነታችን፣ መዘናጋትችን፣ ቸልተኝነታችን መፍትሄ ካላገኘ የነገ ህይወታችንን ያጨልማልና ከፍተኛ ጥንቃቄ እናድርግ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia