TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ETHIOPIA🇪🇹

" ልንከተለው የሚገባው ፖሊሲ አለመፍራት ነው ፤ ... አለመፍራት ሲባል ማንቀላፋት ማለት አይደለም " - አቶ መልስ ዜናዊ (የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ)

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት ፓርላማ ቀርበው ማብራሪያ ሲሰጡ በግብፅ ጉዳይ ተናግረው ነበር። ንግግራቸው የፓርላማ አባላትን ፈገግ ያሰኘ ደግሞም ጠንከር ያለ ነበር።

ምን ነበር ያሉት ?

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ፦

" ... የግብፅ መንግሥት #የጥፋት_መንገድ ለማንም እንደማይጠቅም ፤ ተከባብሮ እና ተጠቃቅሞ መኖር እንደሚቻል እንዲገነዘብ ማድረግ ነው ዋናው ስትራቴጂያችን።

አንዱ የግብፅ ስትራቴጂ ትልቅ ወታደር አስቀምጦ ማስፈራራት ነው ፤ ይሄን በተመለከተ ልንከተለው የሚገባው ፖሊሲ አለመፍራት ነው የሚሆነው ማለት ነው።

አለመፍራት ሲባል የቀረርቶ ጋጋታ ማስቀመጥ ማለት አይደለም፤ አለመፍራት ሲባል ማንቀላፋት ማለት አይደለም፤ አለመፍራት ሲባል በተጨባጭ በሀገራችን ላይ ሊቃጣ የሚችለው ወረራ ምን ያህል ነው ? ብሎ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መፈተሽ ማለት ነው።

ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ሲፈተሽ የግብፅ ወረራ አደጋ በኢትዮጵያ ላይ በጣም ትንሽ ነው። ዜሮ ነው ማለት ግን አይቻልም። ነገር ግን በጣም ትንሽ ነው።

ስለዚህም በዚህ በጣም ትንሽ በሆነ አደጋ ምክንያት እንቅልፍ የምናጣበት ምክንያት የለም። ይሄ ማለት ዜሮ ሳላልሆነ ያቺ ትንሿን አደጋ ለመቋቋም ተጨማሪ የአቅማችንን ያህል ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል።

ይሄን የምናደርገው ግብፅ ይወረናል ብለን ቡራ ከረዮ ለማለት አይደለም። አደጋው በጣም ትንሽ ነው መፍትሄው በጣም ቀላል ነው ፤ መፍትሄው ተደጋግፎ መኖር ነው።

ዋናው ስትራቴጂያችን ላይ እየተረባረብን ምናልባት 5በመቶ እድልም ቢሆን 5በመቶ ትኩረት ሰጥቶ ለዚህ ጉዳይ የመከላከል አቅማችንን መገንባት ነው። "

#ETHIOPIA
#GERD🇪🇹

@tikvahethiopia