TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጣልያን ከዛ ሁሉ መከራ እየወጣች ነው...

በጣልያን የአገር ውስጥ በረረራዎችና ጉዞዎች ተፈቅደዋል ፤ አገሪቱ ዓለም አቀፍ ድንበሮቿንም እየከፈተች ትገኛለች።

አገሪቱ እቀባዎችን በማቃለሉ ሂደት የመጨረሻውን ምዕራፍ በገባደደችበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ተስፋ የተሞላው ንግግር ማሰማታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

"አሁን ፈገግ ልንል፣ ልንደሰት ይገባናል፤ ከዚያ ሁሉ መከራ እየወጣን ስለሆነ…" ቀጥለውም "አሁን አገራችንን በኢኮኖሚ የመጠገን ሥራን እናፋፍማለን" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ይህ ወረርሽኝ (ኮቪድ-19) በአገራችን ሥር ነቀል መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት እንድንነሳ እድል ሰጥቶናል፤ አገራችንን በድጋሚ ነድፈን #ልንገነባት ይገባል" ሲሉ ተደምጠዋል።

ጠ/ሚ ጁሴፔ በዚህ ተስፋን በሰነቀው ንግግራቸው ማብቂያ ሕዝባቸው በፍጹም #እንዳይዘናጋ መክረዋል። በተለይም ማኅበራዊ ርቀትን መጠበቅና ጭምብል ማጥለቅ መዘንጋት የለበትም ብለዋል። እነዚህን ቸል ማለት ዋጋ ያስከፍላል ሲሉ አስምረውበታል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia