TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የWFP ሪፖርት ምን ይላል?

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሰሜን ኢትዮጵያ የከፋ ረሃብ ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቋል።

#ትግራይ

በትግራይ ክልል ውስጥ 40 በመቶ የሚጠጉ ሰዎች በከፍተኛ የምግብ እጥረት ውስጥ ናቸው።

በትግራይ ክልል በተደረገው አስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዋስትና ግምገማ 83% የሚሆነው ሕዝብ የምግብ ዋስትና ችግር አጋጥሞታል።

በዚህ ሳቢያ የተለያዩ ቤተሰቦች ያላቸውን ምግብ ሁሉ አሟጠው በመጨረሳቸው ጥራጥሬ ብቻ መመገብና የሚመገቡትን የምግብ መጠን ለመቀነስ ተገደዋል።

ከተመጣጣነ ምግብ አንጻር ግምገማው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ትግራይ ውስጥ ከሚገኙ ልጆች መካከል 13% እና ከነፍሰጡር ሴቶች ግማሽ ያህሉ እንዲሁም ጡት የሚያጠቡ እናቶች ለተለያዩ ችግሮች በሚያጋልጥ ሁኔታ የተመጣጠነ ምግብ ችግር ገጥሟቸዋል።

#አማራ

በአማራ ክልል በቅርቡ በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ባለፉት 5 ወራት የረሃብ ሁኔታ ከእጥፍ በላይ ጨምሯል።

በዚህ ሳቢያ ከ5 ዓመት በታች ከሆኑ ህጻናት መካከል 14%ና አንድ ሦስተኛ የሚሆኑ ነፍሰጡርና የሚያጠቡ እናቶች የተመጣጣነ ምግብ ችግር አጋጥሟቸዋል።

#አፋር

በአፋር ክልል በጦርነት በተከሰቱ መፈናቀሎች ምክንያት ረሃብና የተመጣጠነ ምግብ ችግር መጠን ከፍ ብሏል።

በቅርቡ የተሰበሰበ መረጃ በክልሉ ከ5 ዓመት በታች ከሆኑ ህጻናት መካከል 28 በመቶው የተመጣጠነ ምግብ ችግር አጋጥሟቸዋል።

#ሰሜንኢትዮጵያ- WFP በተያዘው የፈረንጆች ዓመት በሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ከ9 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች እርዳታ ማቅረብ ያስፈልጋል ብሏል።

በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ ኃይሎች የእርዳታ አቅርቦት እንዲጓጓዝ እንዲፈቅዱ ጠይቋል፥።

ሙሉ ሪፖርት www.wfp.org/news/severe-hunger-tightens-grip-northern-ethiopia?s=09

@tikvahethiopia