TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላይ መኪናቸው ውስጥ ባልታወቀ ምክንያት ህይወታቸው አልፎ ከተገኘ ሁለት ሳምንታት አለፉ።

የኢንጂነሩ ሞት በበርካቶች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤን የፈጠረ ነበር። BBC ያነጋገራቸው የኢንጂነር ስመኘው ቤተሰብ አባላትም መሪር ሃዘን ውስጥ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢንጂነር ስመኘው ባለቤት የወ/ሮ ዕሙን ጌታሁን ታናሽ ወንድም የሆነው አካሉ ጌታሁን ''ሃዘናችን እጅግ ከባድ ቢሆንም እየበረታን ነው። ከቀብሩ ጀምሮ መንግሥት እየደገፈን ነው። ምንም ያወጣነው ወጪ የለም" ብሏል። አካሉ ጨምሮም "የስመኘው የመጀመሪያ ልጅ የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዶ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንዲመደብ እየተባበሩን ነው'' በማለት ከመንግሥት የተደረገላቸውን ድጋፍ የገለጸ ሲሆን ''ገዳዩን ለፍርድ ለማቅረብ ግን ፖሊስ በምንፈልገው #ፍጥነት እየሄደልን አይደለም'' ሲል
በምረመራው ውጤት #መዘግየት ቤተሰቡ ቅር እንደተሰኘ ይናገራል።

አካሉ ''እሱ ከተገደለ 15 ቀናት አልፈዋል። ከፖሊሶቹ ጋር በየጊዜው እንገናኛለን ይሁን እንጂ እስካሁን ግልጽፅ ያለ ነገር አልነገሩንም። ከሆስፒታል ስለተሰጣቸው መረጃም በግልጽ የነገሩን ነገር የለም'' ይላል።

የኢንጂነር ስመኘው ባለቤት የወ/ሮ ዕሙን ጌታሁን እናት የሆኑት ወ/ሮ መንበረ መኮንን ደግሞ በሃዘናቸው ወቅት ከጎናቸው በመሆን ያጽናኗቸውን ሁሉ አመስግነው ''ስለ ስመኘው እና ባለቤቱ የሚወራው ነገር ስህተት ነው። እኔ እስከማውቀው ድረስ ባል እና ሚስት በፍቅር ነበር የሚኖሩት። ተፋተዋል እየተባለ የሚወራው #ሃሰት ነው። እንዲህ አይነቱ ወሬ እያስጨነቀን ነው'' በማለት በማህበራዊ ሚዲያ የሚወራው ስህተት መሆኑን ይናገራሉ።

አካሉም ታላቅ እህቱ ለትምህርት ከሃገር ውጪ መሆኗን አስታውሶ ''እንደውም ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርጋ ልትመጣ ነበር። #መምጣቷም አይቀርም'' ብሏል።

የቤተሰብ አባላቱ በሃዘናችን ወቅት የኢትዮጵያ ህዝብ አጽናንቶናል። መንግሥትም ከጎናችን ሆኖ እየደገፈን ነው ለዚህም ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል።

ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ህይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው እንደሆነ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ዘይኑ ጀማል ገልፀው ነበር።

ዝርዝር የአሟሟታቸውን ሁኔታ በተመለከተ ፖሊስ ምርመራ እያካሄድኩ ነው ማለቱም ይታወሳል።

ኢንጂነር ስመኘው ህይወታቸው ከማለፉ ከአንድ ቀን በፊት ቢቢሲ አማርኛ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን አስመልክቶ ባነጋገርናቸው ወቅት ፕሮጀክቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለ ገልጸው ነበር።

ኢንጂነር ስመኘው ግድቡ የደረሰበትን ደረጃ የBBC ጋዜጠኞች በአካል ተገኘተው እንዲመለከቱ ጋብዘው ነበር።

©BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጅግጅጋ⬇️

በጅግጅጋ ከተማ የሚገኙ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ከዛሬ ጀምሮ ወደ መደበኛ አገልግሎት እንዲገቡ ተጠየቀ።

በሶማሌ ክልል በተለይም በጅግጅጋ ከተማ ከሃምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ከተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ በኋላ ቅዳሜ እለት የሰላም ኮንፈረንስ ተካሂዷል።

በሰላም ኮንፈረንሱ ላይ የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪ ተወካዮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የጎሳ መሪዎች የተሳተፉ ሲሆን፥ ድርጊቱ #በተደራጀ መንገድ በመዋቅር ተመርቶ የተፈፀመ መሆኑን ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል።

#ድርጊቱ በክልሉ መንግስት አመራሮች የተመራና ክልሉን ለመበጥበጥ የተፈጸመ መሆኑንም አንስተዋል።

በኢፌዴሬ መከላከያ ሚኒስቴር የመረጃ ሃላፊ ሌተናል ጀኔራል ሃሰን ኢብራሂም ለተፈጸመው ችግር የክልሉ አመራሮች ተጠያቂ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ለጥቂት ሰዎች #ስልጣን ተብሎ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ መደፍረስ እንደሌለበት ያነሱት ሃላፊው፥ መከላከያ ሰራዊት ወደ ክልሉ ሰላም ለማስከበር ብቻ መግባቱንም ነው የተናገሩት።

ከዚህ ውጭ ግን ከሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ጋር ሊዋጋ ነው በሚል የሚናፈሰው ወሬ #ሃሰት መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የደቡብ ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል በላይ ስዩም በበኩላቸው የኢፌዴሪ መከላከያ እና የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል በሰሩት ስራ አሁን ላይ አንጻራዊ ሰላም መታየቱን አንስተዋል።

ከመከላከያ ሰራዊት፣ ከክልሉ ልዩ ሃይልና ከክልሉን ፖሊስ የተውጣጣ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን በጥቀስ።

በጅግጅጋ ከተማ ሰላም በመታየቱ ሁሉም ሁሉም የገንዘብ እና የንግድ ተቋማት ወደ ስራ እንዲገቡም ተጠይቋል።

ከዚህ ባለፈም የሃገር ሽማግሌዎች ስለ ሰላም እንዲሰብኩና ወጣቶችም ከጥፋት ድርጊት በመታቀብ ለሰላም ዘብ እንዲቆሙም ተጠይቋል።

©FBC
@tseagabwolde @tikvahethiopia
#Free_Nazrawit_Abera!!

መንግስት በቻይና መንግስት እፅ በማዘዋወር ተጠርጥራ እስር ላይ የምትገኘውን ናዝራዊት አበራን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው ከfbc ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ መንግስት #ጓንዡ_ግዛት በሚገኘው ማረሚያ ቤት የምትገኘውን የናዝራዊት አበራን ጉዳይ #በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ተናግረዋል።

በስፍራው በሚገኘው የኢፌዴሪ ቆንስላ ፅህፈት ቤት ሰራተኞችም ናዝራዊት በምትገኝበት ማረሚያ ቤት ሶስት ጊዜ በመሄድ ያለችበትን ሁኔታ ተመልክተዋል ነው ያሉት።

መንግስትም ዜጋውን የመከታተል መብቱን ተጠቅሞ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ጠቅሰው፥ ተጠርጣሪዋን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ እየተናፈሱ ያሉ ወሬዎች #ሃሰት መሆናቸውንም ነው የተናገሩት።

በተለይም ከተጠረጠረችበት ጉዳይ ጋር በተያያዘ #የሞት_ፍርድ_ተፈርዶባታል በሚል እየተናፈሰ ያለው ወሬ ሃሰት መሆኑንም ገልጸዋል።

ተጠርጣሪዋ አሁን ላይ በማረሚያ ቤት የምትገኝ ሲሆን አቃቤ ህግም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ክሱን ካቀረበ በኋላ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት አምርቶ #እንደሚወሰንም አስረድተዋል።

መንግስት አሁን ላይ እንደ ዜጋ መጠየቅ የሚችለውን እያደረገ ሲሆን፥ ትክክለኛ ፍርድ እንድታገኝ ክትትል ይደረጋልም ነው ያሉት።

ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tijvahethiopia
"ፍፁም #ሃሰት ነው" አቶ አሰመኸኝ

የአማራ ክልል የኮሚኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰመኸኝ አስረስ በቀጣይ ሳምንት አዳዲስ አመራሮች ምደባ ይካሄዳል ብለዋል። የሚሟሉት የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ዝርዝር ጉዳይ በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆንም አስታውቀዋል፡፡ ክልሉን #ፌደራል_መንግስት እያስተዳደረው አይደለም ወይ? ተብለው ተጠይቀው "ፍፁም ሐሰት ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

Via #DW
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MoH

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ባልደረባ የነበሩት አቶ ሙከሚል አብደላ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው አሳውቋል።

የአቶ ሙከሚል አብደላ ህልፈተ ህይወት በኮሮና ቫይረስ እንደሆነ ተደርጎ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨው መረጃ #ሃሰት መሆኑንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል፡፡

አቶ ሙከሚል አብደላ በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ ከኮቪድ-19 በሽታ #ነጻ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia