TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MetekelZone

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ቡለንና ድባጤ ወረዳ ነዋሪዎች ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሱ እንደሆነ አሳውቀዋል።

ከባለፈው ረቡዕ አንስቶ በቡለን ወረዳ 2 ቀበሌዎች ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ከ4 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።

ከትላንት በስቲያ በቆንጢ ቀበሌ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 2 ሰዎች ሲገደሉ 3 ሰዎች ቆስለዋል፤ በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል።

ታጣቂዎቹ በተለያየ ስፍራ ጥቃት ፈፅመው ከስፍራው እንደሚሸሹ ነዋሪዎች ከዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።

አንድ የቡለን ወረዳ ነዋሪ በስልክ ለዶቼ ቨለ ሲናገር እንደተደመጠው ፥ ከሶስት ቀን በፊት ከፌዴራል ፣ ከክልል እና ከዞን አመራሮች በተሰጠው አቅጣጫ ህብረተሰቡ ወደ ሰብል መሰብሰብ ቢመለስም ጥቃት ተፈፅሞበታል።

በጥቃቱ ባል እና ሚስት ፣ ወጣት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ህይወታቸውን አጥተዋል፤ ከ4-8 ሰዎች ቆስላው ሆስፒታል ይገኛሉ።

'ዶሽ' በተባለ የቡለን ቀበሌ ሰሞኑ የአካባቢው የፀጥታ ኃይል በመምሰል እና የደንብ ልብስ በመልበስ ጥቃት ተፈፅሟል። በዚህም የሰዎች ህይወት ማለፉን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በቡለን በተፈፀሙት ጥቃቶች ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት ስብሰባ ላይ ነን በሚል ለሬድዮ ጣቢያው ምላሽ አልሰጡም።

የፀጥታ ኃይል እርምጃ ለመውሰድ ሲንቀሳቀስም ታጣቂዎቹ ወደ ጫካ እንደሚሸሹ ነው የተነገረው።

የዞኑ ኮማንድ ፖስት በትላንትናው ዕለት ባወጣው መረጃ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ባልተወጡ 66 አመራሮች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጿል፤ ከነዚህ መካከል የፖሊስ አባላት ይገኙበታል።

በወታደራዊ አሰሳም 50 ሰዎች መማረካቸውን 43 የሚሆኑ እጅ መስጠታቸውን ኮማንድ ፖስቱ መግለፁን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Metekel

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን "የጸጥታ ችግር" ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት የተረጋገጠ ከፍተኛና በየደረጃው ያሉ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋል እንደጀመሩ የክልሉ መንግስት ዛሬ ምሽት ገልጿል።

እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር የዋሉ ፦

• አቶ ቶማስ ኩዊ ፡- የኢፌዴሪ ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ

• አቶ አድጎ አምሳያ፡- የቀድሞው የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር

• አቶ ሽፈራው ጨሊቦ፡-የቀድሞ የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር

• አቶ ባንዲንግ ማራ፡- የመተከል ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ

• አረጋ ባልቢድ፡- የመተከል ዞን የቀድሞ አመራር የነበሩ

#BenishangulGumuz #MetekelZone

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT