TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በሱማሊያ በአንድ ቀን 51 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 51 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 722 ደርሷል።

በሌላ በኩል አስር (10) ተጨማሪ ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 44 ደርሷል።

በተጨማሪ ባለፉት 24 ሰዓት የአንድ (1) ሰው ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ሰላሳ ሁለት (32) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት የ174 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል (ከመጋቢት 1 በኃላ የተመዘገበ ዝቅተኛ ቁጥር ነው) በሀገሪቱ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 28,884 ደርሷል።

- በጣልያን ያገገሙ ሰዎች 80,000 ደርሰዋል።

- በኳታር ተጨማሪ 679 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 15,551 ደርሷል።

- በሩሲያ በአንድ ቀን 10,633 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ 58 ሰዎች ሞተዋል።

- በኢራን ባለፉት 24 ውስጥ 47 ሰዎች ሞተዋል (ከየካቲት 30 በኃላ የተመዘገበ ዝቅተኛው ቁጥር ነው) እንዲሁም 976 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በደቡብ ኮሪያ ባለፉት 24 ሰዓት 13 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አስሩ ከውጭ የገቡ ናቸው።

- በUAE 564 ሰዎች በአንድ ቀን በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። 7 ሰዎችም ሞተዋል።

- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት የ315 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል። 4,339 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በሳዑዲ አረቢያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1,552 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 8 ሰዎች ሞተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጎረቤታችን ሱዳን እንዲህ ነው እየሆነ ያለው...

በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ፦

መጋቢት 9/2012 - 1 ሰው
መጋቢት 15/2012 - 1 ሰው
መጋቢት 19/2012 - 2 ሰዎች
መጋቢት 20/2012 - 1 ሰው
መጋቢት 21/2012 - 1 ሰው
መጋቢት 22/2012 - 1 ሰው
መጋቢት 24/2012 - 1 ሰው
መጋቢት 25/2012 - 2 ሰዎች
መጋቢት 27/2012 - 2 ሰዎች
መጋቢት 29/2012 - 2 ሰዎች

(ከላይ ያሉትን መረጃዎች የወሰድነው ከወርልዶሜትርስ ድረገፅ ነው፤ ከታች ደግሞ ያስቀመጥናቸው ቁጥራዊ መረጃዎች ከሱዳን ጤና ሚኒስቴር ያገኘናቸው ናቸው)

ሚያዚያ 1/2012 - 1 ሰው
ሚያዚያ 2/2012 - 2 ሰዎች
ሚያዚያ 3/2012 - 2 ሰዎች
ሚያዚያ 5/2012 - 10 ሰዎች
ሚያዚያ 6/2012 - 2 ሰዎች
ሚያዚያ 7/2012 - 1 ሰው
ሚያዚያ 10/2012 - 30 ሰዎች
ሚያዚያ 12/2012 - 26 ሰዎች
ሚያዚያ 13/2012 - 15 ሰዎች
ሚያዚያ 14/2012 - 33 ሰዎች
ሚያዚያ 15/2012 - 22 ሰዎች
ሚያዚያ 16/2012 - 12 ሰዎች
ሚያዚያ 17/2012 - 39 ሰዎች
ሚያዚያ 18/2012 - 24 ሰዎች
ሚያዚያ 19/2012 - 38 ሰዎች
ሚያዚያ 20/2012 - 43 ሰዎች
ሚያዚያ 21/2012 - 57 ሰዎች
ሚያዚያ 22/2012 - 67 ሰዎች
ሚያዚያ 23/2012 - 91 ሰዎች
ሚያዚያ 24/2012 - 59 ሰዎች

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመገመት የሚከብድ ፤ የለም ሲባል የሚኖር ፤ ቀንሷል ሲባል በአንዴ ሳይገመት የሚያሻቅብ ነውና መጠንቀቃችን፤ የጤና ባለሞያዎችን ምክር መስማታችን ከከፋው ነገር ይታደገናል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በፈረንሳይ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የ135 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል (ከ6 ሳምንታት በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ነው)

- በአሜሪካ ሟቾች ቁጥር ከ68,000 በላይ ሆኗል፤ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከ1.1 ሚልዮን መብለጣቸው ተገልጿል።

- በደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 6,783 ደርሰዋል፤ በአንድ ቀን 447 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። የሟቾች ቁጥርም በስምንት ጨምሮ 131 ደርሷል።

- በግብፅ ባለፉት 24 ሰዓት 272 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 6,465 ደርሰዋል። በሌላ በኩል 14 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 429 ደርሷል።

- በሩዋንዳ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 259 ደርሰዋል። እስካሁን ሞት አልተመዘገበም።

- በAfricaCDC መረጃ መሰረት እስካሁን በአፍሪካ ደረጃ 1,761 ሰዎች ሞተዋል፤ 43,060 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ተይዘዋል ፤ 14,343 አገግመዋል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ የሟቾች ቁጥር ከ247,335 ደርሷል፤ 1,137,349 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፤ 3,546,758 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#COVID19

የኢትዮጵያና የአጎራባች ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦

- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,112፣ ሞት 2፣ ያገገሙ 686

- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 465፣ ሞት 24፣ ያገገሙ 167

- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 722፣ ሞት 32፣ ያገገሙ 44

- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 592፣ ሞት 41፣ ያገገሙ 52

- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 135፣ ሞት 3፣ ያገገሙ 75

- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 46፣ ሞት 0፣ ያገገሙ 0

- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 26

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መዓድ ማጋራት!

ወገን ለወገን ደራሽ ብቻ ሳይሆን አዳኝ የሆነበት እውነታ ላይ እንገኛለን። ነገ ማየት የኔ፣ ያንተ፣ ያንቺ፣ የኛ የሁል ጊዜ ህልም ነው። እውን ለማድረግ ደግሞ ከፈጣሪ በታች ከመቼውም በላይ የሁላችንም ትብብርና እገዛ ይሻል!

ነገ ያላንቺ ላያምር፤ ነገ ያለሱ ላይሰምር፤ ነገ ያለኛ ባዶ ሊሆን እያስፈራራን ባለበት ወቅት በአብሮነት አብረን ተባብረን መሻገር ግድ ይለናል።

ወገን ሆይ ያለንን ተቋድሰን አብረን ይህን መከራ ልንወጣ እንታጠቅ ፤ የሌለውን ጎረቤት ከማዕዳችን አካፍለን ፤ ጎዳና ካሉት አንድ ወንድም ወይም እህት ወደቤት አስገብተን ወገኖቻችንን ታድገን እራሳችንን እንታደግ!

ዛሬ ላይ ቆመን ነጋችንን የሚገነባ ኃይል የጋራነት እሴቶቻችን የሚያጠናክር ጉልበት እንፍጠር! ነገን ተቋድሰን እናስውባት!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱዳን ተጨማሪ 86 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸዉ ተረጋገጠ!

(በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ)

የሱዳን ጤና ሚንስቴር ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ ተጨማሪ 86 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ሲያዙ 9 ሰዎች ማገገማቸዉን ገልጸዋል።

በዚህ መሰረት በአጠቃላይ የቫይረሱ ስርጭት በሀገሪቱ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 678 መድረሱንና ከዚህ ዉስጥ 41 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 61 ሰዎች ማገገማቸዉን አስታዉቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ሱዳን ተጨማሪ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

በደቡብ ሱዳን የ138 የላብራቶሪ ምርመራ ውጤት ይፋ ተደርጓል ፤ ከእነዚህ መካከል ተጨማሪ ሶስት (3) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 49 ደርሷል። በሀገሪቱ እስካሁን ያገገመም ሆነ የሞተ ሰው የለም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

'ያስካይ' የተሰኘ ሃገር በቀል ኩባንያ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ (ቬንትሌተር) መስራቱን አስታውቋል።

የያስካይ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሳሙዔል ይትባረክ እንደገለጹት መሳሪያው ከውጭ ሃገር የሚገባውን የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ ሙሉ በሙሉ ከመተካቱም ባሻገር በተሻለ ደረጃ መጠቀም የሚያስችል ነው ብለዋል።

የመተንፈሻ መሳሪያው በይዘቱ አነስ ተደርጎ የተሰራ ሲሆን በዋጋ ደረጃም ከውጭ ከሚመጣው መሳሪያ በ90 ከመቶ ቅናሽ እንዳለውም ስራ አስፈጻሚው ጠቁመዋል፡፡

የዘርፉ ሐኪሞች እንዲሁም መካኒካል መሃንዲሶች ለ20 ቀናት ባደረጉት ጥረት መሳሪያውን ለመስራት እንደተቻለ አቶ ሳሙዔል ተናግረዋል፡፡ ስራው እንዲሳካ ከጤና ሚኒስቴር እና ከሚመለከታቸው አካላት ማበረታቻ እንደተደረገላቸውም ተገልጿል፡፡

ምንጭ፦ ዋልታ ቴሌቪዥን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 5 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,758 ላቦራቶሪ ምርመራ አምስት (5) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መቶ አርባ (140) ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከፑንትላንድ የተመለሰና በጅግጅጋ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 2 - የ23 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከፑንትላንድ የተመለሰና በጅግጅጋ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 3 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከፑንትላንድ የተመለሰና በጅግጅጋ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 4 - የ17 ዓመት ኢትዮጵያዊ የባህር ዳር ነዋሪ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #ያለው

ታማሚ 5 - የ19 ዓመት ስዊድናዊ (ትውልደ ኢትዮጵያዊ) ፤ ከስዊድን የተመለሰና በአዲስ አበባ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 24,088
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 1,758
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 5
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 60
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አዲስ ያገገሙ - 0
• አጠቃላይ ያገገሙ - 75
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 140

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የውጭ አገራት የጉዞ ታሪክ ሳይኖራቸው የኮሮና ቫይረስ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር #እየጨመረ መሆኑ ተጠቆመ!

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ #ለኢዜአ እንደተናገሩት ፤ ኅብረተሰቡ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር "አነስተኛ ነው" በማለት እየተዘናጋ ነው።

የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸውና ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ሳይኖራቸው በቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ መዘናጋት አይገባም ብለዋል።

በጎረቤት አገራት በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ሆኑንም ገልጸው ይህም ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል።

ሳይንሳዊ ምርምሮችም የቫይረሱ ስርጭት ሊጨምር እንደሚችል እያሳዩ መሆኑን ጠቁመው ኅብረተሰቡ ሳይዘናጋ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ምክራቸውን ለግሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrMercyMwangangi

በኬንያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 490 ደረሱ!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1,012 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ተጨማሪ ሀያ አምስት (25) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ዛሬ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው ግለሰቦች አስራ አምስቱ (15) ከናይሮቢ አስሩ (10) ደግሞ ከሞንባሳ ናቸው።

በአጠቃላይ በኬንያ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 490 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 1,116 ደርሰዋል!

የጅቡቲ ጤና ሚኒስቴር ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው ሪፖርት 366 የላብራቶሪ ምርምራ ተደርጎ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አሳውቋል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 1,116 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል ከኮቪድ-19 የሚያገግሙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። በትላንትናው ዕለት 27 ሰዎች ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 713 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱማሊያ ተጨማሪ 34 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 34 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 756 ደርሷል።

በሌላ በኩል አስራ ሰባት (17) ተጨማሪ ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 61 ደርሷል።

በተጨማሪ ባለፉት 24 ሰዓት የሶስት (3) ሰው ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ሰላሳ አምስት (35) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ሱዳን የመጀመሪያዎቹ ሁለት (2) ታማሚዎች ከኮቪድ-19 አገገሙ!

የደቡብ ሱዳን ጤና ሚኒስቴርን ጠቅሶ አይ ሬድዮ ባሰራጨው መረጃ ከኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች መካከል የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሰዎች አገግመዋል።

ከበሽታው እንዳገገሙ የተገለፀው በህክምና ክትትል ላይ የነበሩት 'ታማሚ 3' እና 'ታማሚ 4' ናቸው ተብሏል።

በአሁን ሰዓት በደቡብ ሱዳን በአጠቃላይ አርባ (40) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረገጥ፤ ሁለት (2) ሰዎች አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- የሮም 'ቻምፒኖ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ' ሊከፈት እንደሆነ ተገልጿል።

- በጣልያን የሟቾች ቁጥር ከትላንትናው ጨምሯል፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ195 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል። 1,221 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ69,000 በላይ ሆኗል።

- በኳታር 640 ሰዎች በአንድ ቀን በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 16,191 ደርሷል።

- በጃፓን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እስከ ግንቦት 23 ተራዝሟል።

- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት24 ሰዓት የ288 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል (ከየካቲት ወር መጨረሻ በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው ቁጥር ነው) አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 28,734 ደርሷል።

- በቱርክ የሟቾች ቁጥር 3,461 ደርሷል፤ ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ የ64 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

- በፈረንሳይ የሟቾች ቁጥር ከትላንት ጨምሯል፤ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 306 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ የሟቾች ቁጥር 250,099 ደርሷል፤ 1,170,448 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፤ 3,610,189 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#COVID_ORGANIC ማዳጋስካር ለኮሮና ቫይረስ መፍትሄ ነው ብላ COV/COVID ORGANIC ተሰኘ ባህላዊ መድሃኒት አስተዋውቃለች! በተለያዩ ሀገራት ሳይንቲስቶች ለኮሮና ቫይረስ በሽታ መድሃኒት ለማግኘት ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ። የክትባት ሙከራዎች እየተካሄዱ እንዳለ ይታወቃል። ሀገራችን ኢትዮጵያም ለዚህ ዓለምን ለፈተነ ወረርሽኝ መፍትሄ ይሆናል ፣ ሰዎችንም ከጭንቀት ይገላግላል ያለችውን መፍትሄ…
#COVID_ORGANICS

በማዳጋስካሩ ፕሬዚደንት አንድሪ ራጆሊና የተዋወቀው እና 'የኮሮና ቫይረስ ፈውስ ነው' ለተባለው ባህላዊ መድሃኒት ከሰሃራ በታች ያሉ አገራት ያላቸው ፍላጎት እየጨመረ ነው፡፡

'ባህላዊ መድሃኒቱ' ከኮቪድ-19 እንደሚያድን የሚያረጋግጥ ሳይንሳዊ መረጃ እንደሌለ ቢነገርም ፍላጎታቸው አልተገታም' ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

'መድሃኒቱን' ካዘዙት መካከልም መድሃኒቱን ለማምጣት ወደ ደሴቷ አገር አውሮፕላን የላኩት የታንዛኒያው ፕሬዚደንት ጆን ማጉፋሊ ይገኙበታል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ኮንጎ ብራዛቪል ፣ ኮንጎ ፣ ጋቦን እና ኮሞሮስ መድሃኒቱን ወደ አገራቸው የማስገባት ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡ ኢኳቶሪያን ጊኒ እና ጊኒ ቢሳዎም የተወሰኑ መድሃኒቶችን ለማምጣት አውሮፕላን ልከዋል - #BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AndryRajoelina 

የማዳጋስካሩ ፕሬዝዳንት ራጆሊና ሀገራቸው ባዘጋጀችው 'ፈዋሽ ነው' በተባለለት መድሃኒት ዙሪያ ከአሜሪካውያን ተመራማሪዎች ጋር መነጋገራቸውን ገልፀዋል።

ፕሬዝዳንቱ ፈዋሽ ነው ብለው ያዘጋጁት መጠጥ ከዓለም ጤና ድርጅት እውቅና እንዲያገኝ እየሰሩ መሆኑን ጨምረው አስታውቀዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ኮቪድ-19 ለመከላከል ተብለው በግል የሚወሰዱ መድሃኒቶችን እንደማይመክር ለቢቢሲ በላከው ደብዳቤ ገልጿል።

ተጨማሪ መረጃ ፦

ባለፉት 24 ሰዓት በማዳጋስካር 161 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ከቫይረሱ #ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል።

በማዳጋስካር እስካሁን በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 151 ሲሆኑ 99 ሰዎች አገግመዋል (ዛሬ 1 ሰው አገግሟል) ፤ በአሁን ሰዓት የህክምና ክትትል እያደረጉ ያሉ 52 ሰዎች ናቸው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ ፣ የማዳጋስካር ጤና ሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ADDISABABA

የፐብሊክ ሰርቪስ ድርጅት ከረቡዕ ጀምሮ ተሳፋሪዎች የአፍ መሸፈኛ ጭንብል በአስገዳጅነት እንዲጠቀሙ ሊደርግ መሆኑን አስታውቋል።

ከረቡዕ ጀምሮ የአፍ መሸፈኛ ጭምብል የማይጠቀሙ ተሳፋሪዎችን እንደማይጭንም ገልጿል።

በተጨማሪ የትራንስፖርት እጥረትን ለመፍታት የመጫን አቅምን ከአስገዳጅ የአፍ መሸፈኛ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ወደ 43 የሚያድግ ይሆናል ተብሏል - #FBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia