TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Turkey ቱርክ ለኢትዮጵያ 1 ነጥብ 7 ቶን መጠን ያለው የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባሳለፍነው ሳምንት ከቱርኩ ፕሬዘዳንት ረጂብ ጣይብ ኤርዶሃን ጋር በስልክ መወያየታቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በውይይታቸው ወቅት በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ቱርክ ድጋፍ እንድታደርግ ጠይቀው ፕሬዘዳንቱ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸው…
#FilsanAbdullahi #YaprakAlp

ዛሬ የቱርክ መንግስት ያደረገው ድጋፍ በዋነኝነት ለኮቪድ-19 በሽታ መከላከያ ተግባር የሚውሉ 280 ካርቶን ወይም 1700 ኪሎ ግራም የሆኑ የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች፣ የኬሚካል ማጽጃዎች፣ የማጽጃ አልባሳት እና ሌሎችም ቁሳቁሶች ይገኙበታል፡፡

የቁሳቁስ ርክክቡ በተካሄደበት ወቅት በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ሚስትረስ ያፕላክ አልፕ በሁለቱ አገራት መካከል ባህል፣ በታሪክ እና በዲፕሎማሲው መስክ የቆየ ወዳጅነት መኖሩን አስታውሰው በኢኮኖሚው ረገድም የአገሪቱ ኢንቬስተሮች በኢትዮጵያ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ እያፈሰሱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት፤ የቱርክ መንግስት በዚህ አስከፊ ወቅት ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን በመሆን ላደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ አመስግነው ይህም በአገራት መካከል የጠበቀ ግንኙነት ለመኖሩ ትልቅ ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም ድጋፉ ወረርሽኙን ለመከላከል እንደ አገር እየተደረገ ላለው ርብርብም የበኩሉን እገዛ እንደሚያደረግ ገልጸዋል፡፡

(የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FilsanAbdullahi

"የማህበራዊ ሃላፊነት በሁሉም ተቋማት እንዲጎለብት በማድረግ ፤ እንዲሁም ባለሃብቶች መሰል ድጋፎችን ማድረግ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ዋነኛ ሃላፊነት አድርገው መንቀሳቀሰስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ህብረተሰቡ በግለሰብ ደረጃ ጎሮቤት ጎሮቤቱን በማስታወስና በመደገፍ የቆየ እሴቱን ማጎልበት ይኖርበታል፡፡ ይህን ማድርግ ከቻልን ይህ አስቸጋሪ ወቅት ማንንም የከፋ ችግር ላይ ሳይጥል ልንሻገረው እንችላለን፡፡ የተባበሩት አረብ ሃገራት ኢሚሬትና አስሊ መንዲ ሬስቶራንት ላደረጉልን ድጋፋና ቀና ምላሽ እናመሰግናለን!" - ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia