TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#COVID_ORGANIC ማዳጋስካር ለኮሮና ቫይረስ መፍትሄ ነው ብላ COV/COVID ORGANIC ተሰኘ ባህላዊ መድሃኒት አስተዋውቃለች! በተለያዩ ሀገራት ሳይንቲስቶች ለኮሮና ቫይረስ በሽታ መድሃኒት ለማግኘት ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ። የክትባት ሙከራዎች እየተካሄዱ እንዳለ ይታወቃል። ሀገራችን ኢትዮጵያም ለዚህ ዓለምን ለፈተነ ወረርሽኝ መፍትሄ ይሆናል ፣ ሰዎችንም ከጭንቀት ይገላግላል ያለችውን መፍትሄ…
#MADAGASCAR

የዓለም ጤና ድርጅት ለኮቪድ-19 ከወደ ማዳጋስካር ተገኘ የተባለው መድኃኒት ማስረጃ የሌለው ነው ብሏል።

የማዳጋስካሩ ፕሬዝደንት ኮሮናቫይረስን 'የሚፈውስ' መድኃኒት ከቅጠላ ቅጠሎች ሠርተናል ማለታቸው ይታወሳል።

ይሁን እንጂ የሃገሪቱ ሜዲካል አካዳሚም ቢሆን ፕሬዝደንት አንድሪ ራጆሊና ያስተዋወቁት 'መድኃኒት' ፈዋሽ ስለመሆኑ #ማስረጃ የለም ብሏል።

ሰዎች ላይ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት በሳይንሳዊ መንገድ አልተመረመረም ሲል አካዳሚው ግኝቱን አጣጥሏል። አርቲሚሲያ ከተባለው ተክል የተሠራው ፈሳሽ መድኃኒት አቅም ለሌላቸው በነፃ ይሰጣል ተብሏል።

የፕሬዝንቱ ፅ/ቤት ኃላፊ ለቢቢሲ እንደተናገሩት መድኃኒቱ በ20 ሰዎች ላይ ለሶስት ሳምንታት ከተሞከረ በኋላ በጠርሙስ ታሽጎ ለገበያ ቀርቧል። የ45 ዓመቱ ፕሬዝደንት ፈሳሹን የጠጡ ሁለት ሰዎች ከኮሮና ድነዋል ይላሉ።

የዓለም ጤና ድርጅት ማንኛውም ዓይነት ሳንይንሳዊ ድጋፍ ያላገኘ መድኃኒት ኮሮናቫይረስን ለማከም ጥቅም ላይ መዋል የለበትም ብሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MADAGASCAR

ከደቂቃዎች በፊት የማዳጋስካር ጤና ሚኒስቴር ባወጣው ዕለታዊ መግለጫ ለአራተኛ (4) ተከታታይ ቀን በሀገሪቱ አዲስ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ኬዝ እንዳልተመዘገበ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MADAGASCAR

ላለፉት አራት (4) ተከታታይ ቀናት አዲስ ኬዝ ሳይመዘገብባት የቆየችው ማዳጋስካር ዛሬ አንድ ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙን አሳውቃለች፤ በሀገሪቱ አጠቃላይ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 122 ደርሷል። ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 61 ናቸው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot