TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ventilators

ደቡብ ሱዳን 5 ምክትል ፕሬዘዳንቶች ያላት ቢሆንም ለ11 ሚሊዮን ህዝብ የሚሆን 4 የኦክስጅን መስጫ ማሽኖች አላት ሲል ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል፡፡

ምንም እንኳን ለኮሮና ቫይረስ ህመምተኞች ለመተንፈስ የሚያግዛቸው ቬንትሌተር ማሽን በደቡብ ሱዳን ካሉ ምክትል ፕሬዘዳንቶች እኩል ባይሆንም አንድም እንኳን ከሌላት ሱማሊያ በቁጥር ልቆ ታይቷል፡፡ በሱማሊያ ምንም አይነት የመተንፈሻ መሳሪያ እንደሌለ ዘገባው ያስረዳል፡፡

ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ 5 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሲሆን 3 ቬንትሌተር ብቻ ነው ያላት ፤ ላይቤሪያም በተመሳሳይ ከ6ቱ 3ቱ ብቻ ናቸው የሚሰሩት።

ቡርኪና ፋሶ ለ20 ሚሊየን ህዝብ 11 ነው ያላት ፤ በኬኒያ 257 ፤ በጋና 200 ፤ ሱዳን 80 አላቸው፡፡ በሀገራችንም 575 ቬንትለተሮች እንዳሉ ዘገባው ጠቁሟል፡፡

በአፍሪካ በአሁን ሰዓት በአጠቃላይ 2,000 ቬንትለተሮች ያሉ ሲሆን ከ46 ሺህ በላይ ሰዎች በሞቱባት በአሜሪካ ብቻ 17 ሺህ ቬንትሌተሮች እንዳሉ ነው ዘ ኒዉ ዮርክ ታይምስ በዘገባው ያስረዳው፡፡

#ETHIOFM #DERESEAMARE
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 965 የላብራቶሪ ምርመራ በዕለቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች #አለመኖራቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 10,736
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 965
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 0
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 90
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አጠቃላይ ያገገሙ - 21
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 116

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MADAGASCAR

ከደቂቃዎች በፊት የማዳጋስካር ጤና ሚኒስቴር ባወጣው ዕለታዊ መግለጫ ለአራተኛ (4) ተከታታይ ቀን በሀገሪቱ አዲስ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ኬዝ እንዳልተመዘገበ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በስፔን የሟቾች ቁጥር ጨምሯል። ባለፉት 24 ሰዓት 440 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 22,157 ደርሷል።

- በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ47,000 በላይ ሆኗል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 850,000 እየተጠጋ ነው።

- በካናዳ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ40,000 በልጧል፤ ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ 1,769 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

- በቻይና ተጨማሪ 10 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል። ስድስቱ (6) ከውጭ ሀገር የገቡ ናቸው።

- በደቡብ ኮሪያ ተጨማሪ 8 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል፤ አራቱ (4) ከውጭ የገቡ ናቸው። በተጨማሪ ለአምስተኛ ተከታታይ ቀን ነው ከ15 በታች ኬዝ ሲመዘገብ።

- በሩሲያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ62,000 በልጧል። በአንድ ቀን 4,774 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል።

- በUAE ተጨማሪ 518 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 8,756 ደርሷል።

- በኳታር ተጨማሪ 623 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 7,764 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ ያገገሙ ሰዎች 252 ደረሱ!

በጅቡቲ ባለፉት 24 ሰዓት 69 ተጨማሪ ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ በሽታ ማገገማቸው ሪፖርት ተደርጓል። በሌላ በኩል 347 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 12 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 986 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrMercyMwangangi

በኬንያ ባለለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 668 የላብራቶሪ ምርመራ አስራ ሰባት (17) ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 320 ደርሷል።

በሌላ በኩል ተጨማሪ ስድስት (6) ሰዎች ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ በሀገሪቱ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 89 ደርሷል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrLiaTadesse በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ! በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 1073 የላብራቶሪ ምርመራ ሁለት (2) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 116 ደርሷል። የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦ ታማሚ 1 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ቦታው በአፋል ክልል ገዋኔ ፤ የውጭ ሀገር…
የአፋር ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ፈረጅ ረቢሳ ለኢቢሲ ከተናገሩት ፦

- ትላንት በአፋር ክልል ዞን 3 ገዋኔ ወረዳ ላይ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘበት ግለሰብ ጋር ንክኪ ያላቸው ጓደኞቹ እንዲሁም ህክምና ያደረጉለት የጤና ባለሞያዎች በለቶ ማቆያ ውስጥ ይገኛሉ።

- ቫይረሱ የተገኘበት ግለሰብ የቀን ሰራተኛ (ከሰል አክሳይ) ነው። ቤተሰቦቹ አማራ ክልል ነው የሚገኙት፤ ከአማራ ክልል ከመጣ ወራት ተቆጥረዋል።

- 12 ከሰል አክሳዮች ቫይረሱ እንደተገኘበት ከተረጋገጠው ግለሰብ ጋር ጓደኝነት ያላቸው እንዲሁም 9 የጤና ባለሞያዎች ሲያክሙት እና ሲከታተሉት የነበሩ ወደለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደርገዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በአፋር ክልል የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እየተከናወኑ ስለሚገኙ ተግባራት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ፈረጅ ረቢሳ ከተናገሩት ፦

- አፋር ክልል በጅቡቲ እና በኤርትራ ድንበር አካባቢ ያለ ክልል በመሆኑ የቅድመ መከላከል ስራዎች ተጠናክረው እየተሰሩ ነው።

- በጋላፊ ጅቡቲ መስመር ጠንከር ያለ የመከላከል ስራ እየተሰራ ነው። በአማካይ በቀን 2143 የሚሆኑ ከባድ መኪናዎች ስለሚገቡ ሹፌሮች እና ረዳቶች የሙቀት ልኬት እየተደረገላቸው ይገኛል።

- ከባለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ መኪናዎችን ኬሚካል የመርጨት ስራ እየተሰራ ይገኛል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#DrFerejReebisa

በአፋር ክልል የኮቪድ-19 ምርመራ ለማድረግ ዝግጅት ከተጠናቀቀ በኃላ ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ የተገኙት PCR ማሽኖች ሲፈተሹ ሊሰሩ እንዳልቻሉ ዶክተር ፈረጅ ረቢሳ ተናገረዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ይህን ችግር ለመፍታት ከጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከEPHI ጋር ንግግር እያደረገ ይገኛል።

በየቀኑ ከ50 - 60 ሰው ሰመራ ዩኒቨርሲቲ እየገባ ነው ፤ አሁንም ክልሉ ናሙና ወደ አዲስ አበባ እየላከ ነው ምርመራ እያስደረገ የሚገኘው።

አፋር ክልል የመግቢያ በር እስከሆነ ድረስ አማራጭ ካለ ወደ ክልሉ ማሽኑ መጥቶ በ24 ሰዓት ውስጥ ምርመራ የሚደረግበት መንገድ እንዲመቻችም የፌደራል መንግስት ተጠይቋል።

PHOTO : FILE
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Qatar

- የኳታር አሚር በትላንትናው እለት ለበርካታ የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አድርገዋል።

- በረመዳን የፆም ወቅት የመንግስት ሰራተኞች በቀን አራት ሰዓታት ብቻ (ከ 9:00 AM - 1:00 PM) እንዲሰሩ፤ በግል ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞች ደግሞ በቀን ለስድስት ሰዓታት (ከ 9:00 AM - 3:00 PM) እንዲሰሩ ተወስኗል። ሆኖም ውሳኔው ምግብ ነክ ምርቶችን የሚያቀርቡ ሱቆችን፣ ፋርማሲዎችን እና በትዕዛዝ የሚሰሩ ምግብ ቤቶችን አይመለከትም።

- ማንኛውም ነዋሪ ወደ ሱቆች፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ እንዲሁም የህዝብ እና የግል ቢሮዎች ሲሄዱ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ይህን ውሳኔ ተላልፎ የሚገኝ ግለሰብ ህጋዊ #እርምጃ ይወሰድበታል።

- ከImam Muhammad ibn Abd al-Wahhab መስጅድ በስተቀር ሁሉም መስጅዶች ዝግ ሆነው ይቆያሉ።

(የኢትዮጵያ ኤምባሲ-ዶሃ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
አጫጭር መረጃዎች፦

- በUK በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ክትባት #ሙከራ ለሁለት በጎ ፍቃደኞች በዛሬው ዕለት ተሰጥቷል።

- በፈረንሳይ ተጨማሪ 516 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 21,856 ደርሷል።

- በጣልያን የሟቾች ቁጥር ጨምሯል። ባለፉት 24 ሰዓት 464 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። ተጨማሪ 2,646 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት 638 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተድርጓል። ቁጥሩ ባለፉት 2 ቀናት ከተመዘገበው ዝቅተኛ ነው። በሀገሪቱ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 18,738 ደርሷል።

- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ48,000 በልጧል። በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ865,000 በልጧል።

- በደቡብ አፍሪካ ባለፉት 24 ሰዓት 9,796 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ተጨማሪ 318 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3,953 ደርሷል።

- በሴኔጋል ባለፉት 24 ሰዓት 387 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 37 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 479 ደርሰዋል። 257 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

- በሩዋንዳ 1,343 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አንድ (1) ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 154 ደርሰዋል። በሌላ በኩል ተጨማሪ 3 ሰዎች ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 87 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሙከራ በUK ፦

- በዛሬው ዕለት በዩናይትድ ኪንግድም የኮሮና ቫይረስ ክትባት #ሙከራ ለሁለት በጎ ፍቃደኞች ተሰጥቷል።

- ዛሬ በሙከራ ደረጃ የተሰጠው ክትባት በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ነው።

- ይህ የኮሮና ቫይረስ ክትባት 80% ውጤታማ እንደሚሆን በሳይንቲስቶች ተስፋ ተጥሎበታል።

- የUK ጤና ሚኒስትር ማት ሀንኮክ ከቀናት በፊት በሰጡት አስተያየት "ስለ ሂደቱ እርግጠኛ መሆን አደማይቻል ፤ የክትባት ዝግጅት የሙከራ እና የስህተት ሂደት" መሆኑ አስገንዝበው ነበር።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#EthiopianAirlines

'የኢትዮጵያ አየር መንገድ የምህንድስና ክፍል' የተበላሹ የመተንፈሻ ቬንትሌተሮችን በመጠገንና ለኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ህመምተኞች ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ የህክምናውን ዘርፍ በመደገፍ ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ERITREA

በኤርትራ ተጨማሪ 5 ሰዎች አገገሙ!

የኤርትራ ጤና ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አምስት (5) ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ በሽታ አገግመው ከሆስፒታል መውጣታቸውን አሳውቋል። በሀገሪቱ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 11 ደርሷል። እስከዛሬ ድረስ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 39 ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrDebretsionGebremichael

እስካሁን በተደረገው ዳሰሳና ምርመራ በትግራይ ክልል ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው እንዳልተገኘ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ገልፀዋል። በቀጣይ ግን የሚታወቅ ነገር የለም ብለዋል ምክትል ፕሬዘዳንቱ።

ዶክተር ደብረፅዮን በተወሰኑ የንግድ ተቋማት ላይ ተጥሎ የነበረው ክልከላ እንደሚነሳም አሳውቀዋል። ይሁን እንጂ የቫይረሱን ወረርሽኝ ለመከላከል የሚደረጉ ሁሉም ዘዴዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ኮፊ ሀውስ፣ ካፌ፣ ጭማቂ ቤት፣ ጸጉር ቤቶች ስራ መቀጠል ይችላሉ ተብሏል፤ ጠላ ቤቶች (take away - ገዝቶ ለሚሄድ)፣ መጠጥ ቤቶችና አከፋፋዮች በመጋዘን የያዙትን ብቻ መሸጥ ይችላሉ (take away) ፤ በትራንስፖርት በኩል ደግሞ በገጠር ወረዳ ውስጥ ከቀበሌ ቀበሌ የሚሄዱ መኪኖች ብቻ አገልግሎት እንዲቀጥሉ ተብሏል።

ምንጭ፦ ትግራይ ቲቪ፣ ዳንኤል ብርሃኔ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UAE

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ለ24 ሰዓት ጥላ የነበረውን የእንቅስቃሴ ገደብ ለረመዳን ወር በመጠኑ ማላላቷን ቢቢሲ ዘግቧል።

አዲሱ የእንቅስቃሴ ገደብ ከምሽቱ አራት ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ የሚዘልቅ ሆኖ ዜጎች ቀን እንዲንቀሳቀሱ ይፈቅዳል።

ላለፉት ሦስት ሳምንታት ዱባይ በጣም ጥብቅ የተባለውን የእንቅስቃሴ ገደብ የጣለች ሲሆን በዚያም ወቅት ዜጎች በቤታቸው እንዲቀመጡ ታዘው ነበር።

ዱባይና አቡዳቢ በቅርቡ ሱቆቻቸውን ለመክፈት እቅድ እንዳላቸው ለማወቅ ተችሏል።

የንግድ ማዕከሎቹ የሚከፈቱበት መመሪያ የተዘጋጀ ሲሆን የገበያ አዳራሾቹ ማስተናገድ ከሚችሉት 30 በመቶ ብቻ እንዲያስተናግዱ የማዕከላቱ አስተዳዳሪዎችም ይህን መፈፀሙን እንዲያረጋግጡ ታዝዟል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
رمضان مبارك

የእስልምና እምነት ተከታይ ለሆናችሁ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በሙሉ እንኳን ለ1,441ኛው የተቀደሰው የረመዳን ጾም በሰላም አደረሳችሁ፤ የወቅቱ ፈተና የሚያልፍበት ፤ ረህመት ሚዘምብበት ወር እንዲሆን ከልብ እንመኛለን!

ረመዳን ሙባረክ!
رمضان مبارك
Ramadan Mubarak!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#CARD

የጥላቻ ቃላትን እና ዓረፍተ ነገሮችን ለመለየት እና ለመረዳት የሚደረግ ሰርቬይ ነው። ሰርቬዩ የጥላቻ ቃላትን ዝርዝር በተጠና መንገድ በማዘጋጀት የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንዲያስወግዷቸው ይረዳል። 

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSe2vnd9oVr9iL1TA_Q8T6q9AXpUKNklWrPOkvH5yB_uxLH-SA/viewform?usp=send_form

Qorannoo sarara irraa Itiyophiyaa kessatti tamsaasa jechoota jibbaa fi balaa uumuu dandaa'an ilaalchise godhame.

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdh2N-lwmZBNlKV2jcAB1tEz_9LEIU4krsUzxJKL0ZaN5xg7w/viewform?usp=send_form

This survey intends to identify and understand hate and inflammatory words and terms in Ethiopian local languages. The result will help us develop a lexicon of hate speech terms and phrases to help social media users to avoid the use of them and the social media platform moderate them effectively. 

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScRCF9rDhOQYTf6m7mizLBjUQsjJCYycRjWcUBsHlqp9Tbr0Q/viewform?usp=send_form
#DrLiaTadesse

አንድ (1) ተጨማሪ ሰው የኮሮና ቫይረስ ተገኘበት!

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 933 ሰዎች መካከል አንድ (1) ሰው የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት የጤና ሚኒስቴር ገልጿል። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 117 ደርሷል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
(በሸገር ኤፍ ኤም 102.1)

ለሌላ ህክምና የሄዱ ግን በኮቪድ-19 የጠረጠራቸውን ህሙማን በተለየ ክፍል የሚያክመው የቅዱስ ጳውሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እስካሁን ካከማቸው መካከል ሶስቱ (3) ቫይረሱ እንዳለባቸው ተረጋግጦ ወደ የካ ኮተቤ ሆስፒታል መላካቸውን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ተናግሯል።

ሆስፒታሉ ለአጣዳፊ ቀዶ ህክምናና ለሌላም መጥተው ግን በኮቪድ 19 የጠረጠራቸውን ለማከም 18 አልጋ ያለው ክፍል አዘጋጅቶ ከሌሎች ህሙማን ለይቶ ማከም ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡

ይህ ክፍል ሌሎች ህሙማን በፍጹም የማይገቡበት ሐኪሞችም ለነሱ ብቻ ህክምና የሚሰጡበት እንደሆነ ሆስፒታሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግሯል፡፡

እስካሁንም በኮቪድ 19 ለተጠረጠሩ 200 ህሙማን የቀዶ ህክምናና ሌላም ህክምና ሰጥቷል የተባለ ሲሆን በመጨረሻ ከዚህ ቀደም በተደረገ ምርመራም ከመካከላቸው ፖዘቲቭ ሆነው የተገኙ 3 ህሙማንን አግኝቻለሁ ብሏል፡፡

ፖዘቲቭ ሆነው የተገኙ የኮቪድ 19 ህክምና እየተሰጠበት ወደሚገኘው የካ ኮተቤ ሆስፒታል የተላኩ ሲሆን ቀሪዎቹ ነፃ በመሆናቸው መደበኛ ህክምናውን ተቀላቅለዋል ተብሏል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia