TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia #Sudan

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ እና ሱዳንን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ በአረብኛ ቋንቋ ባሰራጩት መልዕክት የሱዳንና የኢትዮጵያ ህዝቦች ወንድማማቾች መሆናቸውን ገልፀው በሁለቱ ሀገራት መካከል ችግር መኖሩ ግልፅ ነው ብለዋል።

ነገር ግን ሁለቱ ሀገራት እነዚያን ችግሮች ለመፍታት ሊጥሩ እና ሊተባበሩ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ እና ሱዳንን ለማጋጨት የሚፈልጉ መንግስታት ወይም #ሌሎች_ወገኖች ቢኖሩም እነዚህ አካላት ከሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ግጭት የሚያተርፉት አይኖርም ሲሉ አስረድተዋል።

#በውጭ_ሀይል_ግፊት በሁለቱ ሀገራት መካከል ውዝግብ ሊኖር እንደማይግባ ገልፀው ራሳችንን ልንቆጣጠር እና ከግጭት ልንቆጠብ ይግባል ብለዋል።

" በመካከላችን የጠላትነት መንፈስ ሊኖር አይግባም ፤ ይልቁንም በልማት ልንተባበር እና አብረን ልናድግ ይገባናል " ሲሉ ገልፀዋል።

ለሱዳን ህዝብ ክብር አለን ያሉት ዶ/ር ዐቢይ የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ያጋጠማቸውን ችግር በወንድማማችነትና በመልካም ጉርብትና መንፈስ የመፍታት አቅም አላቸው ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ ትላንት የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ም/ቤት ሊቀ መንበር አብዱል ፋታህ ከአውሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኔቴ ዌበር ጋር ካርቱም ውስጥ ተወያይተው ነበር ፤ በዚህም ወቅት ቡርሃን " ከኢትዮጶያ ጋር ጤናማ ግንኙነት እንዲኖረን እንፈልጋለን " ማለታቸውን ሱና ዘግቧል።

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ያለውን አለመግባባት ለማርገብ ጥረት እያደረገ መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethiopia