TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Malawi የማላዊ ምክትል ፕሬዜዳንት ሳውለስ ቺሊማን እና ሌሎች ባለስልጣናትን ይዞ ከራዳር እይታ ውጭ የሆነውን እና የገባበት ያልታወቀውን አውሮፕላን ፍለጋ እየተካሄደ ነው። ፍለጋው እየተካሄደ ያለው በመከላከያ ወታደሮች ፣  በፖሊስ አባላት እንዲሁም በሌሎች ሲቪል ዜጎች እንደሆነ ተነግሯል። የሀገሪቱ መንግስት #ያሰማራው_ኃይል እንዲህ አይነቱን ፍለጋ ለማድረግ አቅም ስለሌለው እና ምንም ማድረግ ስለማይችል…
" ፓይለቱ ወደ ኃላ እንዲመለስ ተነግሮት ነበር ፤ ከዛ በኃላ ግን አውሮፕላኑ የት እንደገባ አልታወቀም " - የማላዊ ፕሬዜዳንት

የተሰወረው የማላዊ አውሮፕላን አልተገኘም።

በአውሮፕላኑ ውስጥ ከም/ፕሬዜዳንቱ ጋር የቀድሞው ፕሬዜዳንት ባኪሊ ሙሊዚ ባለቤት / የቀድሞ ቀዳማዊ እመቤት ሻኒል ዲዚምቢሪ እንደሚገኙበት ተነግሯል።

አንዳንድ ሚዲያዎች እና የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ባኪሊ ሙሊዚ " በጣም ድቅድቅ ጨለማ ሆኗል " በሚል " በቃ ነገ ጥዋት ይቀጥላል ተብሎ " ፍለጋው እንደቆመ ተናግረዋል።

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ላዛሩስ ቻክዌራ ለሊቱን በሰጡት መግለጫ " ይሄ ውሸት ነው ምንም የቆመ ፍለጋ የለም ፤ የመከላከያ ወታደሮች በስፍራው ላይ ፍለጋ ላይ ናቸው " ብለዋል።

ከዚህም ባለፈ ፕሬዝዳንቱ ለፍለጋው ጎረቤት ሀገራትን እና የአጋር ሀገራት አሜሪካ ፣ ኖርዌይ ፣ እስራኤል ፣ ዩናይትድ ኪንግደም መንግሥታትን " አፏልጉኝ " ሲሉ እገዛ እንደጠየቁ አሳውቀዋል።

ፕሬዜዳንቱ አውሮፕላኑ ከዋና ከተማ ሊሎንግዌ ተነስቶ ወደ መዳረሻው መዙዙ ከተማ ሲጓዝ እንደነበር ገልጸዋል።

ነገር ግን ፓይለቱ በመጥፎ የአየር ሁኔታ የተነሳ ለእይታ ምቹ ሁኔታ ስላልነበር አውሮፕላኑን ማሳፈር እንዳልቻለ ፤ በኃላም የአቪዬሽን ሰዎች ወደ ኃላ (ሊሎንግዌ) እንዲመለስ እንደተነገሩት ከዛ በኃላ ግን የት እንደገባ እንዳልታወቀ አስረድተዋል።

አውሮፕላኑ ምክትል ፕሬዜዳንቱን ጨምሮ በአጠቃላይ 10 ሰዎችን ይዞ ነበር።

#Malawi #ChilimaMissingPlane

@tikvahethiopia