TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FightCOVID19

- የነቀምቴ ከተማ ወጣቶች ባለፉት ቀናት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሊቸገሩ ለሚችሉ ወገኖች እገዛ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰሩ እንደነበር አሳውቀውናል።

- በይርጋዓለም ከተማ የሆስፒታል ሰፈር ወጣቶች 'እኛ ለእኛ' በሚል ስያሜ በተቋቋመው ማህበር ከማህበሩ አባላትና ከአንዳንድ በጎ ፈቃደኞች የተሰበሰበ እህል እና የፅዳት መጠበቂያ ሳሙናዎችን ለአቅመ ለሌላቸው ወገኖች የመጀመሪያ ዙር እርዳታ ማድረጋቸውን አሳውቀውናል።

- የዲላ ከተማ ጤና ስፖርት ማህበር/ Dilla Town Health Sport Association ማዕዳቸውን አጋርተዋል። ዲላ ከተማ ጤና ስፖርት ማህበር በየወሩ ከሚያግዛቸው ስዎች በተጨማሪ የኮረና ወረርሽኝ መግባቱ ከታወቀ በኃላ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላላቸው በድጋሚ ሁለተኛ ዙር 35 እረዳት የሌላቸውን እናትና አባቶች ድጋፍ አድርገዋል።

PHOTO : (1-ይርጋለም) (2 - ዲላ) (3- ነቀምቴ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

- በወልቂጤ ከተማ የሚገኘውን የቁርአን ትምህርት ቤትና በጉብሬ ክፍለ ከተማ የሚገኘው ኤዋን ህንፃ የኮሮና ቫይረስ የሚጠረጠሩ ሰዎች ቢገኙ ለለይቶ ማቆያ እንዲሆን የእስልምና እምነት አባቶች ለከንቲባው አስረክበዋል። ህንፃዎቹ ከ90 በላይ ሠዎችን የማስተናገድ አቅም አላቸው።

- በምዕራብ ናዝሬት መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን መሪዎች፣ አገልጋዮች እና ምዕመናን ከ120 ለሚበልጡ ቤተሠቦች እገዛ አድርገዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#FightCOVID19

- የድሬ ከተማ ተጫዋቾች ከዚህ በፊት የአንድ ወር ደሞዛቸውን በኮሮና ወረርሽኝን ምክንያት ለሚጎዱ ህብረተሰብ ድጋፍ አድርገዋል። አሁን ደግሞ ቢኒያም ታደሰ እና ሻፊ አብዱረዛቅ የተባሉ የክለቡ ደጋፊዎች ማህበር አባል የሆኑት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር አቅመ ደካማ የሆኑ ህብረተሰብን ለሁለት ሳምንት እየመገቡ ይገኛሉ።

- የሀና መውጫ ወጣቶች ማህበረሰቡን በማስተባበር ለ50 አረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞችና ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የበአል ስጦታ(እቁላልና ዶሮ)፣ እንዲሁም የተለያዩ የምግብ ግብአቶችንና የንፅህ መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድረገዋል።

- የጅማ ዩኒቨርሲቲ ዲፖ የሴቶች ኮንዶሚኒዬም ነዋሪ መምህራንና ሰራተኞች ከዚህ በፊት የትምህርት ቁሳቁስ በመግዛት ሲረዷቸዉ የነበሩትን ወላጅ አልባ ልጆችን ጨምሮ በቀበሌዉ ለሚገኙ 25 ቤተሰብ 14,180 ብር በማዋጣት ድቄት ዘይትና ሳሙና ገዝተዉ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

PHOTO : (1-JIMMA) (2-ADDIS ABABA) (3-DIREDAWA)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#FightCOVID19

- የአዲስ አበባ ከተማ ከተማ አሰተዳደር ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ከሜድሮክ ኢትዮዽያ ኢትዮ አግሪሴፍ የተረከባቸውን 45 የደለቡ በሬዎች 'ማዕድ ማጋራት' በሚል ለአርባ ሰፈሮች በቄራዎች ድርጅት ጤናማነቱን ያረጋገጥ እርድ ተከናውኖ እንድሰራጭ በቄራዎች ድርጅት ግቢ ርክክብ ተደርጎል። የስጋ ስርጭቱን የአ.አ ቄራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ሰይድ እንድሪስ እና ከአርባ ሰፈር በጎ ፈቃደኞች ወጣቶች ጋር በመተባበር ለመስራት ቃል ገብተዋል።

- አትሌት መሰረት ደፋር መገናኛ አካባቢ እያስገነባች ያለውን ባለ 12 ወለል ሕንጻ ኮቪድ-19ኝን ለመከላከል ለለይቶ ማቆያነት እንዲያገለግል አስረክባለች።

- ራይድ #RIDE የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው ጥረት በተለያዩ የህክምና ተቋማት እያገለገሉ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች እንዲሆን 50,000 የአፍ መሸፈኛ ማስኮችን ለኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች ማህበር አስረክቧል።

- ጋስት ሶላር መካኒክስ ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የያዛቸው ታካሚዎች አተነፋፈሳቸውን የሚያግዝ ቱቦ ወደ አየር ቧንቧቸው ሲገባ እንደ መከላከያ የሚያግዝ መሳሪያ ለጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እገዛ አድርጓል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
አጫጭር መረጃዎች ፦

- ሳዑዲ አረቢያ ባለፉት 24 ሰዓት 1,132 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ሪፖርት አድርጋለች። እስካሁን በአንድ ቀን ከተመዘገቡት ኬዞች ከፍተኛው ነው። በሳዑዲ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 8,274 ናቸው።

- በኢራን ባለፉት 24 ሰዓት 1,374 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ በ26 ቀን የተመዘገበ ዝቅተኛው ኬዝ ነው። እንዲሁም 73 ሰዎች በአንድ ቀን ሞተዋል፤ በ38 ቀናት የተመዘገበ ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ነው።

- በስፔን የእንቅስቃሴ ገደብ እስከ May 9 ተራዝሟል።

- በፈረንሳይ ባለፉት 24 ሰዓት የ642 ሰዎች ሞት ተምዝግቧል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 19,323 ደርሷል።

- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ38,000 በላይ ሆኗል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ728,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል።

- በሩዋንዳ ባለፉት 24 ሰዓት 712 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አንድ (1) ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 144 ደርሰዋል። በሌላ በኩል ተጨማሪ 4 ሰዎች በማገገማቸው አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 69 ደርሰዋል።

- ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ 25 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 19 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 135 ደርሰዋል። በተጨማሪ ሁለት (2) ሰዎች ባለፉት 24 ሰዓት ሞተዋል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የተያዙ ሰዎች 2,313,897 ደርሷል። ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ590,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል። ከ159,000 በላይ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሱማሊያ ?

የመመርመር አቅሟ ትንሽ በሆነው በጎረቤታችን ሱማሊያ ከትላንት በስቲያ 47 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 36 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት በተደረገ 25 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 19 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። አሁን አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 135 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ዛሬ ቫይረሱ እንደተገኘባት የተረጋገጠው የጅማ ዞን ሊሙኮሳ ወረዳ ነዋሪ ከሆነችው ግለሰብ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ እያሰባሰበ መሆኑን የወረዳው አስተዳደር ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ገልጿል።

እስካሁን 39 ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ መግባታቸውን እና የቅርብ ግንኙነት ያላቸው የ12 ሰዎች ናሙና ተወስዶ ውጤት በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ጣሂር ኢብራሂም ተናግረዋል።

በሊሙ ኮሳ ወረዳ የወለኬ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው የ20 ዓመት ወጣት የህመሙን ምልክት ካየች ከአንድ ወር ያላነሰ ጊዜ እንደሆነ እና ለህክምና እና ለጠበል ወደተለያዩ አካባቢዎች መንቀሳቀሷን አቶ ጣሂር ተናግረዋል።

ከእነዚህ ውስጥም ለ19 ቀናት ያህል በጢስ አባይ ጠበል ላይ መቆየቷን ይናገራሉ። በቫይረሱ መያዟ ከተረጋገጠባት ወጣት መኖሪያ ቀበሌና አካባቢው እንቅስቃሴዎች መገደባቸውን አቶ ጣሂር ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
Baga ayyaana Du'aa Ka'u Kiristosin nagaan gessan!
እንኳዕ ንበዓል ትንሳኤ ኣብፀሓኩም!

ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆናችሁ በየትኛውም የዓለም ክፍል የምትገኙ የቲክቫህ አባላት እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ! በዓሉ የሰላም፣ የጤናና የመተሳሳብ እንዲሆን እንመኛለን።

የዘንድሮው የትንሳኤ በዓል በፈተና ውስጥ ሆነን እያከበርን እንደሆነ ይታወቃልና በዓሉን ስታከብሩ ሊደረጉ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎች ችላ እንዳትሉ ለማስታወስ እንወዳለን!

ረጅም እድሜና ጤናን እንመኝላችኃለን!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ 1 ሺህ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎችን እንዲይዝ ተደርጎ እየተዘጋጀ ያለውን የሚሊኒየም አዳራሽ ማዕከል ተዘዋውረው መጎብኘታቸውንና የተከናወነውን ስራ መገምገማቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ሚሌኒየም አዳራሽ ለድንገተኛ ወረርሽኝ ምለሽ መስጠት በሚችል ትልቅ ሆስፒታል ደረጃ መዘጋጀቱ ተገልጿል። በአሁኑ ወቅት 360 አልጋዎች ዝግጀቱ ሆነዋል፤ ቀሪዎቹም አልጋዎች በሳምንት ውስጥ ዝግጁ እንደሚሆኑም ነው የተመለከተው።

በህክምና ማዕከሉ 40 የፅኑ ህክምና መስጫ አልጋዎች እና 60 የማገገሚያ አልጋዎችም የኖሩታል። የህክምና ማዕከሉ 700 የህክምና ባለሙያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 1 ሺህ ሰራተኞች እንደሚኖሩትም ነው የተገለፀው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 667 የላብራቶሪ ምርመራ ሶስት (3) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 108 ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ62 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ፤ ከአሜሪካ የመጡና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ።

ታማሚ 2 - የ52 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላት፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላት ግንኙነት በመጣራት ላይ ያለ።

ታማሚ 3 - የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ ከሳዑዲ አረቢያ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 7,557
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 667
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 3
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ያሉ - 87
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 1
• አጠቃላይ ያገገሙ - 16
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 108

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia