TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሳይንስ እና ቴክኖ. ዩኒቨርሲቲ⬇️

አዳማና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ለ3ኛ ጊዜ ሊሰጥ ነው።

በ2011 #የአዳማና #የአዲስ አበባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ፈተና ለ3ኛ ጊዜ ‘#በቀጥታ’ በበይነ መረብ ሊሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ስር የሚገኙት የአዳማና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች ለ2011 የትምህርት ዘመን የመሰናዶ ትምህርት ጨርሰው #ከፍተኛ ውጤት ያመጡትና ለፈተና ከቀረቡት 4 ሺህ 700 ተማሪዎች መካከል በፈተና በማወዳደር 3ሺህ ተማሪዎች ሊቀበል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፈተናው #ረቡዕ ነሃሴ 30፣ 2010 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ እስከ 11፡00 ድረስ በተለያዩ ክልሎች ባሉ 37 ዩኒቨርስቲዎች በቀጥታ በበይነ መረብ የሚሰጥ ሲሆን፥ የመግቢያ ውጤቱ ለታዳጊ ክልሎች፣ ለሴቶችና አካል ጉዳተኞች ዝቅ እንዲል ተደርጓል ተብሏል፡፡

ፈተናው ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ሂሳብና ኢንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነቶቸን የሚያካትት ሲሆን፥ ዝቅተኛው የማለፊያ ውጤት ከ50 በላይ ሁኗል ተብሏል፡፡

ፈተናው በበይነ መረብ ከአንድ ማዕከል የሚተላለፍ ሲሆን፥ የወረቀት ብክነትንና የፈተና ስርቆትን ለማስቀረት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደረግ ነው የተገለጸው፡፡

ታላላቅ ድርጅቶች ብዛት ያለው የሰው ሀይል ለመቅጠር በፈተና ማወዳደር በሚፈልጉበት ጊዜ ይህንን ስርዓት በመጠቀም ፈትነው ለቃለመጠይቅ ብቻ የሚፈልጉትን ሰው በመጥራት መቅጠር እንዲችሉ ያደርጋል ተብሏል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርም ይህንን የፈተና ስርዓት መጠቀም ለሚፈልግ ማንኛውንም አካል ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮ. አየር መንገድ ከግጭት ተረፈ⬇️

ዘ ኢስት አፍሪካን እንደዘገበው ባለፈው #ረቡዕ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ ኢት 858፣ ቦይንግ 737-800 ከጣሊያኑ የሌዢር ኤርላይን ኒዮስ ቦይንግ 767-306 R የበረራ ቁጥር NOS 252 ጋር በኬንያ ሰማይ ላይ #ለመጋጨት ሲቃረብ #በአንድ ደቂቃ ልዩነት ተርፏል።

አደጋ ተፈጥሮ ቢሆን ኖሮ በአለም አሰቃቂው የአውሮፕላን አደጋ ተብሎ ይመዘገብ እንደነበር ጋዜጣው ዘግቧል። ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ በ37 ሺ ጫማ ከፍታ ላይ በመብረር ላይ የነበረ ሲሆን፣ በተመሳሳይ ቀን ምሽት 12 ሰዓት ላይ የጣሊያን አውሮፕላን ከቪሮና ተነስቶ ወደ ዛንዚባር በማምራት ላይ ነበር። እኩለ ሌሊት ላይ ሁለቱም አውሮፕላኖች ወደ ኬንያ አየር ክልል የገቡ ሲሆን፣ ሁለቱም ለግጭት በሚያደርሳቸው ሁኔታ ፊት ለፊት እየተጓዙ እንደነበር ጋዜጣው ዘግቧል።

የግጭት መቆጣጠሪያ መሳሪያው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የማስጠንቀቂያ መልዕክት እንዳስተላለፈ ፣ ፓይለቱ በአንድ ደቂቃ ውስጥ ወደ 38 ሺ ጫማ ከፍ በማድረግ እና ለ5 ደቂቃ በዚሁ ከፍታ ላይ በመቆየት አደጋ እንዳይፈጠር ለማድረግ ችሎአል። የኬንያ አየር ተቆጣጣሪዎች የኢትዮጵያን የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ተጠያቂ አድርገዋል።

የኢትዮጵያ የአየር ታረፊክ ተቆጣጣሪዎች
እንደገለጹት የጣሊያን አየር መንገድ አስቀድሞ በምን ያክል ከፍታ እንደሚበር ሲገልጽ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ይህን ባለማድረጉ አደጋው ሊደርስ እንደነበር ገልጸዋል። የኢትዮጵያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አደጋው ከመድረሱ አራት ቀናት በፊት የስራ ማቆም አድማ አድርገው ነበር።

ይህንን ተከትሎ የኬንያ አየር መንገድ ከ አዲስ አበባ የሚነሱና ወደ አዲስ አበባ የሚደረጉ በረራዎች ደህንነታቸው አስተማማኝ አለመሆኑን አስቀድሞ #ማስጠንቀቂያ ልኮ እንደነበር ጋዜጣው አክሎ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን ባለስልጣን በኬንያ በኩል የቀረበውን ክስ ውድቅ አድርጎታል። የኬንያ አየር ተቆጣጣሪ ያወጣው መግለጫ ሃሰትና መሰረተ ቢስ ነው ያለው የሲቪል አቬሽን ባለስልጣን፣ እንዲህ አይነት አደጋ ይከሰታል የሚል መረጃ ለኢትዮጵያአየር ተቆጣጣሪዎች አለመነገሩን ገልጿል።

📌የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን ለአድማ አነሳስተዋል የተባሉ 9 አመራሮችና ሰራተኞች #መታሰራቸው ይታወቃል።

©ESAT
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update DV 2020⬆️

የ2012 ዲቪ ሎተሪ ከዛሬ፤ #ረቡዕ መስከረም 23/2011 ዓ.ም. ጀምሮ ክፍት እንደሚሆን አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ አስታውቋል። በሎተሪው ለመሣተፍ የሚፈልጉ አመልካቾች #ለመመዝገብ ምንም ዓይነት ክፍያ ለማንም መክፈል እንደሌለባቸው አሳስቧል።

ማሳሰቢያ፦ በVOA ዘገባ በምትሰሙት ድምፅ ያለውን የቀን ስህተት ወደ ዛሬ ትቀይሩት ዘንድ በአክብሮት ጠይቃለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቀን ማስተካከያ፦

#StopHateSpeech በዚህ ሳምንት የሚደረጉት መድረኮች ላይ የቀን ማስተካከያ ተደርጓል። በዚህም መሰረት፦

#ረቡዕ የጉዞ መነሻ ከሀዋሳ፣ወልቂጤ፣ ከአርባ ምንጭ፣ ከወ/ሶዶ ከተሞች --- #ደብረ_ብርሃን ይታደራል።

√ሀሙስ - ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጋር ውይይት ይደረጋል።

√አርብ - ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ከTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጋር ውይይት ይደረጋል።

√ቅዳሜ - መቐለ ዩንቨርስቲ ልዩ ዝግጅት ተዘጋጅቷል።

አዲስ ነገር...👇

በዚህ ዘመቻ ላይ በወጣቶች ብቻ የተመሰረተ የሙዚቃ ባንድ ይቀላቀለናል፤ በረቂቅ ሙዚቃም ፍቅር እና ሰላምን ይሰብካሉ። እንዲሁም በሴቶች ላይ ስለሚነገሩ እና ስለሚሰነዘሩ የጥላቻ ንግግሮች ግንዛቤ ለመስጠት #መራሂት እና #ያንቺ_ንቅናቄ በሴቶች ላይ የሚሰሩ ቡድኖች አብረውን ይጓዛሉ።


@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StateHouseKenya

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለ2 ቀናት የሥራ ጉብኝት ወደ ኬንያ እንደሚያቀኑ የኬንያ ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤትን ዋቢ አድርጎ ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

የኬንያው ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ፕሬዝዳንት ኡኹሩ ኬንያታ እና ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በመርሳቢት ግዛት በምትገኘው ሞያሌ በመጪው #ረቡዕ እንደሚገናኙ አስታውቋል።

በዕለቱ ሁለቱ መሪዎች የሞያሌ የድንበር መተላለፊያን ጎብኝተው በይፋ እንደሚከፍቱ መግለጫው ገልጿል። ሁለቱ መሪዎቹ በዚያው ዕለት የላሙ የወደብ ግንባታን ይጎበኛሉ።

የላሙ ወደብ ግንባታ ኬንያ ፣ ኢትዮጵያ እና ደ/ሱዳንን ለማስተሳሰር የታቀደ የመሠረተ ልማት ግንባት አንድ አካል ነው።

* የState House Kenya ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጨማሪ የባህር ዳር ፣ ጎንደርና ሸዋሮቢት ነዋሪዎች ምን አሉ ? የባህር ዳር ፣ ጎንደር ፣ ሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎች ከተማቸው በመከላከያ ሰራዊት ስር እንደሚገኝና ዛሬ ተኩስ እንዳልነበር ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ በሰጡት ቃል ተናግረዋል። #ባህርዳር ነዋሪ 1 " ከትለንት ከግማሽ ለሊት በኃላ መከላከያው ተቆጣጥሮታል። ተኩስም የለም፤ መከላከያው ተቆጣጥሮታል። አንፃራዊ ሰላም አለ። መከላከያው…
የአማራ ክልል ከተሞች እንዴት ዋሉ ?

በአማራ ክልል በትልልቆቹ ከተሞች በዛሬው ዕለትም ተኩስ ሳይሰማባቸው መዋላቸውን ፤ ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ እንዳልተጀመረ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ነዋሪዎች ምን አሉ ?

#ባሕርዳር

ዛሬ  የተኩስ ድምጽ አለመሰማቱን ፤ ግጭትም ይሁን ውጊያ እንዳልነበር ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ አልጀመረም።

የንግድና የተለያዩ ቋማት በአብዛኛው ባለመከፈታቸው ከተማዋ ጭር ብላ ነው የዋለችው።

የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ መኪኖች እና ባጃጆች ወደ ሥራ ባለመመለሳቸው የነዋሪው እንቅስቃሴ ተገትቶ ውሏል።

ተቋርጦ የነበረው የ ' ኢትዮጵያ  አየር መንገድ በረራ ' ወደ ባሕር ዳር መጀመሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነገር ግን ከአውሮፕላን ማረፊያ ወደ ከተማ የሚወስድ ትራንስፖርት ስለሌለ ተሳፋሪዎች በእግራቸው ለመጓዝ ተገደዋል።

አሁንም የተወሰኑ መንገዶች በትላልቅ ቋጥኖች እና ድንጋዮች እንደተዘጉ ስለሆኑ ለትራንስፖርት አስቸጋሪ ነው።

ከተማዋ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ ባትመለስም አንዳንድ ነዋሪዎች በእግራቸው ሲንቀሳቀሱ ውለዋል።

#ደብረ_ማርቆስ

በደብረ ማርቆስ ከተማ ትራንስፖርትም ሆነ የንግድ መደብሮች ወደ ስራ እንዳልተመለሱ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

" ሱቅ፣ ሆቴል ዝግ ነው። " ያሉ አንድ ነዋሪ " ምንም እንኳን በአይኔ ባላይም ጥዋት አንድ ባስ ከማርቆስ ወጥቶ ወደ አ/አ ሄዷል የሚባል ነገር አለ ፤ ከአዲስ አበባ መስመር ግን አንድ ሁለት ባሶች ማርቆስ ገብተዋል። " ሲሉ ገልጸዋል።

በደብረ ማርቆስ ወደ ጎንደር፣ ወደሌሎችም ቦታዎች የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች እንደቆሙ ናቸው ፤ መደበኛ እንቅስቃሴም አልተጀመረም።

#ደጀን

ከተማዋ አሁን ላይ የተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም ሰሞኑን ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ አገልግሎቶች ተስተጓጉለዋል።

የውሃ እንዲሁም መብራት አገልግሎት ከተቋረጠ ቀናት እንደተቆጠሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ አስተያየት ሰጪ ፤ በብቸና መስመር ወደ ሞጣ የሚያልፍ በርካታ የመከላከያ ኃይል እንደተመለከቱ ገልጸዋል።

ብቸና ላይ ግጭት እንደነበር የሚጠርጥሩት ነዋሪው ሥፍራው ከደጀን ከ35 ኪሎ ሜትር ርቀት በላይ ቢሆንም የከባድ ተኩስ ድምፅ ግን ይሰማ እንደነበር ጠቁመዋል።

#ጎንደር

ከትላንት #ረቡዕ ጀምሮ ተኩስ እንደማይሰማና አሁን ላይ ሰላም መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ሰዎች በእግር ይንቀሳቀሱ እንጂ፣ ተሽከርካሪ የለም።  በብዛት ሱቆች እና ወፍጮ ቤቶች አገልግሎት እየሰጡ አይደለም።

በከተማው የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲከፈቱ ቢታዘዙም ሁሉም ሙሉ በሙሉ እንዳልተከፈቱ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በጎንደር የመከላከያ ሠራዊት አባላት እና ታንኮች በተለይ ደግሞ አድማ በታኞች በስፋት እንደሚታዩ ተነግሯል።

ዛሬ ወደ ጎንደር ከተማ በረራ ይጀመራል ቢባልም ወደ ከተማው አውሮፕላን እንዳልገባ ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።

#ደብረብርሃን

በደብረ ብርሃን ሱቆች እና ትራንስፖርት ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ወደ አገልግሎት እየተመለሱ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ አስተያየት ሰጪ ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ ባጃጅ መንቀሳቀስ መጀመሩን ጠቁመዋል። ዛሬ ደግሞ ሱቆች መከፈታቸውንና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ስራ መጀመራቸውን ገልጸዋል።

የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ፍተሻ እያደረጉ መሆኑ ተመላክቷል።

#ላሊበላ

" ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ባይሆንም " የመንግስት ሰራተኞች ወደ ስራ መግባታቸው ፣ ተቋማት እና ተሽከርካሪዎች በተወሰነ ደረጃ ስራ እንደጀመሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ከወትሮው የተለየ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳልታየ የገለፁት ነዋሪዎች የአውሮፕላን በረራ እንዳልተጀመረና የበረራው መጀመር እየተጠበቀ መሆኑን ጠቁመዋል።

በላሊበላ በረራ ለመጀመር ቀናት ሊፈለግ እንደሚችል ተነግሯል።

#ደብረታቦር

የከተማዋ እንቅስቃሴ በጣም ቀዝቃዛ ነው። ነዋሪው በጊዜ  ነው ወደ ቤቱ እየገባ ያለው።

አሁን ላይ በከተማዋ ፤ ምንም ዓይነት የተኩስ ድምፅ ባይሰማም  በከተማዋ የጦር መሣሪያም ሆነ ስለት ያለው ቁስ ይዞ መንቀሳቀስም ሆነ መገኘት አደጋ እንደሆነ ነዋሪዎች ገልጻዋል። ይህን ይዞ የተገኘ ሰው እርምጃ ይወስድበታል ብለዋል።

ሆቴሎችና ባንኮች ዝግ እንደሆኑ ይገኛሉ።

ምንም እንኳን በከተማው ላይ የተረጋጋ ሁኔታ ቢኖርም 800 መቶ ብር የነበረ የምግብ ዘይት እስለ 1500 ብር ድረስ እየተሸጠ እንዳለ ፤ ይሄም ቢሆን ሱቆች አሁንም ዝግ ስለሆኑ በሰው በሰው የሚገኝ እንደሆነ ተጠቁሟል።

መረጃው ከኤኤፍፒ፣ ዶቼቨለ፣ ቢቢሲ የተሰባሰበ ነው።

NB. የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ፦
- በባህር ዳር ፣
- በደብረ ማርቆስ፣
- በደብረ ብርሃን፣
- በላሊበላ ፣
- በጎንደር ፣
- በሸዋሮቢት ከባጃጆችና ከሞተር ሳይክሎች በስተቀር ሌሎች የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ከነሐሴ 4 ጀምሮ ወደ ሥራ የመመለስ እና አገልግሎት የመስጠት #ግዴታ_እንደተጣለባቸው ማሳወቁ ይታወሳል።

ከዚህም በተጨማሪ ፤ የሕዝብ የአገልግሎት ሰጪ ፣ የመንግሥት፣ የማኅበረሰብና የንግድ ተቋማት ከነሐሴ 4/2015 ጀምሮ ክፍት እንዲሆኑ ማዘዙ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
የኢድ አልፈጥር በዓል መቼ ነው ?

#ኢድ_አልፈጥር በዓል ጨረቃ በመጪው ሰኞ  ማታ ከታየች #ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ #ረቡዕ አንደሚከበር የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ዒድአልፈጥር

የዒድ አልፈጥር በዓል #ጨረቃ ዛሬ ከታየች ነገ #ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ #ረቡዕ ይከበራል።

በሳዑዲ አረቢያ የሸዋል ጨረቃ ለማየት በቱማይር እና ሱዳይር የመመልከቻ ቦታ አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
የአሜሪካ ኤምባሲ ሁለት ቀን ተዘግቶ ይውላል።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የኤሜሪካ ኤምባሲ ሰኞ እና ማክሰኞ ዝግ ሆኖ እንደሚውል አስታውቋል።

ኤምባሲው ፥ ሰኞ ግንቦት 19/2016 ' ሚሞሪያል ዴይ 'ን ወይም በግዳጅ ላይ የተሰዉ የአሜሪካ አርበኞች መታሰቢያ በዓልን ምክንያት በማድረግ እንደሚዘጋ አመልክቷል።

በነጋተው ማክሰኞ ግንቦት 20 የ #ደረግ_መንግሥት የወደቀበትን ቀን ምክንያት በማድረግ ሙሉ ቀን ተዘግቶ እንደሚውል ገልጿል።

ኤምባሲው ዳግም የሚከፈተው #ረቡዕ_ግንቦት_21 መሆኑን አሳውቋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
የግንቦት 2016 ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ #ረቡዕ ይከፈታል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዓመት ሁለት ጊዜያት ከሚካሔዱት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤያት አንዱ የግንቦት 2016 ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ነው፡፡

ይህ ጉባኤ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ርእሰ መንበርነት ረቡዕ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከጧቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በመንበረ ፓትርያርክ የቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚከፈት ተገልጿል።

@tikvahethiopia