#EngTakeleUma
በሚቀጥለው ሳምንት ተማሪዎች በያሉበት ሆነው ትምህርት እንደሚጀምሩና የምገባ መርሃ ግብሩም እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አረጋግጠዋል።
በተያዘው መርሃ ግብር መሰረት ከ7ኛ ክፍል በታች የሚማሩ ተማሪዎች ትምህርቱን በሬዲዮ የሚከታታሉ ይሆናል ተብሏል። ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርታቸውን በፕላዝማ የሚከታተሉ ይሆናል።
በዚህ ሂደት ተማሪዎችና መምህራን የተለያዩ መረጃዎችን የሚለዋወጡበት የአሰራር ስርአትም መሰርጋቱ ተገልጿል።
የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብርም በተለያዩ አካባቢዎች 1 ሺህ 200 ተማሪዎች የሚመገቡባቸው የምግብ ባንኮች ተዘጋጅተዋል፤ ለምግብ አቅርቦቱም 30 ሺህ ወጣቶች ዝግጁ ሆነዋል ተብሏል።
ምንጭ፦ ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የኢትዮጵያ የማዕድን ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን በዛሬው እለት በሙገርና በዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ተገኝተው የሲሚንቶ ምርት እንቅስቃሴዎችን ተመልክተዋል።
ኢ/ር ታከለ ፥ " የሲሚንቶ ምርትን ለመጨመር እየሰራነው ባለው የማሻሻያ ሥራ የሁለቱም ፋብሪካዎች በቀን የነበረው የምርት መጠን እየጨመረ ይገኛል" ብለዋል።
በተለይም የሲሚንቶ አምራቾች ለግብዓትነት የሚጠቀሟቸው ከውጭ የሚገቡ እንደ ድንጋይ ከሰል ያሉ የማዕድን ምርቶችን ሙሉ ለሙሉ በሃገር ውስጥ ምርት ለመተካት እየሰራን እንገኛለን ሲሉ አሳውቀዋል።
" በቅርብ ጊዜም ይህ ውጥናችን በተግባር እንደሚገለጥ ጅምራችን ማሳያ ነው" ያሉት ኢ/ር ታከለ ኡማ " ለሀገራችን ከምንም በላይ የሚጠቅማት የእድገት መንገዷ ነውና ባሰብነው ልክ ወደፊት መጓዛችንን እንቀጥላለን" ብለዋል።
ኢ/ር ታከለ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት ፅሁፍ ፥ " ኢትዮጵያዊነት ከደም አልፎ በልብ ውስጥ የተቀመጠ የተከበረ ማንነት ነው" ያሉ ሲሆን " ይህንን የተከበረ ማንነት ለማንኳሰስ ካሉበት ተጠራርተው ስለ ኢትዮጵያ በውስጣቸው የተቀበረውን ደባ ይሸርቡላታል፡፡ ግን ዛሬ ትላንት አይደለም ህዝባችን ትላንት የነበረውን ዋይታ እያወቀ ኢትዮጵያንና የዛሬው ተስፋውን ክፉ ለሚመኙለት አሳልፎ አይሰጥም፡፡ እኛ ግን በወሬው ወጀብ ሳንናወጥ ስራችንን መስራታችንን ቀጥለናል " ሲሉ ገልፀዋል።
@tikvahethiopia