TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላይ መኪናቸው ውስጥ ባልታወቀ ምክንያት ህይወታቸው አልፎ ከተገኘ ሁለት ሳምንታት አለፉ።

የኢንጂነሩ ሞት በበርካቶች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤን የፈጠረ ነበር። BBC ያነጋገራቸው የኢንጂነር ስመኘው ቤተሰብ አባላትም መሪር ሃዘን ውስጥ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢንጂነር ስመኘው ባለቤት የወ/ሮ ዕሙን ጌታሁን ታናሽ ወንድም የሆነው አካሉ ጌታሁን ''ሃዘናችን እጅግ ከባድ ቢሆንም እየበረታን ነው። ከቀብሩ ጀምሮ መንግሥት እየደገፈን ነው። ምንም ያወጣነው ወጪ የለም" ብሏል። አካሉ ጨምሮም "የስመኘው የመጀመሪያ ልጅ የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዶ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንዲመደብ እየተባበሩን ነው'' በማለት ከመንግሥት የተደረገላቸውን ድጋፍ የገለጸ ሲሆን ''ገዳዩን ለፍርድ ለማቅረብ ግን ፖሊስ በምንፈልገው #ፍጥነት እየሄደልን አይደለም'' ሲል
በምረመራው ውጤት #መዘግየት ቤተሰቡ ቅር እንደተሰኘ ይናገራል።

አካሉ ''እሱ ከተገደለ 15 ቀናት አልፈዋል። ከፖሊሶቹ ጋር በየጊዜው እንገናኛለን ይሁን እንጂ እስካሁን ግልጽፅ ያለ ነገር አልነገሩንም። ከሆስፒታል ስለተሰጣቸው መረጃም በግልጽ የነገሩን ነገር የለም'' ይላል።

የኢንጂነር ስመኘው ባለቤት የወ/ሮ ዕሙን ጌታሁን እናት የሆኑት ወ/ሮ መንበረ መኮንን ደግሞ በሃዘናቸው ወቅት ከጎናቸው በመሆን ያጽናኗቸውን ሁሉ አመስግነው ''ስለ ስመኘው እና ባለቤቱ የሚወራው ነገር ስህተት ነው። እኔ እስከማውቀው ድረስ ባል እና ሚስት በፍቅር ነበር የሚኖሩት። ተፋተዋል እየተባለ የሚወራው #ሃሰት ነው። እንዲህ አይነቱ ወሬ እያስጨነቀን ነው'' በማለት በማህበራዊ ሚዲያ የሚወራው ስህተት መሆኑን ይናገራሉ።

አካሉም ታላቅ እህቱ ለትምህርት ከሃገር ውጪ መሆኗን አስታውሶ ''እንደውም ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርጋ ልትመጣ ነበር። #መምጣቷም አይቀርም'' ብሏል።

የቤተሰብ አባላቱ በሃዘናችን ወቅት የኢትዮጵያ ህዝብ አጽናንቶናል። መንግሥትም ከጎናችን ሆኖ እየደገፈን ነው ለዚህም ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል።

ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ህይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው እንደሆነ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ዘይኑ ጀማል ገልፀው ነበር።

ዝርዝር የአሟሟታቸውን ሁኔታ በተመለከተ ፖሊስ ምርመራ እያካሄድኩ ነው ማለቱም ይታወሳል።

ኢንጂነር ስመኘው ህይወታቸው ከማለፉ ከአንድ ቀን በፊት ቢቢሲ አማርኛ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን አስመልክቶ ባነጋገርናቸው ወቅት ፕሮጀክቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለ ገልጸው ነበር።

ኢንጂነር ስመኘው ግድቡ የደረሰበትን ደረጃ የBBC ጋዜጠኞች በአካል ተገኘተው እንዲመለከቱ ጋብዘው ነበር።

©BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከትግራይ ክልል ወደ አዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ ክልል የሚደረገው የየብስ ትራንስፖርት ዛሬ በይፋ መጀመሩ ተገልጿል።

ይህ የተገለፀው ፦
👉 የአማራ ክልል የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን
👉 የአፋር ክልል የትራንስፖርት እና መንገድ ቢቶ
👉 የፌዴራል የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።

የአማራ ክልል የትራንፖርት እና የሎጀስቲክስ ባለስልጣን ምን አለ ?

- በአማራ ክልል አቅጣጫ ዛሬ 4ኛ ቀኑን የያዘ የሕዝብ ትራንስፓርት የሙከራ ጉዞ  ወደ አዲስ አበባ ተደርጓል።

- ሶስት (3) የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች በአማራ ክልል በኩል ጉዞ አድርገዋል።

- ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ ይፋዊ ጉዞ ጀምሯል።

- የአማራ ክልል መንግሥት ለማንኛውም የትራንፓርት እና ሰላማዊ እንቅስቃሴ ድጋፍ ያደርጋል።

- የክልሉ ሕዝብ ለሰላማዊ እንቅስቃሴ በጎ አመለካከት ያለው በመኾኑ ጉዞው ላይ ችግር አያጋጥምም።

የአፋር ክልል የትራንፖርት እና መንገድ ቢሮ ምን አለ ?

- በአፋር ክልል በኩል በመጀመሪያው ቀን ብቻ ሁለት የሙከራ ጉዞዎች የተደረጉ ሲሆን ትራንስፖርት ከተጀመረ ዛሬ 6 ቀናት ተቆጥረዋል።

-  ክልሉ ማንኛውም የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሰላማዊ እንዲኾን ያግዛል።  መንግሥት ብቻ ሳይኾን ሕዝቡም ሰላማዊ አንቅስቃሴውን ይደግፋል።

- ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ ይፋዊ የየብስ ትራንፖርት ጀምሯል።

የትራንፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ምን አለ ?

- ተቋርጦ የነበረው የየብስ ትራንፖርትን ለማስጀመር ሁለት የጥናት ቡድን በአማራ ክልል በኩል እና በአፋር ክልል በኩል በመላክ ጥናት ተደርጓል።

- በሁለቱም ክልሎች በኩል 19 የሙከራ ጉዞዎች ከአዲሰ አበባ ትግራይ ክልል እና ከትግራይ ክልል አዲስ አበባ ተደርጓል።

- ከዛሬ ጀምሮ  ይፋዊ የየብስ ትራንስፖርት ተጀምሯል።

የትግራይ ክልል የትራንፖርት ቢሮ ኀላፊዎች በአየር ትራንፖርት #መዘግየት ምክንያት በአዲስ አበባ በተሰጠው የጋራ መግለጫ ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል።

#አሚኮ

@tikvahethiopia