TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሞሪሽየስ ለየትኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ ድንበሬ ዝግ ነው ስትል አሳውቃለች። የሞሪሺየስ ጠቅላይ ሚኒስትር 3 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች መገኘታቸው በመረጋገጡ ነው ይህን ጥብቅ ውሳኔ ያሳለፉት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ደቡብ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የጉዞ እገዳ ያደረገችባቸው ሀገራት 9 ደርሰዋል። ሀገራቱ ፦ ቻይና ፣ ፈንሳይ ፣ ጀርመን ፣ ጣልያን ፣ ደቡብ ኮሪያ ፣ እንግሊዝ ፣ አሜሪካ ፣ ስፔን እና ኢራን ናቸው። ከዚህ ቀደም በእገዳው ውስጥ ያልተካተተችው #ፈረንሳይ እገዳው ተጥሎባታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሩሲያ የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ሞት ሪፖርት አደረገች። ሞስኮ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው እንዳለፈ የተነገረው የሰባ ዘጠኝ (79) ዓመት አዛውንት ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኤርትራ 'ብሔራዊ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ' ፈተና ለ14,960 ተማሪዎች እየተሰጠ ይገኛል። ጅዳና ሪያድ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ይሰጥ የነበረው ፈተና በኮሮና ሳቢያ መሰረዙን የኤርትራ ብሔራዊ ፈተና ማዕከል ዳይሬክተር ብስራት ገብሩ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ እሸቴ በቀለ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ እና የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናዎች የጊዜ ሰሌዳ በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ስርጭት ስጋት ምክንያት እንደሚራዘም ትምህርት ሚኒስቴር መናገሩን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል። ሚኒስቴሩ ትክክለኛ የመፈተኛ ጊዜዎቹን ትምህርት ሲጀመር አሳውቃለሁ ብሏል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በአዲስ አበባ የውጭ አገራት ዜጎች ሲንቀሳቀሱ ኮሮና ቫይረስ [COVID-19] አመጣችሁብን ፣ በእናንተ ምክንያት ነው በቫይረሱ የተጠቃነው በሚል ነዋሪዎች ጥቃት እያደረሱ ነው" - የአሜሪካ ኤምባሲ

"ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የውጭ ሚድያ ጋዜጠኞችን ፎቶ በመለጠፍ "ኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የያዛቸው ናቸው" ተብሎ ሀሰተኛ መረጃ ሶሻል ሚድያ ላይ እየተለጠፈ ነው።" - ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በነገራችን ላይ ...

ከመዲናችን አዲስ አበባ አቅራቢያ በምትገኝ አንዲት ከተማ ውስጥ ከውጭ ሀገራት ዜጎች ጋር የሚሰራ የቲክቫህ አባል የታዘበውንም አካፍሎናል።

ላለፉት 5 ዓመታት ከውጭ ዜጎች ጋር መስራቱን የሚናገረው ይኸው የቤተሰባችን አባል ኢትዮጵያ ውስጥ ኮሮና ገባ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ አብሯቸው በሚሰራ የስራ ባልደረቦቹ ላይ መገለል፣ ዘለፋ፣ ስድብ፣ የሰውን ክብር የሚነኩ ድርጊቶች እየተፈፀሙባቸው እንደሆነ ነግሮናል።

እጅግ በጣም በሚያሳዝን መልኩ ደግሞ አንዳንድ ሰዎች የስራ ባልደረቦቹን በመንገድ ላይ በሚሄዱበት ወቅት 'ኮሮና' እያሉ ሲጠሯቸው እንደታዘበ ገልጾልናል።

ሰዎች ከእንግዲህ ያለ የወረደ ተግባር እንዲቆጠቡ መልዕክት አስተላልፉንኝ ያለን ይኸው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል፤ እንዚህ ሰዎች በብዙ መልኩ እየረዱን ያሉ ታታሪ ሰራተኞች ስለሆኑ ክብራቸውን የሚነኩ ሰዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲል መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኮሮና ቫይረስ ምላሽ ለመስጠት በመላው ኢትዮጵያ ያለመታከት እየሰሩ ነው ላሏቸው የጤናና የህብረተሰብ ጤና ባለሙያዎች እና የድጋፍ ሰጬ ሰራተኞች ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሃሌሉያ አጠቃላይ ሆስፒታል፦

ሃሌሉያ አጠቃላይ ሆስፒታል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መልዕክት ዛሬ ጥዋት ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የሰራው ዜና ሀሰተኛ እና ከእውነት የራቀ ነው ብሏል። ሆስፒታሉ የሙቀት ልየታ እያደድረግ እንደሚገኝ ከመግለፅ በዘለለ ሬድዮ ጣቢያው ለህዝብ እንዲሰራጭ ያደረገው መረጃ ስህተት እንደሆነ አስገንዝቧል። ሆስፒታሉ ፥ ህዝቡም ይሄን ይወቅልኝ ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ራዲሰን ብሉ ሆቴል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መልዕክት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሆቴሉ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ እንዳለ ተደርጎ የሚነዛው ወሬ ሀሰተኛ መሆኑን አሳውቋል።

#SHARE #ሼር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በየአካባቢው ያልተቋረጡት ስብሰባዎች፦

ዛሬ የተለያዩ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ የፌስቡክ ገፆችን ዞር ዞር እያልን እየተመለከትን ነበር፤ የብልፅግና ፓርቲ እንዲሁም ሌሎች ስብሰባዎች እየተደረጉ እንደሆኑ ይገልፃሉ። በአንድ በኩል ህዝቡ ከመጠጋጋት እንዲቆጠብ መልዕክት እየተላለፈ፣ በሌላ በኩል መሰል ብዙ ሰዎች የተሰበሰቡበት ስብሰባዎችን እየተመለከትን ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
«አፍሪቃ ለክፉ ቀን መዘጋጀት አለባት» - ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

«አፍሪቃ ለክፉ ቀን መዘጋጀት አለባት» ሲሉ የዓለም የጤና ድርጅት ዳሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም የኮሮና ወረርሽን በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጨ መሆኑን አስጠንቅቀዋል።

ዶክተር ቴድሮስ ትላንት በሰጡት መግለጫ «አፍሪቃ ንቂ» አህጉሬ ንቂ» ሲሉ አፅዕኖት ሰጥተውም አሳስበዋል። 116 ታማሚዎች ላይ ተህዋሲውን ባረጋገጠችው ደቡብ አፍሪቃ ስድስት እድሜያቸው ከ 10 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ይገኙበታል።

ከ54ቱ የአፍሪቃ ሀገራት 30ዎቹ በተህዋሲው የተያዙ ሰዎች እንዳሉ ያረጋገጡ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ ጋምቢያ፣ ዛምቢያ እና ጅቡቲ እንዲሁ የመጀመሪያ ያሉትን ሰው አግኝተዋል።

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሀሌሉያ ሆስፒታል እያደረገ ያለው ዝግጅት፦

- የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሙቀት ልየታ እያደረገ ነው። ወደ ሆስፒታሉ የሚመጡ ሁሉም ተገልጋዮች እና የሆስፒታሉ ሰራተኞች በዚሁ የሙቀት ልየት እንዲያልፉ እየተደረገ ነው።

- የሙቀት ልየታ ስራው እየተሰራ ያለው የሆስፒታሉ መግቢያ በሮች በሙሉ ተዘግተው በተዘጋጁ ድንኳኖች ውስጥ ነው፤ ይህን ስራ የሚከውኑትም የሰለጠኑ ባለሙያዎች ናቸው። በተጨማሪ ወደ ውስጥ የሚገቡ ሰዎች የእጃቸውን ንፅህናም እንዲጠብቁ ይደረጋል።

- 400 ለሚሆኑ የሆስፒታሉ ሰራተኞች በሽታውን መከላከል በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎች ሰጥቷል። ለሰራተኞቹ የመከላከያ መሳሪያዎችን ሰጥቷል።

- በሆስፒታሉ በሙቀት ልየታ ምርመራ የሚለዩ እና የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ምልክቶች የሚታዩባቸውን ሰዎች ለይቶ ማቆያ ክፍልም አዘጋጅቷል።

#HallelujahGeneralHospital
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
- በስፔን በ24 ሠዓት ውስጥ የ169 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 767 ደርሰዋል።

- በኢራን በ24 ሰዓት ውስጥ የ149 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 1284 ደርሰዋል።

- በጣሊያን በ24 ሰዓት ውስጥ የ475 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል። በሃገሪቱ በቫይረሱ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 3 ሺህ ተጠግቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዶ/ር ሊያ ታደሰ መልዕክት፦

"የኮሮና ቫይረስ በሽታ ዘር ቀለም እና ሃይማኖት የለውም። ከየትኛውም ሃገርና እና ዜግነት ጋር አይገናኝም። በሽታው በሁላችንም ላይ የመጣ የጋራ ፈተና ነውና ይህንን አስቸጋሪ ጊዜ በመተባበርና በመረዳዳት በፍፁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ልናሳልፍ ይገባል።"

#SHARE #ሼር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ያልተገቡ ድርጊቶች ሊቆሙ ይገባል!

"ኤፍሬም እባላለሁ የቴክቫህ ቤተሰብ ነኝ ፤ ስራዬ የቱር ሹፌርና ጋይድ ነኝ በስራዬ ብዙ ነገሮች ቢያጋጥሙኝም ያሁኑ ትንሽ ለየት ያለና ከስብእና ውጪ አልፎም ከኢትዬጽያዊነት ስነ ምግባር ውጪ የሆነ ተግባር እያየሁ ነው። ቱሪስቶች እየተዘለፋና እየተሰደቡ ከነሱም አልፎ እኛንም እየተናገሩን ይገኛል፤ ኮሮና ያመጣችሁብን ምትገሉን እናንተ ናችሁ ሂዱልን አትቅረቡን እየተባሉ ይገኛል፤ ለህብረተሰቡ በተቻለ አቅም ከዚህ አይነት አስተሳሰብ እንዲወጡ የተቻለንን ብናደርግ ስል እመክራለሁ!"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia