TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

በአዲስ አበባ ከተማ የቤንዚን ነዳጅ እጥረት #እንዲከሰት እና #እንዲባባስ በሚያደርጉ ነዳጅ #አቅራቢዎች እና አከፋፋዮች ላይ አስፈላጊውን #ክትትል እያደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ በቂ ነዳጅ እያለ ነገር ግን በአዲስ አበባ ከተማ የቤንዚን እጥረት እንዲከሰት እና እንዲባበስ በመደረጉ ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ያካተተ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር ኢንጂነር ታከለ ኡማ የሚመራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ስራ መጀመሩ ይታወቃል፡፡

በከተማችን ነዳጅ ለማከፋፈል 120 ገደማ የሚሆኑ የነዳጅ ማደያዎች በህግ አግባብ ፈቃድ መውሰዳቸው እየታወቀ 106ቱ ብቻ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ጥር 8 ቀን 2011 ዓ/ም በስራ ላይ ከሚገኙ 106 የነዳጅ ማከፋፈያዎች መካከል 100 ማደያዎች ላይ በተደረገው ክትትል 54ቱ በቂ የቤንዚን እና የናፍታ፣ 5ቱ የቤንዚን ብቻ፣ 8ቱ የናፍታ ክምችት ያላቸው ሲሆን 30 ማደያዎች ደግሞ ነዳጅ ማራገፍ ሲገባቸው ያላራገፉ በመሆኑ፣ ቀሪዎቹ ሙሉ ለሙሉ ዝግ ሲሆን አንዳንዶች ለእረጅም ጊዜ አገልግሎት መስጠት በማቆማቸው ጊዚያዊ የቤንዚን እጥረት መከሰቱን ኮሚሽኑ አረጋግጧል፡፡

እጥረቱን ለማባባስ ልዩ ልዩ ምክንያች እንዳሉ በተደረገው ክትትል ማወቅ ሲቻል አንዳንድ የማደያ ሰራተኞች ከህገ-ወጦች ጋር በመተባበር ነዳጅ በተለይ ደግሞ ቤንዚን በበርሜል በመገልበጥ፣ በሞተር ብሰክሌትና በሌሎች ተሽከርካሪዎች ከስፍራ ወደ ስፍራ በማጓጓዝ በጥቁር ገበያ በከፍተኛ ዋጋ ሲሸጡ እንደተደረሰባቸው፣ እንዲሁም ሌሎች ሆን ብለው ነዳጅ በመደባቅ፣ ነዳጅ እያላቸው ለምሳና ለእራት ወጥተናል በሚል ሰበብ በመፍጠር ፣ የተወሰኑ ደግሞ 24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት ሲገባቸው ያለበቂ ምክንያት በመዘጋታቸው የማደል ስራው እንዲስተጓጎል እያደረጉ መሆኑን ፖሊስ ገልፆ እጥረቱን ምክንያት በማድረግ በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ህገ-ወጥ የሆነ የዋጋ ጭማሪ መደረጉን ደርሶበታል፡፡

ህጋዊ ፈቃድ ወስደው ያለበቂ ምክንያት አገልግሎት የማይሰጡ ማደያዎች በአስቸኳይ ስራቸውን እንዲጀምሩ እንዲሁም በጥቁር ገበያ ነዳጅ በህገ-ወጥ መንገድ በመሸጥ ላይ ያሉ ከህገ-ወጥ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ኮሚሽኑ አሳስቦ ነገር ግን ማሳሰቢያውን ተግባራዊ በማያደርጉ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመሆን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ኮሚሽኑ ከላከው ዘገባ መረደት ተችሏል፡፡

መንግስት በልዩ ልዩ ምክንያት የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት ለማረጋጋት በቂ ነዳጅ ወደ አዲስ አበባ እያስገባ በመሆኑ ከነዳጅ ጋር ተያይዞ ለሚያጋጥሙ ህገ-ወጥ ተግባራት ጥቆማ ለመስጠት ነፃ የስልክ መስመር 991 ወይም 01-11-11-01-11 መጠቀም እንደሚቻል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስተውቋል፡፡

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia