TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኦነግ⬆️

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ አመራሮች መስከረም 5/2011 አዲስ አበባ እንደሚገቡ የኣቀባበል ኣስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

ለኦነግ አመራሮች ከቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ጀምሮ ኣቀባበል እንደሚደረግላቸው ኣስተባባሪ ኮሚቴው ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ኮሚቴው እንዳለው በዚያው ዕለት ለኦነግ አመራሮችና ከውጭ ለሚመጣው የኦነግ ሰራዊት #በመስቀል አደባባይ ልዩ ኣቀባበል ይደረግላቸዋል፡፡

በአቀባበል ስነስርኣቱ ላይ የኦሮሞ ህዝብ ከአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጭ #በብዛት ይሳተፋል ብሏል ኮሚቴው፡፡

#ኦነግ በቻርተር ጊዜ የተዘጋብኝን #ጉላሌ ያለውን ቢሮዬን ኣድሼ መቀመጫዬን አዲስ አበባ ኣደርጋለሁ ብሏል፡፡

ከሌሎች የኦሮሞ ፖሊትካ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እንዳለው ገልፆ፤ ከኦሮሞ ፌዴራልስት ኮንግረስ ጋር #ጥምረት ለመፍጠር ውይይት ላይ ነኝ ብሏል፡፡

©OMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia