TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert

ከሰኔ 15 ጥቃት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በማረፊያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ብርጋዲዬር ጄኔራል ተፈራ ማሞ፣ ኮሎኔል አለበል አማረ እና ኮሎኔል ባምላኩ እያንዳንዳቸው በአስር ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቁና ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከራከሩ መወሰኑን የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል፡፡

Via #AMMA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention በደቡብ ወሎ ዞን "ቃሉ ወረዳ" የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በሰብል እና እንስሳት መኖ ላይ እያደረሰ ይገኛል። ጉዳዩ የሁሉንም ትኩረት ይሻል። #AMMA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
- ተጠርጣሪዎችን አፈላልጎ በመያዝ እርምጃ እንደሚወሰድ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ!

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ አስተዳደር በቤተ እምነት ተቋማት ላይ የደረሰው የቃጠሎ አደጋ በተመለከተ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በትናንትናው ዕለት ታኀሣሥ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡20 አካባቢ በሞጣ ከተማ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የእሳት ቃጠሎ መከሰቱን ተከትሎ በሌሎችም የሃይማኖት ተቋማት ላይ የእሳት ቃጠሎ መፈጸሙን ከዞኑ ፖሊስ መምሪያ ያገኙትን መረጃ ጠቅሰው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ማኅበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል መምሪያ ኃላፊ ጀማል መኮንን ተናግረዋል፡፡ በቡድን በመሰባሰብ መስጂዶች ላይ ጥቃት እንደተፈፀመ ነው ኮማንደር ጀማል የተናገሩት፡፡

በድርጊቱ በሞጣ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 03 የሚገኝ መስጂድ ሙሉ በሙሉ ሲቃጠል፣ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን እና ቀበሌ 05 እና 06 የሚገኙ መስጂዶች ደግሞ በከፊል እንደተቃጠሉና አንድ የገበያ ማዕከል በቃጠሎና በመሰባበር ጉዳት እንደደረሰበት ኮማንደር ጀማል መኮንን ተናግረዋል፡፡

በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ሪፖርት እንዳልተደረገም አመላክተዋል፡፡ ፖሊስ ችግሩን በማስቆም የማረጋጋት ሥራ እየሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ በቀጣይ ተጠርጣሪዎችን አፈላልጎ በመያዝ እርምጃ እንደሚወሰድም አስታውቀዋል፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች ሃይማኖትንና ማንነትን መሠረት አድረገው የሚነሱ ችግሮችን ኅብረተሰቡ ከማባባስ ይልቅ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር የማርገብና የማረጋጋት ልምድ ሊዳብር እንደሚገባ ኮማንደር ጀማል መኮንን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

https://telegra.ph/AMMA-12-21

#AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በደሴ ከተማ አስተዳደር ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ክፍሎች የተወጣጡ የእምነቱ ተከታዮች በሞጣ ከተማ በእምነት ተቋማት ላይ ደረሰው ጥቃት አሳፋሪ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የእምነቱ ተከታዮች በደሴ ከተማ በሚገኘው ዐረብ ገንዳ መስጂድ ባደረጉት ውይይት አጥፊዎቹ በሕግ ሊጠየቁ እንደሚገባም ጠይቀዋል፡፡ ጥቃቱ ከመድረሱ በፊትም ሆነ ከደረሰ በኋላ መንግሥት እያሳዬ ያለው ለዘብተኛ አቋም መታረም እንደሚገባውም አሳስበዋል፡፡

የክልሉ መንግሥት በመስጂዶች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንደሚደርስ መረጃዎች እንደነበሩት በማንሳትም ቅድመ መከላከል አልሠራም በሚል ወቅሰዋል፡፡ ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላም በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው ተጠርጣሪዎች ቁጥር አነስተኛ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

መንግሥት የተቃጠሉ ቤተ እምነቶችን እንዲሠራና የተዘረፉ ንብረቶችን እንዲመለሱ ማድረግ እንደለበትም ተናግረዋል፡፡ችግሩ እንዲባባስም ሆነ የቤተ እምነቶች እንዲቃጠሉ የሚዲያ አካላት ድርሻ ከፍተኛ እንደሆነም ነው ተወያዮቹ ያነሱት፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ሚዲያ አውታሮች በተለይ በመስጂዶች ላይ ጥቃት ሲደርስ የሚሰጡት ሽፋን ሚዛናዊ እንዳልሆና መታረም እንደሚገባውም መክረዋል፡፡ መንግሥት የተቃጠሉ ቤተ እምነቶችን እንዲሠራና የተዘረፉ ንብረቶችን እንዲያስመልስም አሳስበዋል።
#AMMA

#TIKVAH_ETH

በሞጣ ከተማ በእምነት ተቋማት ላይ የተፈፀመው ድርጊት የሚያወግዙ ሰልፎች በተለያዩ ከተሞች እና አካባቢዎች እንደተደረጉ መረጃዎች ደርሰውናል። በባሌ ደሎ መና በተካሄደ ሰልፍ የሙስሊሙ እና ክርስትያኑ ማህበረሰብ አባላት ድርጊቱን አደባባይ በመውጣት በጋራ አውግዘዋል። በተለያዩ ከተሞች እና አካባቢዎች የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎችን ማስፈንጠሪያውን በመጫን መመልከት ትችላላችሁ https://telegra.ph/TIKVAH-12-22

@tikvahethiopiaBot
ወደ ጎንደር 19 ተጨማሪ በረራዎች ተዘጋጅተዋል...

የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ - ጎንደር ተጨማሪ የበረራ መርሃ ግብሮችን ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ እስካሁን ድረስ ጥር 8/2012 ድረስ በአጠቃላይ ወደ ጎንደር የሚደረጉ 19 ተጨማሪ በረራዎች መዘጋጀታቸውን ነው አየር መንገዱ የገለፀው። ለጥምቀት በዓልና ተያያዥ ጉዳዮች በቀጥታ ወደ ጎንደር የሚያመሩ 2 ሺህ 500 የሚደርሱ መንገደኞች መመዝገባቸውም ተመላክቷል፡፡

#AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጥምቀት በዓል ታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ...

የጥምቀት በዓልን ጨምሮ ሌሎች ቅርሶችን በዓለም ቅርስነት ማስመዝገብ ብቻ ሳይሆን መንከባከብ እንደሚገባ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አሳስበዋል፡፡

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ በንግግራቸው መጀመሪያ ጎንደር ወጣቶች ለበዓሉ ድምቀት እያደርጉት ላለው ቀና ትብብር እና በጎ ፈቃደኝነት አመሥግነዋል፡፡ የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት በመመዝገቡ ማግስት ጎንደር ተገኝተው በማክበራቸው መደሰታቸውንም ፕሬዝዳቷ ገልጸዋል፡፡

#AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሜጀር ጀነራል ነስረዲን አብዲ ጎንደር ገብተዋል!

የገደሪፍ ዋና አስተዳዳሪ ሜጀር ጀነራል ነስረዲን አብዲ ለጉብኝት ጎንደር ገብተዋል። የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ማስተዋል ስዩም ለአስተዳዳሪው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

"ሜጀር ጀነራሉ ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ ሀገሬ ውስጥ ያለሁ ያህል ይሰማኛል" ብለዋል። በቆይታቸውም በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን ግንኙነት በሚያጠናክሩባቸው ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በወረታ ደረቅ ወደብ የመጀመሪያ ምዕራፍ ምረቃ ላይ አስተዳዳሪው የሚሳተፉ ይሆናል።

#AMMA
@tikvahethiopia @tikvahethioiaBot
ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ!

የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ሰፊ ክርክር ከተደረገ በኃላ ምክር ቤቱ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዲሆኑ የቀረበውን የፋንታ ማንደፍሮ/ዶ/ር/ን ሹመት አፅድቋል፡፡

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ የዕጩ ተሿማዎችን ለምክር ቤቱ አባላት ሲያቀርቡ እንዳሉት ወቅቱን የዋጀ በዕውቀት ላይ የተመሠረተ አመራር ለመስጠትና ኃላፊነትን በአግባቡ ለመወጣት የሚጠይቅ ወቅት ላይ በመሆናቸው ሹመቱ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

#AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዐብይ ፆም ወቅትን በተመለከተ መግለጫ ተሰጠ!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበር ተክለሃይማኖት አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ የዐብይ ጾም ወቅትን አስመልከቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ብጹእነታው በመግለጫቸው እንዳሉት ምዕመናን የዘንድሮውን ጾም ሲከውኑ ከጥላቻ እና ቂም ራሳቸውን በማራቅ እና በጾም ወቅት ከጥላቻና ዛቻ፣ ከበቀልና ተንኮል ርቀው መሆን አንዳለበት አሳስበዋል፡፡

‹‹እጃችንም፣ እግራችንም፣ አፋችንም ዓይናችንም፣ ጆሯችንም፣ ውስጣችንም በመንፈሳዊ ሕይወት አሸብርቀን መጾም ይገባናል፡፡ በዚህ ወቅት መስማትና ማዳመጥ ያለብን እግዚአብሔርን ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ድምጽ ፍቅርና ሠላም በመሆኑ አንድነትና ስምምነት፣ ዕርቅና ይቅርታ ፍትሕና እውነት፣ እኩልነትና ኅብረት በማድረግ ለሀገር ሠላም በመጸለይ ሊሆን ይገባል›› ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ሁኔታ እንድትወጣ ምዕመኑ በጾምና ጸሎት በአንድ ልቦና ለሀገሩ ሠላም እና ዕድገት፣ ፍትሕ እና እውነት በመቆም ጾሙን መከወን እንደሚገባቸውም ብጹእነታቸው አሳስበዋል፡፡

#AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ADDISABABA

‹‹የአማራ አብሮነት እሴቶች ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነት›› በሚል መሪ ሐሳብ የተለያዩ አካላት በተገኙበት በአዲስ አበባ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

የአማራ ክልል የበይነ መንግሥታት ቢሮ ኃላፊ ደስታ ተስፋው (ዶክተር) ‹‹አማራ የመቻቻልና የመከባበር እሴት ያለው አቃፊ ሕዝብ ነው፤ እውነታው ይህ ቢሆንም በተዛቡ ትርክቶች ምክንያት እንደጨቋኝ መታየቱ ተገቢ አይደለም›› ብለዋል፡፡

ዶክተር ደስታ አብሮነት እና ጠንካራ ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት ለመፍጠር መሠራት እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

በመድረኩም የአማራ የአብሮነት እሴቶችና ተሞክሮዎች፣ የተሳሳቱ ትርክቶች ያስከተሏቸው ችግሮችና የመፍትሔ ሐሳቦች ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡

#AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19 #ETHIOPIA #AMHARA_REGION

የኮሮና ቫይረስ ወደ አማራ ክልል መግባት የሚችልባቸው አጋጣሚዎች መኖራቸውን በአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ባለሙያ አቶ አሞኘ በላይ ለአብመድ ተናገሩ፡፡ አማራ ክልል ሰፊ የቱሪዝም እንቅስቃሴ ያሉበት በመሆኑ በርካታ የውጪ ሀገር ቱሪስቶች ወደ ክልሉ ይገባሉ፡፡

ምንም እንኳን በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የቫይረሱ ምርመራ ቢደረግም በባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ላልይበላ እና ኮምቦልቻ የአውሮፕላን ማረፊያዎች በኩል የመግባት ዕድል ሊኖረው እንደሚችል በኢንስቲቲዩቱ ታሳቢ ተደርጓል፡፡

የተለያዩ የውጪ ሀገር ዜጎች የሚሠሩባቸው ካምፖች ፣ ኢንዱስትሪዎች እና ክልሉን በሚያዋስነው የሱዳን ድንበር ያለው የምድር ትራንስፖርት ኮሮና ቫይረስን [COVID-19] ወደ ክልሉ እንዲገባ ምክንያት ሊሆኑ እንደሚችሉ በስጋትነት ተለይተዋል፡፡

ይህንን ታሳቢ በማድረግ ኢንስቲቲዩቱ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ባለሙያው አስታውቀዋል። በተለዩት ቦታዎች የቫይረሱን ምንነት እና ቢከሰት መከናወን ያለባቸውን ተግባራት አስመልክቶ ለባለሙያዎች ሥልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝም አቶ አሞኘ አስታውቀዋል፡፡

#AMMA

[በአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

በካሜሮን ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መገኘቱን የሀገሪቱ መንግሥት ገልጿል፡፡ የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ዛሬ ዓርብ የካቲት 27/2012 ዓ.ም ነው የመጀሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መገኘቱ የተረጋገጠው፡፡

ቫይረሱ የተገኘበት ግለሰብ የፈረንሳይ ዜግነት ያለው የ58 ዓመት ጎልማሳ ነው፡፡ ግለሰቡ ካሜሩን መዲና ያውንዴ ከገባ በኋላ የቫይረሱ ተጠቂ መሆኑ ሲረጋገጥ በቀጥታ ወደ ለይቶ ማቆያ ገብቶ በከተማው ማዕከላዊ ሆስፒታል ሕክምና እየተከታተለ መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

#CGTN #AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ረጃጅም የነዳጅ ሰልፎች...

ዛሬ ጥዋት የሀዋሳ ከተማ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በከተማው የነዳጅ እጥረት ማጋጠሙን ሪፖርት አድርገዋል።

ላለፉት ቀናት በሀዋሳ ከተማ ነዳጅ ለማግኘት ፈተና ሆኗል፤ በከተማው ረጃጅም የሞተር እና የመኪና ሰልፎች አሉ ብለዋል።

ነዳጅ ለማግኘት መጉላላት እና የስራ መስተጓጎል የየእለት የህይወታችን አንዱ ክፍል ከሆነም ሰንብቷል ሲሉ አማረዋል።

በተመሳሳይ ነዳጅ ለማግኘት በመሰለፍ በሚያጠፉት ጊዜ በአማካይ እስከ 150 ብር እንደሚያጡ በባሕር ዳር አብመድ ያነጋገራቸው የባጃጅ አሽከርካሪዎች ገልፀዋል፡፡

እናተስ የት ከተማ ይህ ችግር አጋጠማችሁ?

#AMMA #TikvahFamilyHawassa
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ዛሬ ማምሻውን መግለጫ ሰጥቷል። በዚህም ተከታዮቹ መመሪያዎች ተፈፃሚ እዲሆኑ አዟል፦

- የመዝናኛ ቤቶችና መጠጥ ቤቶች ከነገ መጋቢት 15/2012 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲዘጉ፣
- ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ፣
- ሰርግን ጨምሮ ተያያዥ ማኅበራዊ ግንኙነቶች እንዲቆሙ፣
- የተሽከርካሪ ባለቤቶች ከመደበኛ የመጫን ልካቸው በግማሽ እንዲቀንሱ፣
- የፓርቲም ሆነ የመንግሥት ስብሰባዎች እንዲቆሙ፣
- ለሌሎች ማኅበራዊ መስተጋብሮች እንዲቀንሱ፣
- ሰዎች ወደ ግብይት ማዕከላት አዘውትረው እንዳይሄዱ፣

#AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሺሻ፣ ጫትና ፑል ቤቶች ላይ ርምጃ ተወሰደ!

በሰቆጣ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ወረርሽኝን ለመከላከል የሺሻ፣ ጫትና ፑል ቤቶች ላይ ርምጃ መወሰዱን የወረርሽኝ መከላከል ግብረ ኃይሉ ገልጿል።

#AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ኅብረተሰቡ አቅም ለሌላቸው ወገኖች ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል!

የጎዳና ተዳዳሪዎች እንዲሁም አቅመ ደካማ ወገኖች ለርሃብ እንዳይጋለጡ ኅብረተሰቡ በሚችለው ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርግ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር መሐሪ ታደሰ ጥሪ አቅርበዋል።

የመኝታ ፍራሽና ብርድ ልብስ ፣ አልባሳት ፣ እንደ ማካሮኒ ፣ ፓስታ ፣ ዱቄት ፣ ሩዝ ያሉ የምግብ ዓይነቶችን 'ሙሉ ዓለም የባሕል ማዕከል' በሚገኘው ጊዜያዊ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ቦታ ማድረስ ይቻላል።

#AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በፈረንሳይ በሆስፒታል ያሉ ታማሚዎች ቁጥር በእጅጉ እቀነሰ ነው። ባለፉት 24 ሰዓት 367 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 23,660 ደርሷል።

- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት 586 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 21,678 ደርሷል።

- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 2,091 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 382 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

- በሩሲያ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ከቻይናና ኢራን በልጧል። ባለፉት 24 ሰዓት 6,411 ሰዎች በቫይረሱ መያቸውን ተከትሎ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 93,558 ደርሰዋል።

- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ58,000 በላይ ሆኗል።

- በሩዋንዳ 5 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 212 ደርሷል። በሌላ በኩል 2 ተጨማሪ ሰዎች ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 95 ደርሰዋል።

- በግብፅ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 5,042 ደርሰዋል። ባለፉት 24 ሰዓት 260 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በተጨማሪ 22 ሰዎች መሞታቸው ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 359 ደርሷል።

- በደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 4,996 ደርሰዋል። ባለፉት 24 ሰዓት 203 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

- ትላንት የኬንያ መንግስት የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተናዎች መስጫ ጊዜያት እንደማይራዘም አሳውቋል ፤ የዚህ ዓመት የብሔራዊ ፈተናዎች በመርሀ ግብሩ መሠረት የሚሰጡ ይሆናል፡፡ በትምህርት መርሀ ግብሩ ያልተሸፈኑ ይዘቶች በፈተናዎቹ አይካተቱም ተብሏል - #AMMA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
16 የኮቪድ-19 ታማሚዎች እየተፈለጉ ነው! በሰሜን ሸዋ ዞን የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 22 ሰዎች መካከል አስራ ስድስት (16) ሰዎች እየተፈለጉ መሆኑን መምሪያው አስታውቋል፡፡ የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ኬዝ ቲም አስተባባሪ አቶ አውላቸዉ ታደሰ ለአብመድ እንደተናገሩት በ79 ሰዎች ላይ ምርመራ ተደርጎ 22 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ አስተባባሪ…
#UPDATE

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) እንዳለባቸው ተረጋግጦ ሲፈለጉ ከነበሩት አሽከርካሪዎች መካከል 15 መገኘታቸውን የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ አስታውቋል፡፡

ኮቪድ-19 ተገኝቶባቸው ወደ ለይቶ ማከሚያ ያልገቡትን አሽከርካሪዎች እና ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የማፈላለጉ ሥራ መቀጠሉን ጤና መምሪያው አስታውቋል፡፡

ከተገኙት 15 አሽከርካሪዎች ውስጥ አስራ ሁለቱ (12) ወደ ደብረ ብርሃን ለይቶ ማከሚያ ማዕከል እና ሦስቱ ደግሞ አዲስ አበባ ወደ ሚገኝ ለይቶ ማከሚያ ማዕከል እንዲገቡ ተደርገዋል፡፡

አንድ (1) የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) እንዳለበት የተረጋገጠ አሽከርካሪ ተንቀሳቃሽ ስልኩ ጥሪ ባለመቀበሉ እስካሁን እንዳልተገኘ እና ፍለጋው መቀጠሉንም ጤና መምሪያው አስታውቋል - #AMMA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 960 ኪ.ግ የሚመዝን አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

ነሐሴ 18/2012 ዓ.ም ከጧቱ 2 ሰዓት ገደማ ከአዲስ አበባ ወደ ባሕርዳር አቅጣጫ ይጓዝ የነበረ ሰሌዳ ቁጥሩ አ.አ 30276 የሆነ አይሱዙ የጭነት ተሸከርካሪ አደንዛዥ እፅ ጭኖ ሲንቀሳቀስ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ሊያዝ ችሏል።

ተጠርጣሪው ተሸከርካሪውን አቁሞ ለጊዜው ከአካባቢው የተሰወረ ሲሆን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እየተደረገ ይገኛል።

የአደንዛዥ እፁ ምንነት ለጊዜው በውል ባለመታወቁ በምርመራ ለመለየት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ተነግሯል።

ከ አደንዘዥ እፁ ጋር አብሮ የአትክልት እና ፍራፍሬ ፣ 43 ኩንታል የእንስሳት መኖ፣ አብሮ በመጫን ለሽፋን ቢጠቀሙም ለፖሊስ በተደረገ ጥቆማ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው #AMMA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ !

- የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ፣ በተገኙበት ዛሬ በይፋ ተመርቋል።

- ኢንዱስትሪ ፓርኩ ለሀገራችን አሥራ ሦስተኛ ፣ ለአማራ ክልል ደግሞ ሦስተኛ ነው።

- በአሁን ሰዓት ኢንዱስትሪ ፓርኩ 8 የተሟላ ቁሳቁስ ያላቸውን የማምረቻ ቦታዎች የያዘ ሲሆን ፣ በቅርቡ ሥራ ይጀምራሉ።

- የመጀመሪያ ምዕራፍ የኢንዱስትሪ ፖርክ 75 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን 2ኛው ምዕራፍ የኢንዱስትሪ ግንባታ 125 ሄክታር መሬት ላይ ያርፋል ተብሏል።

- ፓርኩ በቅርቡ ከ4,000 በላይ ሠራተኞችን ለመቀበል ልየታ ሰርቷል። በሙሉ አቅሙ በ2 ፈረቃ ሲሠራ 10 ሺህ ለሚደርሱ ሰዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል።

- በአካባቢው ለነበሩ የልማት ተነሺዎች ቅድሚያ የሥራ ዕድል ይሰጣል ተብሏል።

- በፖርኩ እስካሁን ‘ሆፕሉን’ የተባለ ኩባንያ ለጨርቃ ጨርቅ እና ጋርመንት ምርት 8 ሼዶችን ወስዷል። በ1 ሼድ ላይ መሣርያ የገጠመ ሲሆን ሠራተኞችን እያሰለጠነ ይገኛል። ከመጪው መጋቢት ጀምሮ ምርቶቹን ወደ አሜሪካና አውሮፖ ኤክስፖርት ማድረግ ይጀምራል።

#DrAbiyAhmed #AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia