TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቪድዮ : የቀድሞ የአሜሪካ ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ የግድያው ሙከራ በተደረገባቸው ወቅት እሳቸው ቅስቀሳ ከሚያደርጉበት ስፍራ በቅርብ ርቀት በሚገኝ ጣሪያ ላይ የነበሩ የ " ሴክሬት ሰርቪስ " የስናይፐር ተኳሾች የግድያ ሙከራውን ባደረገው ሰው ላይ ምላሽ ሲሰጡ ታይተዋል።

አንድ ተቀርጾ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ ቪድዮ ሁለት የሴክሬት ሰርቪስ ስናይፐር ተኳሾች በፍጥነት ኢላማ አድርገው የግድያ ሙከራ ባደረገው ግለሰብ ላይ የተኩስ መልስ ሲሰጡ ተስተውሏል።

ግለሰቡ የግድያ ሙከራ ባደረገ በሰከንዶች ውስጥ መተገው ገድለውታል።

የግድያ ሙከራውን ያደረገው ማነው ?

- FBI የግድያ ሙከራውን ያደረገው ቶማስ ማቲው የተባለ #የ20_ዓመት_ወጣት እንደሆነ ገልጿል።

- ነዋሪነቱ ምርጫ ቅስቀሳውና የግድያ ሙከራው ከተደረገበት ስፍራ የአንድ ሰዓት ጉዞ የሚፈጅ ቦታ ነው።

- በ2022 ነው ቤተል ፓርክ ከተባለ ሀይስኩል የተመረቀው።

- ወጣቱ በብሔራዊ የሒሳብ እና ሳይንስ ኢኒሼቲቭ ተሸላሚም ነበር።

- የሪፐብሊካን ደጋፊም ጭምር እንደሆነ ተመዝግቧል (የዶናልድ ትራምፕ ፓርቲ ማለት ነው)።

- ቅስቀሳው ከሚደረግበት ቅርብ ርቀት በሚገኝ ጣራ ላይ ሆኖ ነው ዶላንድ ትራምፕን ለመግደል የሞከረው።

- ለምን ይህን ለማድረግ እንደፈለገ FBI ምርመራ እያደረገ ነው።

#USElection #FBI

@tikvahEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#US ነገ በአሜሪካ ከሚደረገው ኦፊሴላዊ የድምፅ መስጫ በፊት ባሉት ጥቂት ቀናት ብቻ ከ78 ሚሊዮን በላይ ሰዎች " ለሀገራችን ይሆናታል ፣ ይበጃታል " ያሉትን መርጠዋል። አሜሪካ እና ዜጎቿ በዓለም ከሚታወቁባቸው ጉዳዮች አንዱ የምርጫ ስርዓታቸው ነው። የሀገሪቱ ዜጎች በምርጫ ጉዳይ ቀልድና ፌዝ አያውቁም ምክንያቱም የነገ ዕጣፋንታቸው የሚወስነበት ስለሆነ። ለዚህ ነው በነቂስ እየተሳተፉ " ይሆነናል…
#USElection

አሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ይገኛል።

ዶናልድ ትራምፕም በበርካታ ግዛቶች ድል ቀንቷቸው ምርጫውን እየመሩ ይገኛሉ።

የአሜሪካ ምርጫ ውጤት የሚታወቀው መቼ ነው ?

የምርጫ አሸናፊ በድምፅ መስጫው ምሽት ፣ አሊያም በነጋታው ካልሆነ ደግሞ ከቀናት ወይም ከሳምንታት በኋላ ሊታወጅ ይችላል።

ያለፈው ምርጫ በአውሮፓውያኑ 2020 ማክሰኞ ኅዳር 3 ነው የተደረገው። ነገር ግን ጆ ባይደን አሸናፊ መሆናቸው የተሰማው ቅዳሜ ኅዳር 7 ቀን ነበር።

በወቅቱ አብዛኞቹ ግዛቶች ድምፅ በተሰጠ በ24 ሰዓታት ውስጥ ውጤት ቢያሳውቁም በአንዳንድ ግዛቶች ላይ ቆጠራው ቀናትን ወስዷል።

በ2016 ዶናልድ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው ሲመረጡ ውጤት የታወቀው ከድምፅ መስጫው ቀጥሎ ባለው ቀን ነበር።

በ2012 ደግሞ ባራክ ኦባማ ለሁለተኛ ጊዜ ፕሬዝደንት ሆነው ሲመረጡ ውጤቱ ይፋ የተደረገው በድምፅ መስጫው ቀን እኩል ለሊት ገደማ ነው።

ነገር ግን በ2000 በጆርጅ ደብሊው ቡሽ እና አል ጎር መካከል የተደረገው ምርጫ ከሌሎቹ ለየት ይል ነበር።

ዕጩዎቹ የነበራቸውን ጠባብ ውጤት ተከትሎ ድምፅ ድጋሚ እንዲቆጠር ቢታዘዝም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጣልቃ በመግባት በግዛቲቱ በውጤት እየመሩ የነበሩት ቡሽ አሸናፊ እንዲሆኑ ወስኗል።

ቁልፍ ግዛቶች የትኞቹ ናቸው ?

የአሜሪካ ምርጫ ውጤት የሚወሰነው በጥቂት ግዛቶች በሚገኝ ድምፅ ነው።

ለዚህ ምክንያቱ ኢሌክቶራል ኮሌጅ የተባለው ሥርዓት ነው። ይህ ማለት አሜሪካ ፕሬዝደንቷን የምትመርጠው ዕጩዎች በሚያሸንፉት ግዛት መሠረት ነው። አብዛኛዎቹ ግዛቶች ዲሞክራት አሊያም ሪፐብሊካን ናቸው።

ዘንድሮ በጣም ወሳኝ የሚባሉት ግዛቶች ሰባት ናቸው። እነሱም ፦
° አሪዞና፣
° ጆርጂያ፣
° ኔቫዳ፣
° ኖርዝ ካሮላይና፣
° ዊስኮንሲን፣
° ፔንስሊቪኒያ እና ሚሸጋን ናቸው።

ድምፅ የሚቆጠረው እንዴት ነው ?

ብዙውን ጊዜ ቅድሚያ የሚሰጠው በምርጫው ቀን ለሚሰጡ ድምፆች ነው። ቀጥሎ ከድምፅ መስጫው ቀን በፊት የመረጡ እና በፖስት ድምፃቸውን ያስገቡ ሰዎች ቆጠራ ይካሄዳል።

ከውጭ ሀገራትና ከወታደራዎ ካምፖች የሚላኩ እንዲሁም ድጋሚ እንዲቆጠሩ የተደረጉ ድምፆች ይከተላሉ።

የአካባቢ የምርጫ ባለሥልጣናት አንዳንዶቹ የተሾሙ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ተመርጠው የመጡ ናቸው። እነዚህ የምርጫ አስተባባሪዎች ናቸው።

አስተባባሪዎች የተሰጠውን ድምፅና የተመዝጋቢዎችን ቁጥር ያመዛዝናሉ፤ መረጃዎችን ያጣራሉ፤ ጉዳት የደረሰባቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን ይፈትሻሉ፤ አለመመሳሰል ካለበት ደግሞ ምርመራ ያደርጋሉ።

ወረቀቶቹ ወደ ኤሌክትሮኒክ ሥርዓት ገብተው ውጤታቸው እንዲቆጠር ይደረጋል።

አንዳንዶቹ ድምፆች በእጅ ሊቆጠሩ ይችላሉ።

ድምፁ ትክክለኛ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ መጀመሪያ በክፍለ-ግዛት ቀጥሎ ወደ ግዛት ይሸጋገራል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia