TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

" ከቅጣት በኋላ ካላስተካከሉ የማሸግ እንዲሁም ከዚህ አለፍ ሲል ከዘርፉ እስከማሰናበት እርምጃ ይወሰዳል " - በአ/አ ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ

በአዲስ አበባ የሚገኙ ሆቴሎች እና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተጋጆቻቸውን " የተራቆተ " ልብስ የሚያስለብሱ ከሆነ ከ50 ሺህ ብር እስከ #እገዳ የሚደርስ ቅጣት የሚጥል ረቂቅ መዘጋጀቱ ታውቋል።

የረቂቁ ስያሜ ፦ " በሆቴል እና መሰል አገልግሎቶች ሰጪ ተቋማት የሚሠሩ ባለሙያዎች የደንብ ልብስ አለባበስ፣ የጌጣ ጌጥ እና የመዋቢያ አጠቃቀም ደንብ " ይሰኛል።

የተዘጋጀው ፦ በአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ነው።

በተለይም እንደ #ሥጋ_ቤቶች ባሉ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ በታየው የአስተናጋጆች " የተራቆተ አለባበስ "  ምክንያት ረቂቁ ተዘጋጅቷል።

ረቂቁ ምን ያላል ?

- ከመስተንግዶ ስነምግባር እና ከሀገሪቱ ባህል የወጣ አለባበስ ይከለክላል።

-  አስተናጋጆች ከባህል፣ ከጨዋነት ያፈነገጠ እና የተራቆተ አለባበስ እንዳይኖራቸው ይከለክላል።

- አስተናጋጆች #በሚታይ የሰውነት አካል ላይ ንቅሳት እንዳይኖራቸው ይከለክላል።

- #ወንዶች በምንም ተአምር ጆሮ ጌጥ አድርገው እንዳያስተናግዱ አይፈቀድም።

-  የተቋማቱ ሠራተኞች ከሸሚዝ በላይ የሚሆን የአንገት ጌጥ እንዲሁም የእጅ ጌጥ እንዳይጠቀሙ ይከለክላል።

- ከጌጣ ጌጥ ጋር ተያይዞ ለሴቶች ጆሮ ጌጥ ይፈቀዳል። ነገር ግን ወደታች ያልወረደ እዚያው ላይ ልጥፍ የሚል መሆን አለበት። በተለይ በጆሮ ዙሪያ ላይ የሚደረግ ጆሮ ጌጥ አይፈቀድም።

- በሚታዩ የሰውነት አካላት ላይ . . . ምንም ዓይነት ንቅሳትም ሆነ ሌላም በሥዕል ተጠቅሞ ማስተናገድ አይቻልም። ይሁንና ከንቅሳት ጋር በተያየዘ የሚነሱ የባህል ጉዳዮች የደንቡን መጽደቅ ተከትሎ በሚወጣ መመሪያ ይታያል።

- ከአለባበስ፣ በሚታዩ የሰውነት አካላት ላይ ከሚደረጉ የጌጣ ጌጦች አጠቃቀም በተጨማሪ የፀጉር አያያዝን እንዲሁም የሚጠቀሟቸው ሽቶዎች መጠንን ላይ ገደብ ተቀምጧል።

ክልከላው እነማንን ይመለከታል ?

ሁሉንም ሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪዎችን ይመለከታል።

* ሆቴሎች፣
* ካፍቴሪያዎች፣
* ምሽት ቤቶች፣
* ማሳጅ ቤቶች፣
* ጂሞች
* የስቲም እና ሳውና አገልግሎት ሰጪዎች ክልከላው ከሚመለከታቸው ውስጥ ናቸው።

ቅጣትን በተመለከተ ረቂቅ ደንቡ ምን ይላል ?

ደንቡ ላይ የተቀመጠውን ድንጋጌ የሚተላለፉ ፦

በ15 ቀናት ውስጥ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸዋል።

በ15 ቀን ጊዜ ውስጥ ማስተካከያ ያማያደርጉ ከሆነ የ50 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል።

ከቅጣት በኋላም ካላስተካከለ የማሸግ እርምጃ ይወሰዳል። ከዚህ አለፍ ሲልም ከዘርፉ እስከማሰናበት እርምጃ ይወሰዳል።

መቼ ተግባራዊ ይደረጋል ?

ደንቡ ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው ለአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ቀርቦ ከጸደቀ በኋላ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ማግኘቱን ይገልጻል።

@tikvahethiopia