TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሞተር አልባ ትራንስፖርት በአዲስ አበባ...

የፊታችን እሁድ ወደ ስራ አንደሚገባ የተነገረው ከጀሞ እስከ ለቡ ያለው የብስክሌት ሞተር አልባ ትራንስፖርት መስመር  አገልግሎቱ በአዲስ መልክ ከሚጀመርባቸው መንገዶች አንዱ ሲሆን በአስር አመት ውስጥ ሊተገበር ከታሰበው የ100 ኪሎሜትር  እቅድ አካል ነው።

መንገዱ የተመረጠው በአካባቢው በተከታታይ ‹‹እንደመንገድ ለሰው›  ያሉ ከመኪና ነጻ ሁነቶች የተከናወኑበት፣ የብስክሌት ትራንስፖርት በብዛት ስለሚገኙበትና በአካባቢዎቹ አዳዲስ የመንገድ ፕሮጀክቶች እየተሰሩ በመሆኑ ነው።

በአ/አ ከለቡ እስከ ጀሞ ካለው መስመር በተጨማሪ ከቱሉ ዲምቱ - ቃሊቲ ፣ ከሃይሌ ጋርመንት - ጀሞ በቅርቡ የሞተር አልባ የትራንስፖርት አገልግሎት ከሚጀመርባቸው የከተማዋ ክፍሎች መካከል ናቸው፡፡ ረጅም ርቀት የሚታጠር የህንጻ ዲዛይን እንዳይኖር እና በየመሃሉ  የሞተር አልባ አቋራጭ መንገዶች እንዲሰሩ ለማደረግ መታሰቡም ተሰምቷል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እሳት ከሰማይ ወረደ-ኢትዮጵያ‼️ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በግራዋ ወረዳ ሙደና ጅሩ በሊና በምትባል የገጠር ቀበሌ ውስጥ ከአርብ ጥቅምት 25 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ከሰማይ በሚወርድ እሳት ከ40 በላይ የሳር ቤቶች #ተቃጠሉ፡፡ የአደጋውን መንስኤ ለማጥናት እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሆነና እስካሁን በደረሰው ቃጠሎ በንብረት ላይ ጉዳት ከማድረሱ ውጪ በሰው ህይወት መጥፋት እንዳልተከሰተ ከአካባቢው ያገኘነው…
ከሰማይ ወረደ የተባለ እሳት ቤቶች አቃጠለ!

ከሰማይ የወረደ እሳት በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጠምባሮ ወረዳ በአራት ቀበሌያት ውስጥ 30 የሳር ቤቶችን ማቃጠሉን የከምባታ ጠምባሮ ዞን ፖሊስ መምሪያ ገለፀ።

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር አብረሃም ቲርካሶ ለዞኑ ሕዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት እንደገለፁት በጠምባሮ ወረዳ ዱርጊ ፥ ሲገዞ ፥ ለዘንባራ እና ሆዶ ቀበሌያት ዓርብ ለቅዳሜ አጥቢያ ከሌሊቱ 7፡00 ጀምሮ ከሰማይ ወረደ በተባለ እሳት 30 በላይ የሳር ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን 6 የዳልጋ ከብቶች እና የጤፍ ክምርም የጉዳቱ ሰለባ ሆኗል።

የእሳቱ መንስዔ በግልጽ ባይታወቅም የአካባቢው ኅብረተሰብ በተመሳሳይ ሰዓት ከሰማይ ወርዶ ጉዳት እንዳደረሰ እና ተፈጥሯዊ ነው ብለው ከመናገር ውጭ ይህ ነው ብለው የሚያቀርቡት ነገር ባይኖርም ፖሊስ ግን የእሳቱን መንስኤ እና የጉዳት መጠኑን እያጣራ መሆኑን ኮማንደር አብረሃም ቲርካሶ ገልፀዋል።

[ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦች ከዚህ ቀደም በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በግራዋ ወረዳ ሙደና ጅሩ በሊና በምትባል የገጠር ቀበሌ ውስጥ ከሰማይ ወረደ በተባለ እሳት ከ40 በላይ የሳር ቤቶች መቃጠሉን የሚገልፅ መረጃ አጋርተናችሁ ነበር]

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እሳቱ ያደረሰው ጉዳት...

ከሰማይ ወረደ የተባለው እሳት በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጠምባሮ ወረዳ በአራት ቀበሌያት ውስጥ 30 የሳር ቤቶችን ማቃጠሉን የከምባታ ጠምባሮ ዞን ፖሊስ መምሪያ አሳውቋል። እሳቱ ያደረገሰውን ጉዳት ከላይ በፎቶ ተመልከቱ።

[የከምባታ ጠምባሮ ዞን ህዝብ ግንኙነት]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

አዲሱ የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ በነገው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ይፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በተጨማሪ ምክር ቤቱ የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመቆጣጠር የረቀቀውን ህግ ነገ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#update በኢንተር ኮንቲኔታል በተካሄደው የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር #ታከለ_ኡማ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ #ለባለእድለኞች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ልማትን በጋራ መጠቀም ተገቢ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው፣ በቤቶቹ ግንባታ ከይዞታቸው የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው ለከፈሉት #መስዕዋትነት ዋጋቸውን እንደሚያገኙም አመልክተዋል፡፡…
#UPDATE

ባለፈው ዓመት የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በኢንተር ኮንቲኔንታል አዲስ ሆቴል በቀድሞ የከተማ ልማት ሚኒስትር አቶ ጃንጥራር ዓባይና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር)፣ ዕጣ የወጣባቸው የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለዕድለኞች ለማስተላለፍ የፌዴራል መንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ዕጣው በወጣበት ማግሥት በተለይ በርካታ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በተገነቡበት ኮዬ ፈጬ ሳይት፣ ‹ቤቶቹ የተገነቡት በኦሮሚያ ክልልና በይዞታችን ላይ በመሆኑ ተላልፈው ሊሰጡ አይገባም› በማለት በአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ መነሳቱ ይታወሳል፡፡ ተቃውሞው ከተሰማ በኋላ ከከተማ አስተዳደሩና ከኦሮሚያ ክልል የተውጣጡ የኮሚቴ አባላት የድንበሩን ሁኔታ አጣርተው እንዲያቀርቡ ውሳኔ መተላለፉም አይዘነጋም፡፡

MORE https://telegra.ph/2080-02-12

[ሪፖርተር ጋዜጣ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Audio
#DrDebretsionGebremichael

የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ይገባኛልና ሌሎች ውዝግቦች በሕግና ስርዓት  የመጨረሻ መፍትሔ ሊሰጣቸዉ እንደሚገባ የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት) ሊቀመንበርና የትግራይ ምክትል ርዕሠ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አስታወቁ።

ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን በቅርቡ የኤርትራዉ ፕሬዝደንት ለሰጡት አስተያየት አፀፋ በመሰለ መግለጫቸው ለየውዝግቡ አብነቱ ሕጋዊ መፍትሔ ማግኘት ነው ብለዋል።

የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ኢትዮጵያና ኤርትራ ሰላም ለማውረድ ከተስማሙ በኋላ የሁለቱ ሐገራት የድንበር  ሁኔታን «የከፋ» ብለዉታል። ፕሬዝደንት ኢሳያስ ለሁኔታው መክፋት የትግራዩን ገዢ ፓርቲ ሕወሓትን ተጠያቂ አድርገዋልም።

[የጀርመን ድምፅ ሬድዮ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአንድነት ፓርክ ከነገ ጀምሮ ክፍት ይሆናል!

የአንድነት ፓርክ ከነገ ሀሙስ የካቲት 05/06/2012 ዓ/ም ጀምሮ ክፍት ሆኖ ወደ መደበኛ አገልግሎቱ እንደሚመለስ ተገልጿል።

ፓርኩ ከቅዳሜ ጥር 30 እስከ ረቡዕ የካቲት 4/2012 ዓ.ም ድረስ ለጎብኚዎች ዝግ ሆኖ የቆየ ሲሆን ከነገ ሀሙስ የካቲት 5/2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መደበኛ ስራው እንደሚመለስ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ፓርኩ በአዲስ አበባ በተካሄደው 33ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጋር በተያያዘ ዝግ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል።

[አንድነት ፓርክ፣ ኢፕድ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#JIMMAA #AGGAAROO ዛሬ የጅማ እና የአጋሮ ከተማ የነዋሪዎች አደባባይ በመውጣት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አመራር ያላቸውን ድጋፍ ገልፀዋል። በጅማ ከተማ "ለብልፅግና እንሩጥ" በሚል የጎዳና ላይ ሩጫም ተካሂዷል። የጠቅላይ ሚኒስትሩን አመራር እናደንቃለን ያሉት ወጣቶች 'እኛም ዶ/ር አብይ ነን" ሲሉ ተደምጠዋል። ስድብ እና ጥላቻ፣ እንዲሁም የኦሮሞን ህዝብ መከፋፈል ላይ የተጠመዱ አካላትም…
BBC ያነጋገራቸው የትላንቱ የጅማ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ ተሳታፊዎች...

የሠልፉ አስተባባሪና ተሳታፊ የጅማ ወጣቶች ሊግ ኃላፊ ድማሙ ንጋቱ፦

"ለውጡ መቀጠል አለበት ፤ የኦሮሞ ሕዝብ መከፈል፤ መሰደብም የለበትም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ሌሎች የኦሮሞ ሕዝብም ሆነ እንደ አገር የተወከሉ መሪዎች መከበር አለባቸው በሚል ሃሳብ ሠልፉ ተዘጋጅቷል። የሠልፉ መነሻ ሃሳብ የኦፌኮ አባል የሆኑት አቶ ጃዋር መሐመድ በተለያየ መድረኮች ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሲወረፉ መሰማታቸውን ቅሬታ በመፍጠሩ ነው"

በሠልፉ ላይ ተሳታፊ፦

"ጠቅላይ ሚኒስትሩን በማስመልከት በተለያዩ ሕዝባዊ መድረኮች የሚናገሩት ንግግር ያልተገባ ነው ሕዝቡንም አስከፍቷል። ሕዝቡ የወከላቸው መሪዎችን መስደብና ማንኳሰስ ሕዝቡን ራሱ እንደመስደብ ነው የሚቆጠረው። በፖለቲካ የሃሳብ ልዩነት ያለ ቢሆንም ይህ የሃሳብ ልዩነት ሕዝቡን መከፋፈል የለበትም"

በጅማ በተደረገው የድጋፍ ሠልፍ ላይ አለመሳተፉን የሚናገረው ወጣት አሕመድ አባ መጫ፦

"የኦሮሞ ህዝብ ዓላማ፣ ዋጋ ከፍሎ እዚህ ያደረሰውን ትግል የቀረውን ነገር አሟልቶ ከዳር ማድረስ ነው። የጅማ ወጣቶችና ሕዝቡ ፍላጎትም ይኸው ነው። ጃዋር ተምሳሌታችን ነው፤ ኦፌኮን ከተቀላቀለ በኋላ የሚናገራቸው አንዳንድ ንግግሮች አስከፍተውኛል። ስሜታዊ ሆነን የምናገራቸው ንግግሮች መጥፎ ነገር ያስከትላሉ፤ ስለዚህ ተከባብረን እየተደማመጥን በፕሮግራምና በፖሊሲ ላይ ቢሆን ክርክር ማድረግ እንጂ ጣት መቀሳርና መወራረፍ ጠቃሚ አይደለም። የጅማ ሕዝብ ጥያቄና ሠልፉን ያደረገበት ምክንያት ይኸው ነው"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጅማ ኦፌኮ ስብሰባ ለምን ተከለከለ?

በትናንትናው ዕለት ኦፌኮ በጅማ ስታዲየም ከደጋፊዎቹ ጋር ሊያካሄድ የነበረው ስብሰባ ለምን እንደተከለከለ የድርጅቱ የጅማ ቅርንጫፍ ኃላፊ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከዞኑ አመራሮች ጋር በመግባባት ሲሰሩ እንደቆዩ የሚገልፁት ኃላፊው ነገር ግን ጃዋር ፓርቲያቸውን ከተቀላቀለ በኋላ አለመግባባቶች መከሰታቸውን አስረድተዋል።

"ጃዋር ከመጣ በኋላ ጥሩ አልነበረም። የኦፌኮ ልዑክ ወደ ጅማ ለመምጣት ከወሰነ በኋላ ደግሞ እንደ ጠላት ማሳደድ ጀመሩ" ብለዋል።

ትልቅ ጫና እየደረሰብን ነው ያሉት አቶ ዑመር አባላቶቻቸው እየታሰሩ መሆኑንና ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ይናገራሉ ሲሉ ገልፀዋል።

የተከለከሉት የምርጫ ቅስቀሳ ታካሂዳላችሁ ተብለው እንደሆነ የሚናገሩት ኃላፊው "እኛ የጠየቅነው የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ሳይሆን የሕዝብ ትውውቅ መድረክ ለማካሄድ ነው" ብለዋል።

የጅማ ከተማ ከንቲባ የሆኑት አቶ መኪዩ መሐመድ ጉዳዩን አስመልክቶ በኦፌኮ ለሚቀርበው ቅሬታ ሲመልሱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ያላቸው ግንኙነት ሕጉን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ጠቅሰዋል።

"ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች ቅስቀሳ እንዲያደርጉ አልፈቀደም፤ ኦፌኮ በሌሎች ዞኖች የሚያደርጋቸው እንቅስቀሴዎች የትውውቅ ሳይሆን የምርጫ ቅስቀሳ ነው" ብለዋል

በዚህም ምክንያት ስብሰባውን አለመፍቀዳቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም የከተማው አስተዳደር ሳያውቅ ለሕዝብ ጥሪ መተላለፉንና ፀጥታን በተመለከተ በቂ ዝግጅት ባለመደረጉ ስታዲየሙ ውስጥ ስብሰባ እንዳይደረግ መከልከላቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ከንቲባው አክለው ፕሮግራሙ ሙሉ በሙሉ እንዳልተከለከለ አስተረድተው የትውውቅ መድረካቸውን ወደ ሌላ ጊዜ እንዲያስተላልፉት ለፓርቲው አመራሮች እንደተነገራቸው ገልፀዋል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሠልፎቹን መንግሥት አበል ከፍሎ ነው ያስተባበረው?

የማህበራዊ ሚዲያዎች ርዕስ የነበረው ጉዳይ ትላንት በጅማና አጋሮ የተደረጉት ሰልፎች መንግስት አበል ሰጥቶ ያስተባበረው ነው እንጂ ሰዎች ፈልገው ያደረጉት አይደለም የሚል ነበር።

ለዚህ ጉዳይ ቢቢሲ ዛሬ ይዞት በወጣው ዘገባ ላይ የሠልፉ አስተባባሪ እንዲሁም ተሳታፊ የጅማ ወጣቶች ሊግ ኃላፊ ድማሙ ንጋቱ፦

"አበል መክፈል ይቅርና ቲሸርቶቹንና መፈክሮችን ለማሳተም እንኳ መንግሥት ምንም ዓይነት ገንዘብ አላወጣም" የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrDebretsionGebremichael የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ይገባኛልና ሌሎች ውዝግቦች በሕግና ስርዓት  የመጨረሻ መፍትሔ ሊሰጣቸዉ እንደሚገባ የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት) ሊቀመንበርና የትግራይ ምክትል ርዕሠ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አስታወቁ። ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን በቅርቡ የኤርትራዉ ፕሬዝደንት ለሰጡት አስተያየት አፀፋ በመሰለ መግለጫቸው ለየውዝግቡ…
ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በኤርትራ ጉዳይ፦

"የወሰንና ሌሎች መጨረሻ ያላገኙ ጉዳዮች አሉን እኛ ህግና ስርዓት ተከትሎ መጨረሻ ያግኝ እንላለን በግጭት የሚፈታ ነገር የለም፤ በህግና ስርዓት እንጂ። ስለዚህ የኛ ፍላጎት ይህ መሆኑ መታወቅ አለበት። በሁለታችንም በኩል ያለፈ አልፏል፤ ዓለም አቀፋዊ ይሁን የአካባቢ ህግ አለ በተለይም ይህ ጉዳይ አለም የሚያውቀውና ውሳኔ የተዳሰጠበት ነው። እኛ ተቋማዊ በሆነ መንገድ ታይቶ መጨረሻ እንዲያገኝ ዝግጁነት አለን። ሳትቀራረብ ግን የሚያልቅ ነገር የለም። አሁን ላይ የሚታይ መቀራረብ የለም። እንደ ህዝብና መንግስት ግን ከኛ የሚጠበቀውን ለመፈፀም ዝግጁ መሆናችንን ለመገልፅ እንፈልጋለን።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ ለጦር ጉዳተኞች ብድር እየተሰጠ ነው!

የትግራይ ጦር ጉዳተኞች ማህበር የአባላቱን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጎልበት የአንድ መቶ ሚሊዮን ብር የብድር አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ።

የማህበሩ ስራ አስኪያጅ  አቶ ጨርቆስ ወልደማርያም አንደገለፁት ከደደቢት ብድርና ቁጠባ አክሲዮን ማህበር ጋር በመተባበር ከትናንት ጀምሮ በብድር እየሰጠ ያለውን ገንዘብ የጦር  ጉዳተኞቹ ያለባቸውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ለመፍታት ያለመ ነው።

የብድር አገልግሎቱ በመጀመሪያው ዙር ለ2 ሺህ 460 አባላቱ  የሚከፋፈል መሆኑን ተናግረዋል። አባላቱ በብድር የሚወስዱትን ገንዘብ በሦስት አመታት  ውስጥ ሰርተውና አትርፈው የሚከፍሉት መሆኑነ ከስራ አስኪያጁ ገለፃ ለማወቅ ተችሏል ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JIMMA

ዛሬ በጅማ ስታዲየም የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድን የለውጥ አመራር የሚደግፍ ዝግጅት እየተካሄደ ይገኛል። በርካታ ቁጥር ያለው የጅማ እና አካባቢው ነዋሪ ከጥዋት ጀምሮ ወደ ስታዲየም ሲያመራ እንደነበር የጅማ ከተማ ቲክቫህ ቤተሰቦች ገልፀዋል።

ምን አይነት መልዕክት ነው እየተላለፈ የሚገኘው ብለን የጅማ ቲክቫህ ቤተሰቦቻችን ጠይቀናል፦

- ዶ/ር አብይ አህመድ የሰራውን በጎ ስራ በማጣጣል የሚመጣ ለውጥ የለም፤ ሀሳብ ያላቸው ለህዝቡ ሀሳብ ያቅርቡ።

- ስድብ፣ እና ጥላቻ ባህላችን አይደለም፤ የሀገር መሪዎችን በአደባባይ መሳደብና ማንቋሸሽ ከባህላችን ያፈነገጠ ነው።

- ሀገር ማስተዳደር የሚገልጉ ሰዎች ሀሳባቸውን ሽጠው በምርጫ ይመረጡ፤ ከዛ ውጪ ስድብ እና ማንቋሸሽ፣ የስም ማጥፋት ዘመቻ ማካሄድ ተገቢነት የለውም።

- እኛም ዶክተር አብይ አህመድ ነን!

- የተለያዩ ሀሰተኛ መልዕክቶችን በማስተላለፍ የኦሮሞን ህዝብ ለመከፋፈል የሚሰራው ስራ ሊቆም ይገባል።

- ዶ/ር አብይ የሰላም እና የብልፅግና አባት ነው!

- እኛ የአባጅፋር ልጆች አቃፊዎች ነን!

- ስድብ እና ጥላቻ ተቀባይነት የለውም!

- ጅማ መሬትም ሰውም አለ!

- ጊዜው የዶክተር አብይ ነው!

- ከዶክተር አብይ ጋር ወደብልፅግና እንሻገራለን!

[የቲክቫህ ጅማ ቤተሰቦች]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia