የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ሜዳሊያ ተሸለመ...
በደቡብ ሱዳን፣ ቦር በሚገኘው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል 2ኛ ባታሊዮን አባላት የሜዳሊያ ተሸለመ። በሽልማት ሥነ-ስርዓቱ ላይ የUNMISS ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሻይለሽ ቲናይካር፣ የጆንግሌ ክልል አስተዳዳሪ ሜከር ቲኦንግ ማል፣ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ ታደሰ እንዲሁም ሌሎች የተመድ እና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።
#EPA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

የጀነራል ተፈራ ማሞ ሹመት...
የአማራ ክልል ልዩ ሀይል አዛዥ የነበሩት ጄኔራል ተፈራ ማሞ በአማራ ውሀ ስራዎች ኮንስትራክሽን አማካሪነት ሹመት ቢሰጣቸውም ሳይቀበሉት እንደቀሩ ተሰምቷል። ጄነራል ተፈራ ማሞ ከአማራ ሚዲያ ማዕከል ጋር በነበራቸው ቆይታ ከሰለጠንኩበትና እድሜ ልኬን ካገለገልኩበት ሙያየ ጋር የማይገናኘው የአማራ ውሀ ስራዎች ኮንስትራክሽን አማካሪነት ምደባን አልቀበለውም ብለዋል።
ጀነራሉ ለአሚማ ከተናገሩት የተወሰደ፦
- ቀደም ሲል ወደ አማራ ክልል ገብቼ በአማራ ልዩ ሀይል አዛዥነት ለማገልገል የወሰኑበት ዋነኛ ምክንያት በክልሉና ከክልሉ ውጭ በአማራ ላይ እየደረሰ ያለውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ነበር።
- በአጭር ጊዜ የአመራርነት ቆይታዬም የምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር የነበረውን አለመረጋጋትን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ከአመራር ሰጭነት ድክመት የተከሰተውን ግጭት አንፃራዊ በሆነ መልኩ ለመቆጣጠርና ለማርገብ ተችሎ ነበር።
- የሰኔ 15ቱ አሳዛኝ የወንድሞቻችንን ግድያን ተከትሎ በእስር ቆይተን በተፈታን ማግስት ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባደረግነው ውይይት በፀጥታው ረገድ ያለውን የአመራርነት ክፍተት በመሙላት የአማራን ህዝብ ለመታደግ እንደምንሰራ የነገርናቸውን ወደ ጎን ትተው የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን አማካሪ ማድረጋቸው እንደማልቀበለው ላናገረኝ አካል መልስ ሰጥቻለሁ።
- አማራን በመንደር አጀንዳ ብቻ በመጥመድ በህዝብ ደም ላይ የራሳቸውን ጥቅም ለማጋበስ እና እድሜያቸውን ለማራዘም ለሚሰሩ አካላት ህዝቡ ፍፁም ጆሮ መስጠት የለበትም። አንድነቱን ያስጠበቀ አደረጃጀትን በማስቀጠል በቅድሚያ ሕልውናውን እንዲያስከብር አሳስባለሁ።
ምንጭ፦ አማራ ሚዲያ ማዕከል
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

በትራፊክ አደጋ በየሁለት ሰዓቱ የአንድ ሰው ህይወት እንደሚቀጠፍ ተገለፀ!
ኢትዮጵያ በትራፊክ አደጋ ምክንያት በየሁለት ሰዓቱ የአንድ ሰው ሰው ህይወት እንደሚቀጠፍ ተገለፀ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ የልማት ኮሚሽን አስባበሪነት በኢትዮጵያ መንገድ ደህንነት አጠቃላይ ሁኔታ ላይ በተዘጋጀዉ መድረክ ላይ ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ጌቱ ሰኚ ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ በትራፊክ አደጋ ምክንያት በኢትዮጵያ በዩሁለት ሰዓቱ አንድ ሰው ህይወቱን ያጣል።
እንደ ዶ/ር ጌቱ ማብራሪያ በኢትዮጵያ በትራፊክ አደጋ ሳቢያ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2018 ብቻ 4559 ሞት፣ 7407 ከባድ የአካል ጉዳት፣ 5949 ቀላል የአካል ጉዳት እንዲሁም 30 222 በንብረት ላይ አደጋ ደርሷል።

የኮሎኔል አለበል እና ኮሎኔል ባምላኩ ሹመት...
ዛሬ ጥር 5 ቀን 2012 ዓ.ም በማህበራዊ ሚዲያ ደረጃ ለኮ/ል ባምላኩ አባይ የአማራ ህንጻ ስራዎች ድርጅት አማካሪነት እንዲሁም ለኮ/ል አለበል አማረ ደግሞ የአማራ የገጠር መንገድ ስራ ድርጅት አማካሪነት ሹመት ተሰቷል የሚለው መረጃ ምን ያህል እውነት ነው ሲል የአማራ ሚዲያ ማዕከል ጥያቄ ያቀረበላቸው የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ም/ኃላፊ የነበሩት ኮሎኔል አለበል አማረ እንደማንኛውም ሰው በወሬ ደረጃ ከመስማት ባለፈ እስካሁን የደረሰኝ የሹመት ደብዳቤ የለም ብለዋል። ኮሎኔል ባምላኩ አባይ በበኩላቸው ሲወራ ከመስማት ውጭ እጃቸው ላይ የደረሰ ደብዳቤ አለመኖሩን ገልፀዋል።

የቃሊቲ - ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት...
በተያዘው በጀት ዓመት የቃሊቲ - ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን 75 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ እንደሆነ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ክቡር ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተቋራጮች እየተከናወኑ የሚገኙ የመንገድ ኘሮጀክቶችን ለመገምገምና የሚያጋጥሙ እንቅፋቶችን በአካል ተገኝቶ መፍትሄ ለመስጠት የመስክ ጉብኝት አካሂደዋል፡፡

አቶ አመንቴ ገሺ መታሰራቸው ተሰማ...
የቦሮ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ አመንቴ ገሺ ትናንት መታሰራቸውን ፓርቲያቸው ዐስታወቀ። ሊቀ መንበሩ በምርጫ ቦርድ ጥር 7ና 8 ቀን ፓርቲዎችን ለማወያየት በተዘጋጀው መርኃግብር ላይ ለመሳተፍ ከአሶሳ ቦሌ አየር ማረፍያ እንደደረሱ በፌደራል ፖሊስ ተይዘው መታሰራቸውን የፓርቲው የፖለቲካ ጉዳዩች ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ዐስታውቀዋል።
#DW

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አቶ ኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) ከቢቢሲ ጋር...
በኦሮሚያ ይንቀሳቀሳሉ ከተባሉ ታጣቂዎች መኃል አንዱና የቀድሞ የኦነግ ሰራዊት የጦር መሪ ነበር ተብሎ የሚታመነው አቶ ኩምሳ ድሪባ (በትግል ስሙ መሮ) ከሰሞኑን የሱ ክንፍ በስፋት ይንቀሳቀስበታል በሚባለው ኦሮሚያ ምዕራባዊ ክፍል አለ ስለሚባለው የጦር እንቅስቃሴ ከቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ክፍል ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር።
ቢቢሲ : አሁን አካባቢው ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል?
ጃል መሮ : የአሁኑን በጥቂቱ ለየት የሚያደርገው የስልክ እና የሞባይል ዳታ ግንኙነት መቅረጡ ነው። ህብረተሰቡ እየተገናኘ አይደለም። እንዳሰቡት በኦሮሞ ነፃነት ጦር ላይ የበላይነትን ማሳካት ስላልቻሉ በተለየ መንገድ ሊሄዱበት የወሠኑት ውሳኔ ነው እየተከናወነ ያለው። ከፍተኛ ጦር በበርካታ ተሽከርካሪዎች እየመጣ ነው የቆየው። ከዚህ በተጨማሪ ባለፈው ጊዜ በአስቸኳይ ለአጭር ጊዜ ያሰለጠኗቸው ኃይሎች ወደዚህ መጥተዋል። ይህ ሚስጥር አይደለም። በህብረተሰቡ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ ይታያል። በህዝቡ ተሽከርካሪዎች ነው የሚገለገሉት እንደዚሁ ይመጣሉ መመለስ የለም።
ቢቢሲ : አይመለሱም ስትል ተመተው እዚህ ይቀራሉ ማለት ነው? ብታብራራልን።
ጃል መሮ : አጭር መልስ እኮ ነው!
ቢቢሲ : በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ 17 ተማሪዎች በታጠቀ ኃይል መታገታቸው ይሰማል። በደምቢ ዶሎና ጋምቤላ መኃል የናተ ጦር ነው ያገታቸው ይባላል።
ጃል መሮ : ይህን ለመጀመሪያ ጊዜ እየሰማሁ ያለሁት ካንተ ነው። የኛ ጦር እንደዚህ ያለ ተግባር አይፈፅምም። ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር የሚያይዘን ነገር የለም። ይህ ፍፁም አይሆንም፣ ከዚህ በፊትም ሆኖ አያውቅም፣ ወደፊትም አይደረግም።
https://telegra.ph/BBC-01-14-2
@tikvahethiopia

እነ ጃል መሮ ከህወሓት ሰዎች ጋር አብረው እየሰሩ ነው፤ ጃል መሮም ሰሞኑን መቐለ ነበረ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ ስለሚናፈሰው ወሬ ለቢቢሲ የሰጠው ምላሽ፦
"ስትፈልጉ መሮ ሞቷል፣ ስትፈልጉ መቐለ ነው ያለው፤ የኦሮሞ ልጆች የሚፈልጉት ነገር አለ። ኦሮሞ ራሱን ችሎ፤ የራሱን ፖለቲካ፣ የራሱን የጥበቃ ኃይል አስተዳደር እና ፖሊስ ኖሮት የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ መመለስ ይችላል ብሎ ከማሰብ ይልቅ በተጋሩዎች በኩል ነው፤ በአማራዎች በኩል ነው የሚያዋጣን ብለው ሰበብ ይፈልጋሉ። መሮ ወይም የኦሮሞ ነፃነት ጦር ከነዚህ ጋር ይሰራሉ ሊሉ ይሻሉ እኛ ራሳችንን ችለን ነው የምንቀሳቀሰው። ለማንኛውም እኔ የምገኘው በኦሮሚያ ጫካ ውስጥ በወለጋ ቡና ስር ነው።"

Audio
ወልዲያ ዩኒቨርስቲ ጥሪ አስተላለፈ...
በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄደው የነበሩ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ተመልሰው ትምህርት መጀመራቸውን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው አሁንም ከ1500 የሚልቁ ተማሪዎች አለመመለሳቸውን አስታውሶ ለተማሪዎቹ ጥሪ አስተላልፏል፡፡
ከቤተሰቦቻቸው ለተመለሱት ተማሪዎች የማካካሻ ክፍለ ጊዜ ተዘጋጅቶላቸው ያለፋቸውን ትምህርት እንዲከታተሉ እየተደረገ መሆኑንም ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡
(VOICE OF AMERICA)

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን...
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በኮልፌ ልዩ ልዩ ሙያ ማሰልጠኛ ያሰለጠናቸዉን የፀጥታ እና ህግ ማስከበር ዳይሬክቶሬት አመራሮች እና አባላትን አስመርቋል፡፡
በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የፀጥታ እና ህግ ማስከበር ዳይሬክቶሬት አመራር እና አባላት በተሰማሩባቸዉ ፖሊሳዊ ተልዕኮዎች ሁሉ የወንጀል መከላከል ስራዎችን በፅናት፣ በቁርጠኝነት እና በብቃት ስያከናዉኑ መቆየታቸዉ ተገልጿል፡፡
በቀጣይ የሚጠበቅባቸዉ ሀገራዊ ግዳጆችን በብቃት መወጣት እንዲችሉም በቅርብ ወደ ሰዉ ሃይል የተቀላቀሉ አዳዲስ አባላትን ጨምሮ ለነባር አመራሮች እና አባላት ስልጠናዉ መሰጠቱን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
(AMN)

#Election2012
ባለድርሻ አካላት ለምርጫ 2012...
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ 2012ን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገው ውይይት ተጀምሯል። የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የውይይቱ ተሳታፊዎች ነን የሚነሱ ጉዳዮችን ከስር ከስር መረጃ እናካፍላችኃለን።
#TIKVAH_ETHIOPIA

በዛሬው የምርጫ ቦርድ የውይይት መድረክ ላይ የ2012 #ምርጫ የጊዜ ሰሌዳን በተመለከተ በቦርዱ ሰብሳቢ፤ ብርቱካን ሚደቅሳ፤ ከሚደረገው ገለጻ በተጨማሪ የቦርዱ "ኦፕሬሽን" አበይት ዕቅዶችም ለተሳታፊዎች ይቀርባል።
#Election2012 #Election2020
(ETHIOPIA ELECTION)

TIKVAH-ETHIOPIA
#Election2012 ባለድርሻ አካላት ለምርጫ 2012... የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ 2012ን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገው ውይይት ተጀምሯል። የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የውይይቱ ተሳታፊዎች ነን የሚነሱ ጉዳዮችን ከስር ከስር መረጃ እናካፍላችኃለን። #TIKVAH_ETHIOPIA @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012
የዛሬው ውይይት ዓላማ...
1. ቦርዱ ስላካሄዳቸው አጠቃላይ እንቅስቃሴና እቅድ ገለጻ የሚደረግበት።
2. ቦርዱ ባቀረበው የጊዜ ሰሌዳ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረግ ነው፡፡
(ዶ/ር አበራ ደገፋ - የቦርድ አባል)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዛሬው ውይይት ዓላማ...
1. ቦርዱ ስላካሄዳቸው አጠቃላይ እንቅስቃሴና እቅድ ገለጻ የሚደረግበት።
2. ቦርዱ ባቀረበው የጊዜ ሰሌዳ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረግ ነው፡፡
(ዶ/ር አበራ ደገፋ - የቦርድ አባል)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የምርጫ 2012 ዋና ዋና ቀናት፦
* ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ
- የድምፅ መስጫ ቀን ነሃሴ 10/2012
- ውጤት በምርጫ ጣቢያዎች ይፋ የሚደረግበት ቀን ነሃሴ 10-12/2012
- በምርጫ ክልል ደረጃ ቅድመ ውጤት ይፋ የሚሆንበት ጊዜ ነሃሴ 11-ነሃሴ 15/2012
- የቦርዱ የተረጋገጠ ውጤት ማስታወቂያ ጊዜ ነሃሴ 11-ነሃሴ 20/2012
* የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባቀረበው ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር እተደረገ የሚገኘው ውይይት ቀጥሏል። እየተከታተልን እናሳውቃለን።

በምርጫ ቦርድ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት፦
- የእጩ ምዝገባ ጊዜ ሚያዚያ 13-ሚያዚያ 26/2012
- የምርጫ ዘመቻ ጊዜ ሚያዚያ 27-ነሃሴ 05/2012
* ማስታወሻ : ይህ በረቂቅ ደረጃ የቀረበ ነው።
ውይይቱ በጁፒተር ሆቴል እንደቀጠለ ነው!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
- የእጩ ምዝገባ ጊዜ ሚያዚያ 13-ሚያዚያ 26/2012
- የምርጫ ዘመቻ ጊዜ ሚያዚያ 27-ነሃሴ 05/2012
* ማስታወሻ : ይህ በረቂቅ ደረጃ የቀረበ ነው።
ውይይቱ በጁፒተር ሆቴል እንደቀጠለ ነው!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NEBE
የቦርዱ ኦፕሬሽን እቅድ ዋና ዋና ክፍሎች በተመለከተ በወ/ሮ ብዙወርቅ ከተተ የቀረበ፦
- ቦርዱ እስካሁን ምርጫ ቦርድን መልሶ በማቋቋም ፣ የሰው ኃይል ማደራጀት የፓሊሲ ሥራ ላይ ሲሰራ ቆይቷል፡፡
- የሕግ ማዕቀፉን በተመለከተ መመሪያዎችን ማርቀቅ፣ ግንዛቤ መስጠት እንዲሁም ከፓለቲካ ፓርቲዎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
- በምርጫ ወቅት የሚነሱ ችግሮች የሚፈቱበትን የህግ ማዕቀፍ ሲያዘጋጅ ቆይቷል።
- የምርጫ ወረዳዎችን ማደራጀት፣ የምርጫ ቁሳቁሶች ግዢ፣ የኮምኒኬሽን ስትራቴጂ፣ የመራጮች ትምህርት ማኑዋል፣ የምርጫ ታዛቢዎች ፈቃድ የሚያገኙበትን ሂደት እየሰራ ይገኛል፡፡
ታሳቢ ተደርገው መሰራት የሚገባቸው፡-
- የሴቶች ተሳትፎ
- የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎ
- የአርብቶ አደር አከባቢዎች ላይ ያለው ተደራሽነት
ያሉ ተግዳሮቶች፡-
- ቦርዱ የምርጫ ሂደቱን እየመራ በተመሳሳይ ደግሞ ሪፎርም እያካሄደ ይገኛል፡፡ ሁለቱን በአንድ መስራት ይቻላል ግን እንደ አንድ ተግዳሮት ይቆጠራል፡፡
- ቦርዱ በርካታ ስራዎችን ከአጋር ድርጅቶች ጋር ይሰራል እነሱን መመዝገብ ፈቃድ መስጠት መቆጣጠር ካለው የጊዜ ውስንነት የተነሳ እንደ አንድ ተግዳሮት ይታያል፡፡
- ቋሚና ምርጫውን በተመለከተ የምንቀጥራቸውን የሰው ኃይሎች መለየት የተመረጡት ላይ በፓለቲካ ፓርቲዎች ማስገምገም ራሱን የቻለ ሰፊ ስራ የሚጠይቅ በመሆኑ እንደ ተግዳሮት ተቆጥሯል
- የጸጥታ ጉዳይም ትልቁ ተግዳሮት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የምርጫ ቁሳቁስ ስምሪትም ሆነ በምርጫ ሂደቱ ወቅት የጸጥታ ችግር እንደ ተግዳሮት ይታያል፡፡
#TikvahEthiopia

እነ ጃል መሮ ከህወሓት ሰዎች ጋር አብረው እየሰሩ ነው፤ ጃል መሮም ሰሞኑን መቐለ ነበረ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ ስለሚናፈሰው ወሬ ለቢቢሲ የሰጠው ምላሽ፦ "ስትፈልጉ መሮ ሞቷል፣ ስትፈልጉ መቐለ ነው ያለው፤ የኦሮሞ ልጆች የሚፈልጉት ነገር አለ። ኦሮሞ ራሱን ችሎ፤ የራሱን ፖለቲካ፣ የራሱን የጥበቃ ኃይል አስተዳደር እና ፖሊስ ኖሮት የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ መመለስ ይችላል ብሎ ከማሰብ ይልቅ በተጋሩዎች…
ጃል መሮ ስለተማሪዎች እገታ...
17 የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በጸጥታ ስጋት ወደ ትውልድ ቀያቸው ሲያመሩ ደምቢ ዶሎ እና ጋምቤላ መካከል ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት መታገታቸው ይታወሳል።
ምንም እንኳ የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው፤ ታግተው ከነበሩት ተማሪዎች መካከል አብዛኞቹ እንዲለቀቁ መደረጋቸውን ተናግረዋል። ኃለፊው ይህን ይበሉ እንጂ፤ የተማሪዎቹ ወላጆች ''ማን ይለቀቅ ፤ ማን አይለቀቅ እስካሁን አላወቅንም'' እያሉ ይገኛሉ።
ተማሪዎቹን ያገታቸው የትኛው አካል እንደሆነ በይፋ ባይነገርም፤ በምዕራብ ኦሮሚያ ታጥቆ የሚንቀሳቀሰው እና በድሪባ ኩምሳ የሚመራው ኃይል ስለመሆኑ ብዙዎች ግምታቸው አስቀምጠዋል።
ጃል መሮ ግን "ይህን ለመጀመሪያ ጊዜ እየሰማሁ ያለሁት ከእናንተ ነው። የትግል ዓላማችን ከተማሪዎች ጋር አይገናኝም። በተማሪዎቹ ላይም ይህን የተባለውን አይነት ተግባር አልፈጸምንም። እንደተለመደው የእኛን ስም ለማጉደፍ የተወራ ነው እንጂ በፍጽም እንዲህ አይነት ተግባር አሁንም ወደፊትም እንፈጽምም'' ብሏል።
ጃል መሮ ተማሪዎቹ ታግተውበታል በሚባለው ሥፍራ በኮንትሮባንድ ንግድ ሥራ ላይ ታጥቀው የተሰማሩ አካላት መኖራቸውን ተናግሮ፤ የእሱ ጦር ግን በአካባቢው እንደሌለ ተናግሯል።
#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
17 የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በጸጥታ ስጋት ወደ ትውልድ ቀያቸው ሲያመሩ ደምቢ ዶሎ እና ጋምቤላ መካከል ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት መታገታቸው ይታወሳል።
ምንም እንኳ የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው፤ ታግተው ከነበሩት ተማሪዎች መካከል አብዛኞቹ እንዲለቀቁ መደረጋቸውን ተናግረዋል። ኃለፊው ይህን ይበሉ እንጂ፤ የተማሪዎቹ ወላጆች ''ማን ይለቀቅ ፤ ማን አይለቀቅ እስካሁን አላወቅንም'' እያሉ ይገኛሉ።
ተማሪዎቹን ያገታቸው የትኛው አካል እንደሆነ በይፋ ባይነገርም፤ በምዕራብ ኦሮሚያ ታጥቆ የሚንቀሳቀሰው እና በድሪባ ኩምሳ የሚመራው ኃይል ስለመሆኑ ብዙዎች ግምታቸው አስቀምጠዋል።
ጃል መሮ ግን "ይህን ለመጀመሪያ ጊዜ እየሰማሁ ያለሁት ከእናንተ ነው። የትግል ዓላማችን ከተማሪዎች ጋር አይገናኝም። በተማሪዎቹ ላይም ይህን የተባለውን አይነት ተግባር አልፈጸምንም። እንደተለመደው የእኛን ስም ለማጉደፍ የተወራ ነው እንጂ በፍጽም እንዲህ አይነት ተግባር አሁንም ወደፊትም እንፈጽምም'' ብሏል።
ጃል መሮ ተማሪዎቹ ታግተውበታል በሚባለው ሥፍራ በኮንትሮባንድ ንግድ ሥራ ላይ ታጥቀው የተሰማሩ አካላት መኖራቸውን ተናግሮ፤ የእሱ ጦር ግን በአካባቢው እንደሌለ ተናግሯል።
#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢራን የአውሮፕላን አደጋውን በቪድዮ የቀረፀውን ሰው በቁጥጥር አውላለች!
ኢራን የአውሮፕላን አደጋውን በምስል የቀረጸውን ሰው በቁጥጥር ስር አውላለች፡፡ አውሮፕላኑ በሚሳኤል ተመቶ ሲወድቅ በምስል ያስቀረውን ሰው በቁጥጥር ስር ማዋሏን ነው ኢራን ያስታወቀችው፡፡ ግለሰቡ ከብሄራዊ ደህንነት ጋር በተያያዘ ክስ ይመሰረትበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የበረራ ቁጥሩ PS752 የሆነው ይህ አውሮፕላን ባለፈው ሳምንት ረቡእ እለት ነበር ከቴህራን ከተነሳ በኋላ በሚሳኤል ተመቶ የተከሰከሰው፡፡ ኢራን ድርጊቱ በስህተት የተፈጸመ መሆኑን በመግለጽ፤ ተሳትፈዋል ያለቻቸውን ሰዎች በቁጥጥር ስር እያዋለች መሆኑን አስታውቃለች፡፡
ምርመራው በልዩ ፍርድ ቤት እንደሚታይም ፕሬዘዳንት ሃሰን ሩሃኒ ተናግረዋል፡፡ ይህ መደበኛና የተለመደ አይነት ጉዳይ አይደለም፤ መላው አለም ይህን ችሎት ይመለከተዋል ብለዋል፡፡
በተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት ተጠያቂ የሚሆነው አንድ ግለሰብ ብቻ እንደማይሆንም ተናግረዋል፡፡ ኢራን አውሮፕላኑ በሚሳኤል መመታቱን ክዳ የነበረ ቢሆንም፤ በኋለ ግን በአየር መቃወሚያ ሚሳኤል ተመትቶ መውደቁን አምናለች፡፡
ይህን የሚያሳየው ምስል በማህበራዊ ሚዲያ ከተሰራጨ በኋላ ተንታኞች አውሮፕላኑ በሚሳኤል መመታቱን በእርግጠኝነት እንዲናገሩ አድርጓቸዋል እንደ ቢቢሲ ዘገባ፡፡
(BBC, ETHIO FM 107.8)

የ2012 ምርጫ የጊዜ ሰሌዳን አስመልክቶ በቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርትኳን ሚዴቅሳ የቀረበ ገለጻ፡-
የምርጫ ቀኑን የተወሰነው ሕገመንግስቱን መሰረት ባደረገ መልኩ ነው፡፡ ሕገመንግስታችን አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 እንዳስቀመጠው ፡-
"የምክር ቤቱ የሥራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እስከ ሰኔ ሰላሳ ነው ፣ በመካከሉም ምክርቤቱ በሚወስነው ጊዜ የአንድ ወር ዕረፍት ይኖረዋል።"
በዚህ መሰረት ነባሩ ምክር ቤት ለአዲሱ ምክር ቤት አስረክቦ የሚወጣው የመስከረም ወር መጫረሻ ሳምንት በመሆኑ በአንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት ባደረገ መልኩ የአንድ ወር ጊዜ ገደቡን ጠብቆ ተወስኗል፡፡
ታህሳስ 22 በሚጀመረው የምርጫ ክልል ቢሮዎችን ማደራጀት ሥራ 547 የምርጫ ክልሎች ይቋቋማሉ፡፡ የምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላ በተመለከተ 250,000 የሰው ኃይል ያስፈልገናል፡፡
ከዚህ ቀደም በሲዳማ ሪፍረንደም ላይ አዲስ ተመራቂ ተማሪዎችን በማሳተፍ የሰራን ቢሆንም በሚፈጠሩ ክፍተቶች ላይ የተጠያቂነት ክፍተት በመመልከታችን በሀገራዊ ምርጫው ላይ ይህንን ተግባር ቋሚ ሥራ ላይ የተመሰማሩ ሰዎች፣ መምህራንን እንዲሁም በሴቶች አደረጃጀት ላይ ያሉትን ለማሳተፍ አቅደናል በዚህ ላይም ግብአቶች እንፈልጋለን፡፡
ሌላው የቦርዱ ኃላፊነት የምርጫ ካርታ ማዘጋጀት ቢሆንም መካሄድ የነበረበት የህዝብና ቤት ቆጠራ ባለመደረጉ ምክንያት ቀድሞ የተቀመጠውን የምርጫ ካርታ እንጠቀማለን፡፡ ሆኖም ይህ የምርጫ ካርታ በራሱ ህጉ ከምርጫ 180 ቀናት በፊት በግልፅ ይፋ መሆን አለበት ቢልም በግልፅ ባለመቀመጡ እሱን አጥርተንና አሟልተን ለህዝቡና ለፓለቲካ ፓርቲዎች የካቲት 24 ይፋ እናደርጋለን፡፡
https://telegra.ph/TIKVAH-01-15

#UPDATE
ይፋዊ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ጥር 23 ይታወቃል...
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት ባካሄደው ውይይት ያገኛቸውን ግብዓቶች ያካተተ ይፋዊ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ የሚያሳውቀው የፊታችን ጥር 23 ቀን 2012 በርካታ ተሳታፊዎች በሚገኙበት ኮንፍረንስ ላይ ነው።
#ምርጫ2012 #ELECTION2020
(ETHIOPIA ELECTION)
@tikvahethiopia @tsegabwolde

በ7 የንግድ ሱቆች ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ...
በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ፒያሳ አካባቢ በሚገኙ ሰባት የንግድ ሱቆች ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ፡፡ 4 ሰዓት ከ40 ደቂቃ ላይ በተከሰተው በዚህ እሳት አደጋ ሰባት ሱቆች ላይ ቃጠሎ የደረሰ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ ሁለት ሱቆች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገልጿል።
የአዲስ አበባ የእሳት አደጋና ስራ አመራር ኮሚሽን በስፍራው በመገኘት እሳቱ ተጨማሪ አደጋ ሳይስከትል መቆጣጠር መቻሉ ተጠቁሟል፡፡ በዚህ አደጋ በሰው ላይ ምንም አይነት ጉዳት ያልደረሰ ሲሆን፥ የአደጋው መንስኤም እየተጣራ ይገኛል። አደጋው በተከሰተበት ስፍራ ላይ ምግብ ቤቶች፣ የአልባሳት፣ የመነጽር እና የመዋቢያ ቅባት መሸጫ ሱቆች ይገኛሉ።
(ኤፍ ቢ ሲ)