TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወንጀል ነክ መረጃ‼️

ባለትዳር ሆኖ ሳለ ያላገባ በሚል #በተሳሳተ_ማስረጃ ኮንዶሚኒየም ቤት የሸጠዉ አዛዉንት #በእስራት ተቀጣ፡፡ የ86 አመት እድሜ ያለዉ ተከሳሽ ፋንታሁን ረታ በ1996 ዓ.ም የወጣዉን የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 692/1/ስር የተመለከተዉን ድንጋጌ በመተላለፍ በፈፀመዉ የማታለል ወንጀል ተከሷል፡፡

ተከሳሽ ትዳር መስርቶ በፍርድ ቤት በፍቺ እና በንብረት ክፍፍል ሂደት ላይ መሆኑን እያወቀ እና ይህንኑ መግለፅ ሲገባዉ የግል ተበዳይ ወ/ሮ የትምወርቅ በዳሳን የካ ሀያት 2 የቤት ቁጥሩ ብ357/05 የሆነ ባለሁለት መኝታ ኮንዶሚኒየም ቤት አለኝ በ1.300.000 ብር እሸጥልሻለሁ ትዳር የለኝም የግል ንብረቴ ነዉ በማለት ከ1980 ዓ.ም ጀምሮ ያላገባ የሚል የምስክር ወረቀት በማሳየት የተበዳይን የተሳሳተ እምነት ካገኘ በኋላ የቤት ሽያጭ ዉል በመፈፀም ብሩን የተቀበለ ሲሆን ተበዳይም ሽያጩን ለማስፈፀም ስትሄድ በባልና ሚስት ክርክር ታግዷል የተባለችና፤ በኋላም ፍርድ ቤቱ የጋራ ንብረት ነዉ በሚል ቤቱን በአይነት ወይም በሀራጅ እንዲካፈሉ የወሰነ በመሆኑ
በፈፀመዉ የማታለል ወንጀል የፌዴራል አቃቢ ህግ ክስ መስርቶበታል፡፡

ተከሳሽ በተከሰስኩበት ወንጀል የተጠቀሰዉን ያህል ብር አልወሰድኩም ሆኖም ግን 545.000 ብር ወስጃለሁ ስለቸገረኝ ቤቱንም ሽጫለሁ ባለቤቴ የሆነችዉን ሴትም የአጎቴ ልጅ ናት ብዮ አስመዝግቤአለሁ በዚህም ጥፋተኛ ነኝ ሲል የእምነት ቃሉን ሰጥቷል፡፡በተጨማሪም ከሳሽ የፌዴራል አቃቢ ህግ የሰዉና የሰነድ ምስክሮችን በማስረጃነት አያይዞ አቀርቧል፡፡

ግራ ቀኙን የተመለከተዉ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቦሌ ምድብ የወንጀል ችሎትም ምስክሮቹን ካደመጠና ሰነዶቸን ከመረመረ በኋላ ተከሳሽን ጥፋተኛ ነዉ ሲል ፍርድ ሰጥቷል፣ በዚሁም መሰረት ህዳር 25 ቀን 2011 በዋለዉ 1ኛ የወንጀል ችሎት በ4 ዓመት ፅኑ እስራትና በ4000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ቦታው ሲቂ ማሪያም አካባቢ የአስገድዶ #መድፈር ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ #በእስራት ተቀጣ፡፡

የክሱ ዝርዝሩ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ ጫኔ ተሾመ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 620/2/ሀ/ ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ለአካለ መጠን ያልደረሰች የባለቤቱን እህት በቢላዋ እገልሻለሁ በማለት አስፈራርቶ በፈጸመው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡

ዐቃቤ ሕግ የግል ተበዳይን ጉዳት የሚያስረዳ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡

ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ተከሳሹ በሰራው ወንጀል ጥፋተኛ ብሎታል፡፡

የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ግንቦት 09 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት መዝገቡን መርመሮ ተከሳሹ ምንም አይነት ወንጀል ሰርቶ እንደማያውቅና የቤተሰብ አስተዳደሪ መሆኑን በማቅለያነት በመያዝ ተከሳሹን ያርማል በማለት በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

Via የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia