TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ህዳር14 #ኮሞሮስ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሞሮሱ አደጋ....

ህዳር 14/1989 ዓ.ም ልክ በዛሬዋ ቀን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 767-260ER አውሮፕላን በዋና ካፒቴን ልዑል አባተና በረዳት አብራሪው ዮናስ መኩሪያ እየተመራ 175 ተጓዦችንና የበረራ ቡድን አባላትን በመያዝ ወደ ናይሮቢ ለመጓዝ ነበር ከአዲሰ አበባ ተነሳ፡፡

በጉዞው መሃል ሦስት ኢትዮጵያዊያን ሰዎች አውሮፕላኑን በመጥለፍ "አውስትራሊያ አድርሱን ካልሆነ ይህን ቦምብ እናፈነዳዋለን" አሏቸው፡፡ ነገር ግን አውሮፕላኑ ናይሮቢ የሚያደርሰውን ነዳጅ ብቻ ሞልቶ ነበር የተነሳው፡፡ ታዲያ ወደ መጀመሪያ መዳረሻው ናይሮቢ የሁለት ሰዓት ተኩል ጉዞ ለማድረግ የተነሳው አውሮፕላን ከአራት ሰዓት በላይ አየር ላይ በመቆየቱ ነዳጁን ጨረሰ በመጨረሻም በህንድ ውቅያኖስ በኮሞሮስ ደሴት ውሃ ላይ ተከሰከሰ፡፡ በአደጋው 125 ሰዎች ሲሞቱ ሁለቱን አብራሪዎችን ጨምሮ 50 ሰዎች ተርፈዋል፡፡ ሶስቱ ኢትዮጵያውያን ጠላፊዎችም ከሞቱት መካከል ናቸው።

በጊዜው "የጠላፊዎቹን ከፍተኛ የአካልና የአዕምሮ ጥቃት" ተቋቁመው ውሃ ላይ ማሳረፍ በመቻላቸው ካፒቴን ልዑል አባተና ረዳት አብራሪው ዮናስ መኩሪያ ከፍተኛ አድናቆት አግኝተው ነበር፡፡ እሁድን 23 ዓመታት ወደኋላ ተመልሶ ያስቃኘንን BBC የአማርኛ ክፍል ዝግጅት አመሰገንን፡፡

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot