This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለትውስታ ከአምናው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቲክቫህ ቤተሰቦች ጉዞ...
ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተውጣጡ፤ በተለያዩ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚማሩና በማህበራዊ ሚዲያ(ቴሌግራም) ብቻ የተሰባሰቡት የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች...
በልዩነቶቻቸው ተከባብረው፤ በሰውነታቸው ተዋደው፤ ከምንም ነገር በላይ ሰብዓዊነታቸውን አስቀድመው፤ ጥላቻን፣ ሰዎችን ማንቋሸሽ፣ ሰዎችን በማንነታቸው ማሸማቀቅን፣ መግፋትን፣ ሰዎችን በሰውነታቸው አለማክበርን #ተፀይፈው "ነጩን የሰላም ምልክት፣ባንዲራ ተሸክመው ለሀገራች ህዝቦች ተስፋ የሚሰጥ እንቅስቃሴ አድርገው ነበር።
ለሀገራቸው ሰላም እና ፍቅር ቀና አስበው፤ ያለ አንዳቸው የግለሰብም ሆነ የድርጅት ድጋፍ፣ የትምህርት ጊዜያቸውን ሰውተው፤ ረጃጅም ጉዞዎችን እየተንገላቱ ተጉዘው፤ ከቤተሰባቸው ከሚላክላቸው ገንዘብ ቀንሰው ለጉዞ አውለው፣ ከራሳቸው ኪስ አውጥተው ተመገበው፣ የሚስማማቸውን ምግብ ካገኙ በልተው ከሌለም ፆም አድረው፤ ለፍቅር እና ለሰላም ሲሉ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል። እንደ አንድ #ዜጋ ከራሳቸው የሚጠበቀውን በዚህ እድሜያቸው አድርገዋል። የህሊና ተወቃሽ ከመሆንም ድነዋል። ሁሌም ለሰው ልጅ ባላቸው ቀና አመለካከት ስናከብራቸው እና ስናወድሳቸው እንኖራለን።
የአንድ እናት ልጆች ነን መስመር አይለየን🇪🇹
የአንድ ቤት ልጆች ነን መስመር አይለየን🇪🇹
.
.
"ሁላችንም ወንድማማቾች ነን!"
"ሁላችንም እህትማማቾች ነን!"
"Nuti Hunduu OBBOLEEWWANI"
#Jimma #Wollo #Haramaya #DebreBrihan #Mekelle #Woldia #ArbaMinch #Hawassa #WolitaSodo #Wachamo #Wolkite
የቲክቫህ ቤተሰቦች ትውስታ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ለሚመለከታችሁ አካላት!
ወደ ደሴ በሚወስደው መንግድ-ደብረ ሲና መድረሻ መንገድ ላይ - መንገዱ በወደቀ ዛፍ እና ጭቃ በመዘጋቱ በርካታ መኪኖች ማለፍ አልቻሉም። እስካሁን ድረስም የተዘጋውን መንገድ ለመክፈት ከፍተኛ ርብርብ እና መኩራ እየተደረገ ቢሆንም አልተሳካም የሚመለከታችሁ አካልት መፍትሄ ትፈልጉ ዘንድ መንገደኞች ጠይቀዋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

#2
ለሚመለከታችሁ አካላት!
ከወለንጪቲ ወደ መተሃራ መውጫ - እና - ከመተሃራ ወደ ወለንጪቱ መግቢያ ላይ ሁለት ተሳቢ ተሽከርካሪዎች ተጋጭተው መንገድ ተዘግቷል። በርካታ መንገደኞችም እየተጉላሉ ነው። የሚመለከታቸው አካላት መፍትሄ ይፈልጉ። በነገራችን ላይ በግጭቱ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለሚመለከታችሁ አካላት!
ከወለንጪቲ ወደ መተሃራ መውጫ - እና - ከመተሃራ ወደ ወለንጪቱ መግቢያ ላይ ሁለት ተሳቢ ተሽከርካሪዎች ተጋጭተው መንገድ ተዘግቷል። በርካታ መንገደኞችም እየተጉላሉ ነው። የሚመለከታቸው አካላት መፍትሄ ይፈልጉ። በነገራችን ላይ በግጭቱ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኦሮሚያ እና የአማራ ወጣቶች የጋራ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው!
በኦሮሚያ እና በአማራ ባለሃብቶች ኮሚቴ አስተባባሪነት እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ መድረክ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ ወጣቶች በሀገራዊ ጉዳዮች፣ በሁለቱ ክልሎች ህዝቦች ግንኙነትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ፡፡
የኦሮሚያ እና የአማራ ባለሃብቶች ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ፍሬዓለም ሽባባው ውይይቱ በሁለቱ ክልል ወጣቶች መካከል ያሉ ልዩነቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት አባቶች፣ ፖለቲከኞች፣ ባለሃብቶችና አክቲቪስቶች ውይይት ማካሄዳቸው ይታወሳል፡፡
(EBC)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaBot

- ደብረ ሲና መዳረሻ አካባቢ የተዘጋውን መንገድ ለመክፈት ርብርብ እየተደረገ ይገኛል! መንገዱ በመዘጋቱ በርካታ ተሽከርካሪዎች ቆመዋል።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች!
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች!
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በድንገተኛ ናዳ ምክንያት የተዘጋውን የጣርማበር መንገድ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ ነው!
በዛሬው እለት በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ሳብያ ጣርማበር አካባቢ የመሬት ናዳ ተከስቶ መንገዱን በመዝጋቱ ትራንስፖርቱ ተቋርጧል። በአሁን ሰአት የተዘጋውን መንገድ ለመክፈት የኢትዮጽያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ቦታው ላይ ማሽኖችን አሰማርቶ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው።
ከሁለት ሰአታት በኋላም የተዘጋውን መንገድ ክፍት እንደሚደረግና መደበኛ የትራንስፖርቱ እንደሚጀመር የኢትዮጽያ መንገዶች ባለስልጣን ኮምኑኬሽን ዳይሬክቶሬት ይገገልጻል። አሽከርካሪዎችም መንገዱ እስኪከፈት በትእግስት እንዲጠባበቁ የባለስልጣኑ መ/ቤት ትብብራችሁን ይጠይቃል።
(የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዛሬው እለት በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ሳብያ ጣርማበር አካባቢ የመሬት ናዳ ተከስቶ መንገዱን በመዝጋቱ ትራንስፖርቱ ተቋርጧል። በአሁን ሰአት የተዘጋውን መንገድ ለመክፈት የኢትዮጽያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ቦታው ላይ ማሽኖችን አሰማርቶ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው።
ከሁለት ሰአታት በኋላም የተዘጋውን መንገድ ክፍት እንደሚደረግና መደበኛ የትራንስፖርቱ እንደሚጀመር የኢትዮጽያ መንገዶች ባለስልጣን ኮምኑኬሽን ዳይሬክቶሬት ይገገልጻል። አሽከርካሪዎችም መንገዱ እስኪከፈት በትእግስት እንዲጠባበቁ የባለስልጣኑ መ/ቤት ትብብራችሁን ይጠይቃል።
(የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ህዳር14 #ኮሞሮስ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሞሮሱ አደጋ....
ህዳር 14/1989 ዓ.ም ልክ በዛሬዋ ቀን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 767-260ER አውሮፕላን በዋና ካፒቴን ልዑል አባተና በረዳት አብራሪው ዮናስ መኩሪያ እየተመራ 175 ተጓዦችንና የበረራ ቡድን አባላትን በመያዝ ወደ ናይሮቢ ለመጓዝ ነበር ከአዲሰ አበባ ተነሳ፡፡
በጉዞው መሃል ሦስት ኢትዮጵያዊያን ሰዎች አውሮፕላኑን በመጥለፍ "አውስትራሊያ አድርሱን ካልሆነ ይህን ቦምብ እናፈነዳዋለን" አሏቸው፡፡ ነገር ግን አውሮፕላኑ ናይሮቢ የሚያደርሰውን ነዳጅ ብቻ ሞልቶ ነበር የተነሳው፡፡ ታዲያ ወደ መጀመሪያ መዳረሻው ናይሮቢ የሁለት ሰዓት ተኩል ጉዞ ለማድረግ የተነሳው አውሮፕላን ከአራት ሰዓት በላይ አየር ላይ በመቆየቱ ነዳጁን ጨረሰ በመጨረሻም በህንድ ውቅያኖስ በኮሞሮስ ደሴት ውሃ ላይ ተከሰከሰ፡፡ በአደጋው 125 ሰዎች ሲሞቱ ሁለቱን አብራሪዎችን ጨምሮ 50 ሰዎች ተርፈዋል፡፡ ሶስቱ ኢትዮጵያውያን ጠላፊዎችም ከሞቱት መካከል ናቸው።
በጊዜው "የጠላፊዎቹን ከፍተኛ የአካልና የአዕምሮ ጥቃት" ተቋቁመው ውሃ ላይ ማሳረፍ በመቻላቸው ካፒቴን ልዑል አባተና ረዳት አብራሪው ዮናስ መኩሪያ ከፍተኛ አድናቆት አግኝተው ነበር፡፡ እሁድን 23 ዓመታት ወደኋላ ተመልሶ ያስቃኘንን BBC የአማርኛ ክፍል ዝግጅት አመሰገንን፡፡

በድንገተኛ ናዳ ምክንያት የተዘጋው የጣርማበር መንገድ ለትራፊክ ክፍት ሆነ!
መንገዱ የተከፈተው የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ባደረኩት ርብርብ ነው ብሏል። እንደሚታወቀው ጣርማበር አካባቢ በጣለው ዝናብ የመሬት ናዳ ተከስቶ መንገዱን መዝጋቱና ለመክፈት ርብርብ እየተደረገ እንደሆነ ገልፀን ነበር።
በዚህም ሳብያ ትራንስፖርቱ ተቋርጦ የነበረ ሲሆን በአሁን ሰአት መንገዱ በተደረገለት ማስተካከያ መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ገልጿል። ባለስልጣን መስሪያ አሽከርካሪዎችና የመንገዱ ተጠቃሚዎች መንገዱ ክፍት እስኪሆን ላሳዩት ትእግስት ምስጋናውን አቅርቧል።
(የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
መንገዱ የተከፈተው የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ባደረኩት ርብርብ ነው ብሏል። እንደሚታወቀው ጣርማበር አካባቢ በጣለው ዝናብ የመሬት ናዳ ተከስቶ መንገዱን መዝጋቱና ለመክፈት ርብርብ እየተደረገ እንደሆነ ገልፀን ነበር።
በዚህም ሳብያ ትራንስፖርቱ ተቋርጦ የነበረ ሲሆን በአሁን ሰአት መንገዱ በተደረገለት ማስተካከያ መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ገልጿል። ባለስልጣን መስሪያ አሽከርካሪዎችና የመንገዱ ተጠቃሚዎች መንገዱ ክፍት እስኪሆን ላሳዩት ትእግስት ምስጋናውን አቅርቧል።
(የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ጋሕዴን የውህደቱን አጀንዳ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ!
የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋሕዴን) ዛሬ በጠራው አስቸኳይ ጉባኤ ወደ ብልጽግና ፓርቲ ለመዋሐድ ወስኗል። የጋሕዴን ሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ ላክዴር ላክባክ ለአብመድ በስልክ እንደገለጹት በሀገራዊ ጉዳይ ላይ እኩል የመወሰን መብት ለማግኘት በተደጋጋሚ ሲጠይቅ የቆዬው ጋሕዴን የውሕደት አጀንዳውን ዛሬ በጠራው አስቸኳይ ጉባኤ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
(AMMA)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiBot

የአሊባባ ኩባንያ መስራች እና ሊቀመንበር ጃክ ማ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ይገባሉ!
የአሊባባ ኩባንያ መስራች እና ሊቀመንበር ጃክ ማ ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ታውቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ ወደ ቻይና በሄዱበት ወቅት ከጎበኟቸው ተቋማት አንዱ የአሊባባ ዋና መስሪያ ቤት መሆኑ ይታወሳል። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ያደረጉላቸውን ግብዣ ተከትሎ ጃክ ማ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡ ጃክ ማ ከሌሎች ትላልቅ ኢንቬስተሮች ጋር በመሆን እንደሚመጡ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ትዊተር ላይ አስፍረዋል፡፡
(ኢቢሲ)

ኤምባሲው "በነፍስ ማጥፋትና ተያያዥ ወንጀል" የተከሰሱትን አራት ኢትዮጵያውያን ፍርደኞች የይግባኝ ጥያቄያቸውን ፍርዱን ላስተላለፈው ፍ/ቤት እንዲቀርብ አድርጓል!
በሳዑዲ አረቢያ ማረሚያ ቤት ሁለት ኢትዮጵያውያን ዜጎቻችን በነፍስ ማጥፋት ወንጀል ተከሰው ሰሞኑን የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው መሆኑ እና ጉዳዩ የሚመለከተው የኤምባሲው ባልደረባ የሞት ፍርድ የተላለፈባቸውን ሁለት ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ሠዒድ ሙሀመድ እና ያህያ አሊ ጎብኝቶ፣ በጉዳያቸውም ከእነዚሁ ፍርደኛ ዜጎቻችን እና ከማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጉ ይታወሳል፡፡ የኤምባሲው ተወካይ የሞት ፍርድ ከተላለፈባቸው ዜጎች በተጨማሪ የሃያ ዓመት እስራት የተላለፈበትን ሱልጣን ሙሀመድ እና የአራት አመት እስራት ፍርድ የተፈረደበትን ኢብራሂም አሊን መጎብኘቱም ይታወቃል፡፡
More👇
https://telegra.ph/ETH-11-24

የማስታወቂያ አግልግሎት ከመጪው ረቡዕ ይጀምራል!
ከሰሞኑን በሀገራችን ተፈጥሮ ከነበረው ችግር፤ በተለይም በተወሰኑ ዩንቨርስቲዎቻችን ውስጥ ተፈጥሮ ከነበረው ችግር ጋር በተያያዘ አጠቃላይ የማስታወቂያ አገልግሎት ማቋረጣችን ይታወቃል። ሁሌም በሀገራችን ውስጥ በየትኛውም ቦታ የሚፈጠሩ ችግሮች የሁላችንንም ስሜት የሚረብሹ በመሆናቸው መሰል ውሳኔዎችን እናሳልፋለን። ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ አድርገናል። አሁንም ያሉ ችግሮች በዘላቂነት እንዲፈቱ ጥሪ እናቀርባለን። የተቋረጠው የማስታወቂያ አገልግሎት ከመጪው ረቡዕ ይቀጥላል።
ሰላም ለሀገራችን ዜጎች!
እናመሰግናለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia

በምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ገለጸ!
የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው አለሙ እንዳሉት አደጋው ትናንት ከምሽቱ 12፡20 ላይ የደረሰው በዱግዳ ወረዳ ገርቢ ቆርኬ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ነው።
ከባቱ ወደመቂ ከተማ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ (ኮድ 3-81008 አ.አ) የሆነ አይሱዚ የጭነት መኪና ከመቂ ወደባቱ ይጓዝ ከነበረ (ኮድ 1-61506 ኦ.ሮ) ባጃጅ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ አደጋው መከሰቱን ግልጸዋል።
በአደጋው የባጃጁ አሽከርካሪን ጨምሮ በውስጡ የነበሩ አራት ሰዎች ሕይወታቸው ወዲያውኑ ሲያልፍ ሌሎች ሦስት የባጃጁ ተሳፋሪዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።
ኮማንደር አስቻለው እንዳሉት በአደጋው ሕይወታቸው ካለፈው ሰዎች ውስጥ ሁለቱ ሴቶች ናቸው። ከባድ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሦስቱ ግለሰቦችም በባቱ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን አመልክተዋል።
ባጃጁ ከአቅም በላይ ሰባት ሰዎችን አሳፍሮ መጓዙ እና የጭነት መኪናው ከፍጥነት በላይ በማሽከርከር በተፈጠረ የጥንቃቄ ጉድለት አደጋው ሊከሰት መቻሉን ኮማንደር አስቻለው አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት ያልተጠበቀ ዝናብ እየጣለ በመሆኑ አሽከርካሪዎች የመኪና ፍሬንና የዝናብ መጥረጊያ በአግባቡ መስራቱን ከማረጋገጥ ባለፈ በጥንቃቄ መጓዝ እንዳለባቸው ኮማንደር አስቻለው አስገንዝበዋል።
(ENA)

ሌላ አሳዛኝ ዜና...
"ከአዲስ አበባ ወደ አምቦ እየሄደ የነበረ ሚኒባስ ከከባድ መኪና ጋር ከወልመራ አለፍ ብሎ ያለ ገደላማ ቦታ ተጋጭተው የሰዎች ህይወት አልፏል። በቦታው ነበርኩ መንገድም ለ1 ሰአት ያክል ተዘግቶ ነበር።" የቲክቫህ ቤተሰብ አባል(YEDU)
ተጨማሪ መረጃዎች ይኖሩናል!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ከአዲስ አበባ ወደ አምቦ እየሄደ የነበረ ሚኒባስ ከከባድ መኪና ጋር ከወልመራ አለፍ ብሎ ያለ ገደላማ ቦታ ተጋጭተው የሰዎች ህይወት አልፏል። በቦታው ነበርኩ መንገድም ለ1 ሰአት ያክል ተዘግቶ ነበር።" የቲክቫህ ቤተሰብ አባል(YEDU)
ተጨማሪ መረጃዎች ይኖሩናል!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE
በትግራይ የሚካሄዱ የተፈጥሮና የአካባቢ ጥበቃ ልማት ስራዎችን ከስዊድን ዘላቂ ልማት ማህበር ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተደርጓል። ስምምነቱን የፈረሙት የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አትንኩት መዝገቦ እና የልማት ማህበሩ ፕሬዚዳንት ሚስተር ተርብጆርን ላህቲ ናቸው፡፡

189 የቱርክ ሽጉጥ በቁጥጥር ስር ዋለ!
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ የአማራ ልዩ ሃይል እና የሳንጃ ግምሩክ ባለሙያዎች በጋራ ባደረጉት ፍተሻ 189 ስምንት ጎራሽ የቱርክ ሽጉጥና 40 መሰል የሽጉጥ ጥይት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል፡፡
የአማራ ልዩ ሃይል ረዳት ሳጅን ወርቁ ሙሃባው እንደገለፁት ኮድ ሁለት አአ B44463 የሆነ ተሸከርካሪ መነሻውን ከምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ በማድረግ ወደ ጎንደር ከተማ ለማድረስ በሳንጃ ከተማ ሳንጃ ኬላ ላይ በተደረገ ፍተሻ መያዙን ተናግረዋል፡፡
በወቅቱ የተያዘው ሞትባይኖር ደምል የተባለው አሽከርካሪ እንዳለው ‹ደላላ በ1,500 ብር ከአብርሃጅራ ጎንደር አድርስ ብሎኝ ነው፤ ተሽከርካሪው ምን እንደያዘና የማን እንደሆነ አላውቅም›› የሚል ቃል የሰጠ ሲሆን በቁጥጥር ስር ውሎ ለወረዳው ፖሊስ ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡
በግምሩክ ባለሙያዎች እና በልዩ ሃይል አባላት ጥብቅ ፍተሻ ህገ ወጥ የጦር መሳርያው እንደተያዘ የተናገሩት ረ/ሳጅኑ ህብረተሰቡ እንዲህ አይነት ነገሮች ሲመለከት ጥቆማ እንዲያደርግና ከጎናቸው እንዲሆን ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
(የታች አርማጭሆ ኮሙዩኒኬሽን)

ማንኛውም ዜጋ የፓስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ከቀበሌ መታወቂያ በተጨማሪ የልደት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት!
የልደት ምስክር ወረቀት ከየት ይወጣል?
• ለህፃናት የልደት ምስክር ወረቀት ለማውጣት ከወላጆች አንዱ በነዋሪነት የተመዘገበቡበት ቀበሌ ሁለቱም ወላጆች ህፃኑ/ኗን ይዘው በመቅረብ ማውጣት ይችላሉ፡፡
• ከ18 አመት በላይ የሆነ ሰው ለተለያዩ አገልግሎቶች የልደት ምስክር ወረቀት በሚፈልግበት ጊዜ በነዋሪነት ወደተመዘገበበት እና መታወቂያ ወደተሰጠበት ቀበሌ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ፅ/ቤት በመሄድ ተመዝግቦ የልደት ምስክር ወረቀት ማግኘት ይችላል፡፡
የልደት ምስክር ወረቀት መቼ ማውጣት ይቻላል?
• ለለህፃናት ከተወለዱበት ቀን ጀምሮ እስከ 90 ቀናት ድረስ በመደበኛ የምዝገባ ጊዜ ውስጥ ተመዝግበው ቢያወጡ እንደሃገር ለሚሰበሰበው መረጃ ከፍተኛ ጠቀሜታን ይሰጣል፡፡
• አዋቂዎች በማንኛውም ጊዜ በቀበሌ የስራ ቀን እና ሰአት በመሄድ ማውጣት ይቻላል
በገጠሪቱ የሃገሪቱ ክፍል የልደት ምስክር ወረቀት እንዴት ይገኛል?
ከላይ እንደተገለፀው በማንኛውም የሃገሪቱ ክፍል ባሉ ቀበሌዎች የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራ በማከናወን ላይ ስለሚገኙ በነዋሪነት ወደተመዘገቡበት ቀበሌ በመሄድ የልደት ምስክር ወረቀት ማግኘት ይቻላል፡፡
ማስታወሻ፡- ማንኛውም ዜጋ ፓስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ከቀበሌ መታወቂያ በተጨማሪ የልደት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት
(FDRE Immigration Nationality And Vital Events Agency)
@tikvahethiopia @tsegabwolde