TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የመንግስት_ማስጠንቀቂያ

የኢትዮጵያ መንግስት ሀገርን ለማፍረስ የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠነቀቀ።

ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ያወጣው የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሀገርን ለማፍረስ የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲል አስጠንቅቋል።

መንግስት በመግለጫው "የሽብር ቡድኑ ማሽኖችና በሽርክና የሚሰሩ ሚዲያዎች የሽብር ወሬ እያሰራጩ ናቸው" ብሏል። ቁልፍ ኢላማቸው ደግሞ በአመራሩና ፣ በህዝቡና በወገን ጦር መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠር ፍርሃትም እንዲነግስ ማሸበር ነው ሲል ገልጿል።

በተለያየ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ ያሉ ተላላኪዎቻቸው የፀጥታ ችግር እንዳለ በማስመሰል የግል ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ የማግባባት ስራ እየሰሩ ይገኛሉም ብሏል።

በህዝቡና በወገኑ ጦር ውስጥ ጥርጣሪዎችን ለመፍጠር የመንግስት ባለስልጣናት ቪዛ እየጠየቁ ነው በሚል የውሸት ፕሮፓጋንዳ እየነዙ ናቸውም ሲል ገልጿል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን በመግለጫው ከዲፕሎማሲ መርህ ውጪ የአንዳንድ ሃገር ኤምባሲዎች አዲስ አበባ እንደ ተከበበች በማስመሰልና ያሰቡት ውጥን እንዲሳካ በኤምባሲያቸው የሚሰሩ ዜጎቻቸው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እያሳሰቡ ይገኛሉ ብሏል።

በእንዲህ አይነት መንገድ ሀገርን ለማፍረስ የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰበው መንግስት በሀገር ጉዳይ ቀልድ የለምና ከድርጊቱ ባልተቆጠቡት ላይ የማያዳግም ርምጃ ይወሰዳል ሲል አስጠንቅቋል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#የመንግስት_ማስጠንቀቂያ

የፀጥታና ደኅነት የጋራ ግብረ–ኃይል ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተከሰተውን ወቅታዊ ሁኔታ መገምገሙን ገልጿል።

አለመግባባቱን ለመፍታት የሚደረገው ጥረት በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሚፈጸም የጸና እምነት አለኝ ብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ " በእምነቱ አባቶች በተመሳሳይ ቀንና ቦታ ሕገወጥ የሰልፍ ጥሪ በማድረግ የዜጎች ህይወት የሚቀጠፍበት አጋጣሚ እንዲፈጠር ቅስቀሳዎች እየተደረጉና ሌሎችም ግጭት ቀስቃሽተግባራት እየተፈፀሙ መሆኑን ማረጋገጥ ችያለሁ " ብሏል።

ግብረሃይሉ ሰልፎቹ በሃይማኖቱ ሽፋን የሚደረጉ እና ሕገወጥ ሰልፎች ናቸው ያለ ሲሆን " በሚመለከተው አካል የተፈቀደ ሰልፍ የሌለ መሆኑ ታውቆ ኅብረተስቡ ከዚህ ሕገ ወጥ ሰልፍና ግጭት ቀስቃሽ ተግባራት ራሱን ይጠብቅ " ብሏል።

የጋራ ግብረ-ኃይሉ " ከዚህ ውጭ ሰልፍ አደርጋለሁ ብሎ በሕገ ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ኃይል እንዲሁም ሰልፎቹን ለማስተባበር እና ለመሳተፍ የሚሞክሩ አካላት ለሚደርሰው ማንኛውም ጉዳት ተጠያቂ ናቸው " ያለ ሲሆን " ለዜጎችና ለሀገር ሰላምና ደኅንነት መረጋገጥ ሲባል ሕጋዊእርምጃ ይወሰዳል " ሲል አስጠንቅቋል።

ግብረ ኃይሉ " በየክልሉ የምትገኙ የፀጥታ ኃይሎችም በአካባቢያችሁ ሕገወጥ ሰልፎች እንዳይካሄዱ አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያኗ፣ለእምነቱ አባቶች እና ተከታዮች በአጠቃላይ ለሕዝቡ ተገቢውን የደኅንነት ጥበቃ እንድታደርጉ " ሲል አዟል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia