TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GRD

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት በግድቡ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መግለጫ በዛሬው ዕለት ሰጥቷል፡፡ በመግለጫው የሕዝቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተነግሯል፡፡

ህብረተሰቡ ለግድቡ ግንባታ መሳተፍ ከጀመረ ወዲህ 13 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡና በተያዘው በጀት ዓመት ሩብ ዓመት ብቻ ደግሞ 168 ሚሊዮን 952 ሺህ ብር መሰብሰቡ ተገልጿል፡፡

በመስከረም ወር ብቻ 82 ሚሊዮን ብር የተሰበሰበ ሲሆን ፤ ወደ ፊትም የሕዝቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እንደሚጠበቅና ለዚህም እንደሚሠራ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሃይሉ አብርሃም አስታውቀዋል፡፡

(ዋልታ ቴሌቪዥን)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#GRD

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አካል የሆነው የኮርቻ ቅርፅ ግድብ ሙሌት ስራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የታላቁ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ በላቸው ካሳ እንደገለፁት፥ ቀደም ሲል ከ14 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ በላይ የድንጋይ ጥቅጥቅ ሙሌት ስራ ተከናውኗል።

ከኮርቻ ግድቡ ቀሪ ስራዎች መካከል 30 ሳንቲ ሜትር ሙሌት ይፈልግ የነበረው የላይኛው አርማታ ሙሌት (ፌስ ስላብ) ስራ ዛሬ ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቁንም ገልፀዋል።

ይህም ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራዎች መካከል አንዱ ወሳኝ ስራ መጠናቀቁን እንደሚያሳይ አስታውቅዋል።

በኮርቻ ግድብና በዋናው ግድብ ላይ አተኩሮ ሲሰራ የነበረው የሲቪል ስራ የኮርቻ ግድቡ በመጠናቀቁ ዋናውን ግድብ በፍጥነት ለማጠናቀቅ ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን አቶ በላቸው ተናግረዋል። ኮርቻ ግድቡ 5 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 50 ሜትር ቁመት ያለው መሆኑን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

(FBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GRD

በሕዳሴው ግድብ ውሃ አሞላል እና የግድቡ አተገባበር ላይ በካርቱም የተካሄደው የሦስትዮሽ ውሃ ሚንስትሮች ስብሰባ ተጠናቋል፡፡ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ አሁንም ስምምነት አልተደረሰም፡፡ በድርቅ ትርጓሜ እና በድርቅ ጊዜ ግድቡ እንዴት እንደሚያዝ ግን መቀራረብ እንደተፈጠረ የሱዳኑ ውሃ ሚንስትር እንደተናገሩ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ቀጣዩ ስብሰባ በአዲስ አበባ ታህሳስ 30 እና ጥር 1 ይካሄዳል፡፡

(WazemaRadio)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GRD

በኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ሰሞኑን በሱዳን ካርቱም የተካሄደው የሶስትዮሽ ውይይት ውጤታማ እንደነበር የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ገለፁ።

ሚኒስትሩ ዶክተር ስለሺ በቀለ የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የውሃ ሚኒስትሮች በካርቱም ያካሄዱት ውይይት ውጤታማ እንደነበር ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድና የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታ አልሲሲ በሩሲያ ሶቺ ከተማ ተገናኝተው ግድቡን በተመለከተ አራት ድርድሮችን ለማካሄድ ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል።

https://telegra.ph/ETH-12-24

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia