TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የነቢዩ ሙሐመድ (ሠዓወ) የልደት በዓልን አስመልክቶ ለመላው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት።

#PMOEthiopia

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የስልጤ ዞን ምክር ቤት አቶ አሊ ከድርን የዞኑ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ። ምክር ቤቱ 4ኛ ዙር 5ኛ አስቸኳይ ጉባኤዉን ትላንት በወራቤ ከተማ አካሂዷል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SUDAN

•የሱዳን ዩኒቨርሲቲ በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ሊያስተምር ነው!

•ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ዓረብኛ ቋንቋን ይሰጣል
!

በሱዳን ካርቱም የሚገኝው ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲ ኦፍ አፍሪካ በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ በዲግሪ ደረጃ ለማስተማር ስምምነት ላይ መድረሱ ተገለፀ። ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲም ዓረብኛ ቋንቋን በዲግሪ ደረጃ ሊሰጥ ነው።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሂዩማኒቲስ ቋንቋዎች ጥናት ጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ኮሌጅ ዲን ዶክተር አማኑኤል አለማየሁ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በተገባደደው በጀት ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ፣ ከኮተቤ ሜትሮፖሊታን እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጣ አንድ ልዑክ ቡድን ወደ ሱዳን አቅንቷል።

ልዑኩ ከሱዳኑ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ጋር ባደረገው ውይይት የአማርኛና የአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎችን በሱዳን ዩኒቨርሲቲ እንዲሰጥና የዓረብኛ ቋንቋን ደግሞ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ እንዲሰጥ የሁለትዮሽ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

(የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#CONGRATULATIONS

በአሁን ሰዓት "ጎንደር ዩኒቨርስቲ" የህክምና ተማሪዎቹን በደማቅ ሁኔታ እያስመረቀ ይገኛል፡፡ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የተማሪ ወላጆች፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine
#ደሴ

በህገ ወጥ መንገድ 19 ወጣቶችን ወደ አረብ ሀገር ለማስወጣት የሞከሩ ግለሰቦች ደሴ ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ። ህጻናትና ወጣቶችን ወደ የቤተሰቦቻቸው ለመመለስ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑንም ፖሊስ ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
🕌 እጅግ የምናከብራችሁና የምንወዳችሁ ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሆናችሁ ቤተሰቦቻችን እንኳን 1 ሺህ 494ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ በዓሉ የሰላም፣ የመረዳዳት የመደጋገፍ በዓል እንዲሆንልን እንመኛለን መልካም በዓል🕌

#TIKVAH_ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HappeningNow

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሰላማዊ መማር ማስተማርን በተመለከተ ከጅማ ከተማ ማህበረሰብ ጋር ውይይት እያካሔደ ይገኛል!

ጅማ ዩኒቨርሲቲ “የ2012 ዓ.ም ሰላማዊ መማር ማስተማር ሒደትን ማረጋገጥ” በተመለከተ ከጅማ ከተማ ማህበረሰብ ጋር በግብርና እና እንሰሳት ህክምና ኮሌጅ አዳራሽ ውይይት እያካሔደ ይገኛል፡፡

በውይይቱም የዩኒቨረርሲቲው የማኔጅመንት እና የካውንስል አባላት፣ የጅማ ከተማ መስተዳድር የስራ ሐላፊዎች፣ ከአባገዳዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የሐገር ሽማግሌዎች፣ ቄሮዎች እና ቃሬዎች በ2012 ዓ.ም ሠላማዊ መማር ማስተማር ሒደት ውይይት ላይ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

ውይይቱን እየመሩ የሚገኙት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ዩኒቨርሲቲው መደበኛ ስራውን እንዲፈጽም ሰላም ቀዳሚ መሆኑን አንስተው ሁሉም ተሳታፊዎች የበኩላቸውን እንዲወጡ አጽንኦት በመስጠት ውይይቱን እንዲያስጀምሩ ለከተማ መስተደድሩ ከንቲባ እድሉን ሰጥተዋል፡፡

የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ መክዩ መሐመድ በቡኩላቸው በመላው ሐገሪቱ የሚገኙ አባቶችና እናቶች ልጆቻቸውን አስረክበውናል፤ በመሆኑም የልጆቻችን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ሐላፊነት አለብን በማለት ከቀበሌ አመረር ጀምሮ፣ የከተማው መስተዳድር፣ የሐይማኖት ተቋማት የየድርሻቸውቸን ወስደው መስራት እንዳለባቸወው በመግለጽ ውይይቱን ለተሳታፊዎቸ ክፍት አድርገዋል፡፡

(ጅማ ዩኒቨርሲቲ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት አቶ ፍቅሬ አማንን ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ። ምክር ቤቱ ሹመቱን የሰጠው ትላንት በጀመረው አራተኛ ዙር ሰባተኛ ዓመት አስቸኳይ ጉባኤ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የ2019 የሰላም ኖቤል ሽልማትን ተከትሎ በደቡብ አፍሪካ የሚታተመው The Diplomatic Society መጽሔት በኖቬምበር 2019 እትሙ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የፊት ገጽ ሽፋን ሰጥቷቸዋል፡፡ ሽልማቱን አስመልክቶ በኢፌዴሪ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተደረገው አከባበር በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማሪያም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን አካታች፣ ውጤታማ፣ ለህዝባቸው ቅርብ የሆኑና ለምስራቅ አፍሪካ ሰላም የሚተጉ በማለት የገለጹትን በማስቀደም ዘገባውን ጀምሯል፡፡ የእለቱን እንግዶች መልዕክትም አጠቃሎ አቅርቧል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews

በወላይታ እና ሲዳማ ዞኖች መካከል እልባት ባላገኙ 8 ወረዳዎች የምርጫ ጣቢያ እንዳይቋቋም ከስምምነት ተደረሰ የሚለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

በወላይታ እና ሲዳማ ዞኖች መካከል እልባት ባላገኙ 8 ወረዳዎች ላይ የህዝበ ውሳኔ ድምጽ መስጫ ምርጫ ጣቢያ እንዳይቋቋም ከስምምነት ተደረሰ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የምርጫ ቦርድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 አረጋግጧል።

የቦርዱ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ቦርዱ የሚያውቀው እንዲህ አይነት ስምምነት የለም፤ ጭምጭምታዎችንም ቦርዱ አይሰማም ብለዋል።

(ETHIO FM- ትዕግስት ዘላለም)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዕርቀ ሠላም ሥነ ስርዓት እየተከናወነ ነው!

በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ፣ ማጀቴ፣ ሸዋ ሮቢትና አካባቢው እንዲሁም በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ጅሌ ጥሙጋ እና አካባቢው ተከስተው የነበሩ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት የዕርቀ ሠላም ሥነ ስርዓት እየተከናወነ ነው። የእርቅ መድረኩ ከሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ ሰዎች በተገኙበት በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አላላ ቀበሌ ላይ እየተከናወነ የሚገኝ መሆኑን አብመድ ዘግቧል።

(AMMA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቃሉ ወረዳ #ደጋንና #ገርባ አካባቢዎች ባሉ ቀበሌዎች የሰብል ማሰባሰብ ተግባግ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ተሳታፊወችም፦

• የደሴ ከተማ ኡለሞች ምክር ቤት እና የደሴ ከተማ እስልምና ቦርድ

• የደሴ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች ማህበር

• የወሎ ኡለሞች ምክር ቤትና የወሎ እስልምና ቦርድ

• ሰላም የኮምቦልቻ ሙስሊም ወጣቶች ማህበር

• ወሎ ዩንቨርሲቲ

• የሀርቡ ሙስሊም ወጣቶች የዳእዋ ማእከል

• አማራ ብረታ ብረት

• የወሎ ኮምቦልቻ እግር ኳስ ክለብና ደጋፊ ማህበር

• የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር

• የኮምቦልቻ መሠናዶ ተማሪወችና መምህራን ተሳትፎ በማድረግ መጠነ ሰፊ የሰብል ማሰባሰብ ስራ እየሠሩ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትግራይ ደቡባዊ ዞን አንበጣ መንጋን ከመከላከሉ በተጓዳኝ የደረሰ "ሰብልን የመሰብሰቡ" ስራ #ተጠናክሮ ቀጥሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"ቃጠሎው የተነሳው ከቅኔ ማህሌቱ ሳይሆን ከመቅደሱ ውስጥ ነው፡፡ ማን አስነሳው እንዴት ተነሳ ሻማ አብርቶ የወጣው ዲያቆኑ ነው ወይስ ቄሰ ገበዙ ለምን ሳያጠፉ ወጡ የሚለው ከፖሊስ ምርመራ በኋላ አብረን የምናየው ይሆናል!" - የደብሩ ዋና አስተዳዳሪ መላከ ሰላም አባ ሳሙኤል . . በቀን 28/02/2012ዓ.ም ጥዋት 11 ሰአት ላይ በኮምቦልቻ መንበረ ሕይወት መድሐኒዓለም ቤተ ክርስትያን በደረሰው የእሳት…
ከደ/ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ወንጀል ምርመራ ዋና የስራ ሂደት ኮማንደር ለማ ተስፋየ በኮምቦልቻ ከተማ ቀበሌ 01 የመንበረ ህይወት መድሀኒያለም ቤተ-ክርስቲያን ቃጠሎ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ፦

ኮማንደር ለማ ተስፋየ የቤተ-ክርስቲያኑን ቃጠሎን በተመለከተ እንደተናገሩት በቀን 27/2/2012 ከሌሊቱ 11፡30 በውጭ ቤቱ ተዘግቶ ቤተ-መቅደስ ውስጥ የእሳት ቃጠሎ ደርሷል ብለዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ በወቅቱ ጥሪ የተደረገላቸው የፀጥታ ሀይልና ሌሎች የአደጋ ተከላካይ ሀይሎች ተረባርበው ለማጥፋት ችለዋል ብለዋል፡፡

እንደ ኮማንደር ገለፃ በቤት ውስጥ ያሉ አንዳንድ እቃዎች በቃጠሎው ምክንያት የወደሙ በመሆኑ የኮምቦልቻና የደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ መርማሪዎች በጋራ በመሆን የቃጠሎውን መነሻ ሁኔታ በማጣራት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡ የቃጠሎው መነሻ ከጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ በመሆኑ መጠቀሚያ የሆኑ ጧፍና ሻማ በጥንቃቄ ካለማጥፋት የተነሳ የተከሰተ ክስተት የሚመስል መሆኑን በአብዛሀኛው ምርመራው ያመላክታል ብለዋል፡፡

ቃጠሎው የሚያሳየው በወቅቱ በተገቢው መንገድ እሳቱን አጥፍቶ አለመሄድ ላይ ጉድለት እንደነበረና ሀላፊነትን በአግባቡ ካለመወጣት የተነሳ በአጠቃላይ ከቤተክርስቲያኗ ውጭ ከሌሎች ጥቃት እንዳልተሰነዘረባት ለመረዳት ተችሏል ብለዋል፡፡ ለዚህም ትናንትና ማታ እስከ 2፡30 ድረስ ሲጠቀሙበት ቆይቶ ምዕመናኑ ከዚያ ወጥቶ እና አድሮ ሌሊት ላይ ምንም የተሰበረ በርና መስኮት አለመኖሩ ተረጋግጧል፡፡

በመሆኑም ምንጩን ለማግኝት የተለያየ ፎቶና መረጃዎችን እየሰበሰቡ መሆንኑ በመግለጽ በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገጽ እንደሚባለው የገዘፈና ከሌሎች ወገኖች ጥቃት ያልደረሰ መሆኑን ለመረዳት ችለናል ብለዋል፡፡ በቃጠሎው የደረሰውን ጉዳት በማጣራት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚያሳውቁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

@tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ ተቋማት ከግዥ አዋጅ መመሪያ ውጭ የተፈፀመ ከ529 ሚሊየን ብር በላይ በኦዲት ተገኝቷል!

- ለአንድ ኃላፊ የግል ችግር ዕርዳታ በሚል 125 ሺህ ብር ተሰጥቷል

- ከደንብና መመሪያ ውጭ ከ532 ሺህ ብር በላይ አበልና ደመወዝ ተከፍሏል

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ ተቋማት ከግዥ አዋጅ መመሪያ ውጭ የተፈፀመ ከ529 ሚሊየን ብር በላይ ክፍያ መኖሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ባቀረበው የኦዲት ሪፖርት መሰረት፤ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ በ27 ተቋማት ላይ በተደረገ የኦዲት ምርመራ 529 ሚሊየን 105 ሺህ ብር ከግዥ አዋጅ መመሪያ ውጭ ክፍያ መፈፀሙ ተረጋግጧል።

በተለይ የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ትልቁን ድርሻ በመያዝ የ467 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ከመመሪያ ውጭ ክፍያ የፈፀመ ተቋም ሆኗል። የትራንስፖርት ባለሥልጣን እና መንገዶች ባለሥልጣን በ2010 ዓ.ም በድምሩ ከ40 ሚሊየን ብር በላይ ከአዋጅ ውጭ ክፍያ መፈፀማቸው በሪፖርቱ ቀርቧል።

(EPA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
(ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር)

በምስራቅ ክፍለ ከተማ አንድ የምርጫ ጣቢያ አከባቢ ሲጠጉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በፀጥታ ሀይል ቁጥጥር ስር ዋሉ!

የሲዳማ ብሔር በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱ ተረጋግጦ ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የሚካሄድ መሆኑን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት የቅስቀሳ ስራ የተጀመረ ከመሆኑ በተጨማሪ በሀዋሳ ከተማ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች በሰለጠነ፣ በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የድምፅ ሰጪዎች የምዝገባ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

እነዚህ ስራዎች በሰላማዊ መንገድ ከመሄዳቸው ባሻገር የከተማው ህብረተሰብ ባደረጋቸው ውይይቶች ለሰላም ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን እና ይህ የሲዳማ ብሔር በክልል የመደራጀት ህዝበ ውሳኔ ህግን ተከትሎ ሰላማዊ እና በህዝብ ዘንድ ተዓማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ከመግለፅ አልፈው በአሁኑ ወቅት በተግባር እያሳዩ ይገኛል፡፡

በሀዋሳ ከተማ በ165 የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ ስራ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እየተከናወነ ባለበት በአሁኑ ወቅት ካሉት የምርጫ ጣቢያዎች አንዱ በሆነው በምስራቅ ክፍለከተማ ቴሶ ቀበሌ መንደር አራት የምርጫ ጣቢያ በምሽት ወደ ምርጫ ጣቢያ ለመጠጋት የሞከሩ ግለሰቦች በተደራጀ የፀጥታ ሀይል በቀላሉ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው፡፡

ወደ ምርጫ ጣቢያ መቅረባቸው ለምን ዓላማ እንደሆነ ተጣርቶ የሚገለፅ ቢሆንም የህዝበ ውሳኔው ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ህብረተሰቡ እና የፀጥታ ሀይሉ በቅንጅት እየሰሩ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ምንም አይነት ሂደቱን ሊያደናቅፍ የሚችል እንከን እንደማይኖርና እንደሌለ በመጠቆም ነዋሪው ያለምንም ስጋት የምዝገባ ሂደቱን መቀጠሉን እንገልፃለን።

(ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት)
ከ39 ሺ በላይ ተማሪዎች በአፋን ኦሮሞ እየተማሩ ነው!

በአዲስ አበባ ከ39 ሺ በላይ ተማሪዎች በአፋን ኦሮሞ እየተማሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ገለጸ። በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ውስጥ ባሉት በተለያዩ ክ/ከተሞች 39 ሺህ 365 ተማሪዎች በአፋን ኦሮሞ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡

(OBN)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
''ነብዩ መሀመድ አለም በአራት ነገሮች ተደግፋ እንደምትኖር ተናግረው ነበር፡፡ እነዚህም፡- የጠቢብ ሰው ትምህርት፣ የታላቅ ሰው ፍትህ፣ የመልካም ሰው ፀሎት እና የጀግና ሰው ተጋፋጭነት ናቸው፡፡ እነዚህ አራት ነገሮች የሀገራችንን ሰላምና ብልፅግና፣ የህዝባችንን ፍቅርና አንድነት ለመደገፍ በዚህ ሰዐት እጅግ አስፈላጊዎቻችን ናቸው፡፡''

(ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EliasMeseret #TikvahFamily

የቲክቫህ ቤተሰብ አባልና ዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ዛሬ ከምሽቱ 12:00-1:00 ድረስ የተመረጡ መረጃዎችን ለናተ ለውድ ቤተሰቦቻችን ያደርሳል!

መልካም ምሽት!

@tikvahethiopiaBot👈አስተያየት መቀበያ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኤልያስ መሰረት ለቲክቫህ

የደቡብ አፍሪካው ቴሌኮም ኩባንያ ቮዳኮም ቀጣዩን Women First የ5ኪሜ ሩጫ ውድድር ኢትይጵያ ውስጥ ስፖንሰር ያደርጋል!

"ኩባንያው ውድድሩን ስፖንሰር ሊያደርግ ያሰበው ኢትዮጵያ ውስጥ ለመስራት ኮንትራት አግኝቶ ወይስ ለወደፊቱ አስቦ?" ብዬ የፋይናንስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴታ የሆኑትን ዶ/ር እዮብ ተካልኝን ዛሬ ጠይቄ ነበር። እርሳቸው ሲመልሱም:

"እኛ ገና አማካሪ ድርጅት ነው የቀጠርነው፣ ስለዚህ እስካሁን የመረጥናቸው ድርጅቶች የሉም" ብለውኛል።

አንድ የኢትዮ ቴሌኮም የስራ ሀላፊ ደግሞ "ምናልባት ፍላጎታቸውን ለማሳየት ይሆናል። ባለፈው ግዜም MTN የተባለው ሌላ የውጭ የቴሌኮም ድርጅት እንዲሁ ስፖንሰር ኢትዮጵያ ውስጥ አድርጎ ነበር" ብለዋል።

እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን በኮሙኒኬሽን አገልግሎት አዋጅ መሠረት በግልጽ ውድድር ሁለት ተጨማሪ አዲስ ፈቃዶችን ለቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኦፕሬተሮች ለመስጠት አቅዷል፡፡ በዚህም መሰረት በሚቀጥለው አመት ሁለት አዳዲስ የቴሌኮም ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ስራ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@eliasmeseret @tikvahethiopia