TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባ ወደ ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም መራዘሙን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

(የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ)

#ሼር #share

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታዊ ባለሙያዎች 23ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ በኤርትራ ዋና ከተማ በአስመራ- ተከፈተ!
#Asmera

የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታዊ ባለሙያዎች 23ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ በኤርትራ ዋና ከተማ በአስመራ- ተከፈተ። በዚህ ለ3 ቀናት በሚቆየው ስብሰባ ከ250 በላይ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የመጡ ተወካዮችና አጋር የኢኮኖሚ ድርጅቶች፡ በቀጠናው አዲስ ውህደትና ትብብር ለመፍጠር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ።

(የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዓለም አቀፉ የስፖርት ጋዜጠኛ በቲክቫህ ስፖርት!

#TikvahSportFamily #FirewAsrat

ውድ የTIKVAH SPORT ቤተሰቦች ከፊትችን አርብ ጀምሮ የረጅም ጊዜ የቤተሰባችን አባል የሆነው በተለያዩ አለም አቀፍ እንዲሁም አህጉራዊ ዌብ ሳይቶች ላይ SOKA 25 EAST JW SPORT 1 ኬንያ ለጋናው FOOTY GHANA እንዲሁም የሩሲያው RFL በኢትዮጵያ ስፖርት ፀሀፊ ፍሬው አስራት በየሳምንቱ ያልተሰሙ እና ሊሰሙ ይገባቸዋል የሚባሉ ስፖርታዊ ሀተታዎችን ወደ እናንተ ውድ ቤተሰቦቻችን ባማረ አቀራረብ ማድረሱን ይጀምራል ።

ሰዓት፦ ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ

Join👇@tikvahethsport

https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg

@tikvahethiopiaBot👈አስተያየት መቀበያ!
#EthiopianAirlines #CBE

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ባሉበት ቦታ ሆነው ትኬት መቁረጥና ሌሎች የአገልግሎት ክፍያዎችን መፈጸም የሚያስችል የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር መሆኑን ገለጸ፡፡ አዲሱን የአገልግሎት አሰጣጥ መዘርጋቱን አስመልክቶ አየር መንገዱ እና ንግድ ባንክ በጋራ በመሆን በስካላይት ሆቴል መግለጫ ይሰጣሉ፡፡ በመግለጫውም የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስኪያጅ እና የንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት የሚገኙ ይሆናል ተብሏል፡፡ የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ የአየር መንገዱን አገልግሎት ቀልጣፋና ተገልጋዮችንም ከማያስፈልግ እንግልት ይታደጋል ተብሏል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Ethiopia #Tigray

በቃፍታ ሸራሮ ብሔራዊ ፓርክ ከትላንት በስቲያ ጀምሮ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱ ተገለፀ፡፡ እስካሁን ድረስ ቃጠሎው እንዳልቆመ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ቃፍታ ሸራሮ; በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር የሚገኝ ብሔራዊ ፓርክ ነው፡፡

ምንጭ፦ ሚሊዮን ኃይለስላሴ(ጀርመን ድምፅ ራድዮ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SIDAMA #HAWASSA

ህዳር 10 ቀን የሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ሰላማዊ፣ ነፃ፣ ዴሞክራሲያዊና በህዝብ ዘንድ ተዓማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ሀይሉ ሊሰራ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡ በህዝበ ውሳኔ ወቅት የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመፍታት ረገድ የፍትህ አካላትና የህዝብ ታዛቢዎች ሚናን በተመለከተ በሀዋሳ ከተማ ለታዛቢዎችና ለፀጥታ አካላት በትላንትናው እለት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethioia
#HAWASSA የሲዳማ ብሔር በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ምላሽ የሚያገኝበት ህዝበ ውሳኔ ቅስቀሳ ስራ በይፋ መጀመሩ ይታወቃል፡፡ ይህን ተከትሎ "ሲዳማ በአብሮነት የሚኖሩ ሌሎች ህዝቦችን በማቀፍ በክልልነት የመደራጀት ጥያቄውን በህዝበ ውሳኔ ለማረጋገጥ ይሰራል!" በሚል መሪ ቃል የሀይቅ ዳር ክፍለከተማ ቤሌማ የኪነ-ጥበብ ቡድን የቅስቀሳ ስራ አከናውኗል፡፡

PHOTO: የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጉባዔ ፕሬዚዳንት ብጹዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ሱራፌል ለመላው ካቶሊካውያን የጸሎት ቀን አወጁ፡፡ ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም የመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል ሲከበር በዕለቱ ሁሉም የቤተክርስቲያኗ ቁምስናዎችና ጸሎት ቤቶች ስለኢትዮጵያ ሰላም፣ ስለሞቱ፣ ስለተጎዱ፣ ስለተፈናቀሉ ወገኖች በጋራ በመሆን ለመጸለይ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ የጸሎት ቀን አውጀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአፋርና ሶማሌ የህዝብ ለህዝብ መድረክ!

በሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን የሃገር ሽማግሌዎችና አመራሮች ባለፈው ሳምንት የሰላም ሚኒስቴር ባዘጋጀው የአፋርና ሶማሌ የህዝብ ለህዝብ መድረክ ሶማሌዎች ተሳታፊ አልነበርንም ሲሉ ከሰሱ።

የሶማሌ ነዋሪዎች በሚበዙባት አና በአፋር ክልል ስር በምትገኘው አወዛጋቢዋ የአዳይቱ ወይም ገዳማይቱ ከተማ ላይ በተዘጋጀው መድረክ ላይ የፖለቲካ አመራሮችም፣ የኢሳ ጎሳ ኡጋዝም ሆነ የሃገር ሽማግሌዎች ተሳታፊ አልነበሩም፥ በተቃራኒው በዕለቱ በርካታ የኢሳ ሶማሌዎች ከተማዋን ለቅቀው እንዲወጡ መደረጋቸውንና የተወሰኑትም ታስረው እንደነበር አስታውቀዋል። የሰላም ሚኒስቴር ግን መድረኩ በሁለቱ ክልሎች መካከል ሳይሆን አፋር ክልል ውስጥ ባሉ አፋሮችና ኢሳዎች መካከል የተዘጋጀ ነው ብሏል።

ኮንፈረንሱ የተካሄደባት የአዳይቱ ከተማ አፋርና ሶማሌ ክልል በይገባኛል ከሚወዛገቡባቸው ሶስቱ ቀበሌዎች አንዷ ነች።

(የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአየር ንብረት ለውጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከሚያስፈልግበት ደረጃ መድረሱን ተመራማሪዎች አስታወቁ!

ከ11 ሺህ በላይ ዓለማቀፍ ተመራማሪዎች ባወጡት ጥናት እንዳመለከቱት ዓለም ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያስፈልጋታል፡፡

ለ40 ዓመታት የተደረገ ጥናት እንዳመላከተው መንግሥታት ለአየር ንብረት ለውጥ የሰጡት ምላሽ በጣም አነስተኛ ነው፡፡ በዚህ የተነሳም የሰው ልጅ የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው ፍጹም ተፅዕኖ የከፋ አደጋ ውስጥ ወድቋል፡፡
ተመራማሪዎቹ ከፊት ለፊት እየመጣ ያለውን ሥጋት የመግለጽና የማስጠንቀቅ የሞራል ኃላፊነት እንዳለባቸው በመግለጽ ነው መረጃን ይፋ ያደረጉት፡፡

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-06

(BBC) (AMMA)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በመንጋ ላይ መንጋ እየተጨመረ ዘመቻውን አዳጋች አድርጎታል!

በደቡብ ወሎ ዞን በቃሉ ወረዳ 6ኛ ቀኑን ያስቆጠረው የአንበጣ መከላከል ዘመቻ በዛሬው እለትም ተጠናክሮ የቀጠለ ቢሆንም በመንጋ ላይ መንጋ እየተጨመረ ዘመቻውን አዳጋች አድርጎታል። በመሆኑም በባህላዊ መንገድና በኬሚካል ከመከላከሉ ጎን ለጎን የሠብል ማሰባሠቡም ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention

ለኢፌዴሪ መንግስት፣ ለአብክመ ለሚመለከተው ሁሉ፦

ከድር ኡመር (የቃሉ ወረዳ ም/ዋና አስተዳዳሪ)

በዞናችን በተለይም በወረዳችን ቃሉ፣ አርጎባና ወረባቦ ወረዳወችን ጨምሮ እየተፈታተነን ያለውን የአንበጣ መንጋ በሄሊኮኘተር ርጭት እንድታደርጉልንና ህዝባችንን ከጭንቀት ሲቀጥል ችግሩ በመክፋቱ ከተረጂነት እንድንታደገው በላቀ አክብሮት ጠይቀናል። አካባቢያችን ለአውሮፕላንም ሆነ በሰው አቅም ለመከላከል እጅግ አስቸጋሪ መሆኑን በተጨባጭ ተሞክሮ አረጋግጠናል።

ከድር ኡመር(የቃሉ ወረዳ ም/ዋና አስተዳዳሪ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ እሳት...

የ450 የአፍሪቃ ዝሆኖች መኖሪያ፤ ማደሪያ ብሔራዊ ፓርክ የሆነው የቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ እሳት እሳት መከሰቱን ተጠቁሟል፡፡ የቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ ኃላፊ አቶ ዘነበ አረፋይኔ ለጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን እንደገለጹት "አደባይ የምትባል ቦታ- እሳቱን ለማጥፋት ኅበረተሰቡና አመራሮች ተሰባስበን መንገድ ጀምረናል" ብለዋል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia
መከላከያ እና የትግራይ ልዩ ኃይል ገብተዋል!

(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም)

"ቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ እሳትና ሰው ሲታገሉ አድረዋል። የዱር ሕይወት ጀግኖች ዋጋ ከፍለው ስለ ቃፍታ መዳን ተስፋ ሰጥቸውኛል። መከላከያና የትግራይ ልዩ ኃይል ገብተዋል።"

(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተተከሉ ችግኞች በእንክብካቤ እጦት እየደረቁ ነው!

ባለፈው ክረምት (2011 ዓ/ም) የተተከሉ ችግኞች እንክብካቤ እየተደረገላቸው ባለመሆኑ የመድረቅ አዝማሚያ እየተስተዋለባቸው ነው። ''በአረንጓዴ አሻራ'' ዘመቻ ባለፈው ክረምት በአገሪቷ 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውን መንግሥት ሲገልፅ ከርሟል።

በተለይም ሐምሌ 22/2011 በአገር አቀፍ ደረጃ 200 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ግብ ተይዞ በዘመቻው ከታቀደው በላይ 350 ሚሊዮን ችግኞች ተተክለዋል። ምንም እንኳን እስካሁን ለቁጥሩ የገለልተኛ ወገን ማረጋገጫ ባገኝም። በዘመቻው ወቅት እንከባከባለን እያሉ ቃል ሲገቡ የነበሩ ተቋማትና ግለሰቦች ዛሬ ቃላቸውን እንደረሱትም ይነሳል።

ችግኞቹን ለማዳን መንግሥት በቦቴ ውኃ የሚያቀርብበት ሁኔታ ቢመቻች መልካም ነው ሲሉም የሚመክሩ አሉ። ችግኞች የተተከሉባቸው ቦታዎች እንስሳት እየገቡ እያጠፉት እንደሆነና ተገቢው እንክብካቤ እየተደረገ አለመሆኑን የሚገልፁም አልጠፉም። መንግሥት ችግኞቹን በቋሚነት የሚንከባከብ ሰራተኛ ቀጥሮ ማሰራት እንዳለበትም ያምናሉ።

(Ahadu Radio & Television)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተተከሉት ችግኞች እየደረቁ ነው!

አቶ ደርብ ይማም በአዲስ አባባ ዙሪያ ጌሾ ወንዝ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደን ጥበቃ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ። እርሳቸው እንደሚሉት መንግሥት ከፍተኛ ወጪ አውጥቶባቸው የተተከሉት ችግኞች እንክብካቤ ባለማግኘታቸው እየደረቁ ነው።

”በርካታ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት የተከሉትን ችግኝ ተከታትለው ይንከባከባሉ ተብሎ ነበር” ያሉት አቶ ደርብ አሁን ግን ዞር ብሎ እንኳን የሚያይ ጠፍቷል ይላሉ።

በአካባቢው ከፍተኛ የውኃ እጥረት መኖሩን የገለጹት አቶ ደርብ ”እኔ በግሌ ውኃ እያመጣሁ ነው እያጠጣሁ ያለሁት፤ ውኃ እየተወደደ በመሆኑ አቅም የለኝም ከዚህ በኋላ መንግሥት የሚጠበቅበትን ይወጣ” ብለዋል።

ችግኞቹን ለማዳን መንግሥት በቦቴ ውኃ የሚያቀርብበት ሁኔታ ቢመቻች መልካም ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሰጥተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አምባሳደር ሳሚያ ከቀጠር ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጋር ውይይት አድርገዋል!

ክብርት አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ ትላንት ጥቅምት 25/2012 ዓ.ም ከቀጠር ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር ሃሰን አል ደርሃም ጋር ምክክር አድርገዋል። በውይይታቸውም በሁለቱ አገራት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር ሃሳብ ተለዋውጠዋል።

የቀጠር ዩንቨርሲቲ ከአገራችን የሃዋሳ ዩንቨርሲቲ ጋር ተባብሮ ለመስራት የጀመረውን አጋርነት ለማጠናከር መግባባት ላይ ደርሰዋል። ሁለቱ ዩንቨርስቲዎች በግብርና፣ በቴክኖሎጂ እና በተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ መስኮች በጋራ መስራት እንዲችሉ፤ ብሎም የተማሪዎች እና መምህራን ልምድ ልውውጥ እንዲሁም በጋራ የጥናትና ምርምር ስራዎች ትብብር እንዲያደርጉ ተስማምተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በቀጠር ዩንቨርሲቲ በመማር ላይ ስለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች እና በቀጣይም ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች በዩንቨርሲቲው የትምህርት እድል ስለሚያገኙበት ሁኔታ ምክክር አድርገዋል።

(የኢትዮጵያ ኤምባሲ-ዶሃ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia


በቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ የተነሳውን እሳት መቆጣጠር እንደተቻለ ከ #GetachewM ለመስማት ተችሏል። #ETH

"The 🔥 wildfire outbreak of Kafta Sheraro national park is under control." (Getachew Mulual)

Source:- Chief warden of the park.

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቃሉ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች ሰሞኑን የአምበጣ መንጋ በተከሰተባቸውና ለአደጋው ተጋላጭ የሆኑባቸው ቀበሌዎች በመገኘት የምርት አጨዳና የመሰብሰብ ስራ በመስራት አርሶ አደሩን እያገዙ ይገኛሉ። በ22 ወዳጆና አጎራባች ቀበሌዎች ላይ አዝመራ በመሰብሰብ ላይ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention

አፋር እና ሶማሌ ክልሎች ላይ የአንበጣውን የሕይወት ዑደት ማቋረጥ ካልተቻለ ስርጭቱ አሁን ካለበትም እንደሚጭምር የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታውቋል። የአንበጣ መንጋው ከዚህ በፊት ተከስቶ ከነበረባቸው ስድስት ወረዳዎች ስርጭቱን በማስፋት ዘጠኝ ወረዳዎችን ማዳረሱን ነው ቢሮው ያስታወቀው፡፡

(AMMA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia