TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ዶ/ር ጫላ ዋታ ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ። የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት የነበሩት ዶ/ር ጫላ ዋታ የመንግስት ግዥ ህግ ከሚፈቅደው አሰራር ውጭ በሰሩት ስራ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቷል። ምክር ቤቱ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ነው ያለመከሰስ መብታቸው የማንሳት ውሳኔን ያፀደቀው። አንድ ድምፀ ተአቅቦ ያደረጉት እራሳቸው ዶ/ር ጫላ ዋታ ናቸው። (ዝርዝር ይኖረናል) …
#ዝርዝር
የቀድሞ የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት የነበሩት ዶ/ር ጫላ ዋታ ዛሬ ያለመከሰስ መብታቸው ተገፏል።
የምክር ቤቱ የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስለ ዶ/ር ጫላ ዋታ ምን አለ ?
#የመንግስት_ግዥ_ህግ ከሚፈቅደው አሰራር ውጭ በመሄድ የውስጥ ገቢ ማስገኛ በሚል " ቢኤችዩ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነሪንግ ጄነራል ሌቭል 1 ፒኤልሲ " የተባለ አማካሪ ድርጅት በማቋቋም በስማቸው ንግድ ፍቃድ በማውጣት ከቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ጋር የተለያዩ የግንባታ ስራዎችን የማማከር አገልግሎት ለመስጠት በቀጥታ ግዥ በመፈፀም መዋዋሉን ፣ ለአማካሪ ድርጅቱና ለአማካሪ ድርጅቱ ላፀደቃቸው ተቋራጮች ክፍያ በመፈፀም በመንግስት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል በሚል ጥቆማ ደርሶ ዝርዝር ምርመራ ተደርጓል።
በዚህም በተደረገ የወንጀል ማጣራት ፦
- 195 ሚሊዮን 52 ሺህ 812 ብር ከ81 ሳንቲም የሚያወጡ የተገለያዩ የግንባታ ስራዎች ለዘጠኝ ተቋራጮች ከመንግስት የግዥ አዋጆች እና አፈፃፀም መመሪያ ውጭ በቀጥታ እንዲፈፀም አድርገዋል።
- ዩኒቨርሲቲው ለመሰረተ ልማት ግንባታ የተፈቀደለትን የካፒታል በጀት አላግባብ በመጠቀም የግዥ ህግ እና ደንብ ባልተከተለ መልኩ ዋጋቸው 116 ሚሊዮን ብር የሆኑ 14 ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች በግል ተቋራጭ ድርጅት ስም ግዥ ተፈፅሟል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ተሽከርካሪዎቹ እና ማሽነሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው ገንዘብ የተገዙ ቢሆንም በግል ተቋራጮች ድርጅቶች ስም እንዲሆኑ ተደርጋል።
ተሽከርካሪዎቹ እንዲሁም ማሽነሪዎቹ የተገዙበት ዋጋ እጅግ የተጋነነ ሲሆን ለምሳሌ አንድ ደብል ጋቢና ፒካፕ ለተሽከርካሪ ተቋራጭ ድርጅቱ ከአስመጪ በብር 3 ሚሊዮን 300 ሺህ ግዥ የተፈፀመ ቢሆንም ዩኒቨርሲቲው በብር 6 ሚሊዮን 173 ሺህ 396 ብር ከ83 ሳንቲም እንደተገዛ ተቆጥሮ ክፍያ በመፈፀም ብር 2 ሚሊዮን 873 ሺህ 396 ብር እላፊ ተከፍሏል።
አንድ ሌላ ተሽከርካሪ ግዥ የተፈፀመው በብር 6.1 ሚሊዮን ቢሆንም ዩኒቨርሲቲው በብር 6 ሚሊዮን 415 ሺህ 687 ብር ከ05 ሳንቲም በመግዛት ክፍያ የተፈፀመ በመሆኑ 315 ሺህ 687 ብር ከ05 ሳንቲም እላፊ እንዲከፈል ተደርጓል።
አጠቃላይ የ14ቱ ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች ባለቤት የዩኒቨርሲቲው ሳይሆን የስራ ተቋራጭ ድርጅቶቹ እንዲሆኑ በማድረግ የተሰጣቸውን የመንግስት ኃላፊነትን ወደ ጎን በመተው ለራሳቸው የማይገባ ጥቅም በማግኘት እንዲሁም አማካሪ ድርጅት በሌለበት የተቋሙ የግንባታ ፅህፈት ቤት በፀደቁ የክፍያ የምስክር ወረቀት 11 ሚሊዮን 532 ሺህ 83 ብር ከ53 ሳንቲም ለተቋራጮች ክፍያ እንዲፈፀም በማድረግ የመንግሥት ሃብት እና ንብረት እንዲባክን አድርገዋል።
- በዶ/ር ጫላ እና ቢኤችዩ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነሪንግ ጄነራል ሌቭል 1 ፒኤልሲ በተባለው ድርጅት ላይ በተካሄደው የሃብት ምርመራ ስራ በተገኘው ውጤት ድርጅቱን የሚያንቀሳቅሱት ስራ አስኪያጅ እና የቦርድ ዳይሬክተር ዶ/ር ጫላ ዋታ መሆናቸው በዚህም ድርጅቱ ከቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ጋር በገባው ውል መሰረት በድምሩ 23 ሚሊዮን 135 ሺህ 433 ብር ከ27 ሳንቲም ያለአግባብ ከቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ የባንክ ሂሳብ ላይ ተቀንሶ ወደ ድርጅቱ ሂሳብ ቁጥር ገቢ መደረጉና ከዚህ በመቀጠል ከድርጅቱ ቢኤችዩ ኃ/የተ/የግል ማህበር የባንክ ሂሳን ተቀንሶ በ6 የተለያዩ ጊዜያት በድምሩ 2 ሚሊዮን 116 ሺህ 16 ብር ከ65 ሳንቲም ወደ ዶ/ር ጫላ ዋታ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ የሂሳብ አካውንት ገቢ ተደርጓል።
- በዶ/ር ጫላ ዋታ ባለቤት ስም ወ/ሮ ፀሃይ ኃይሉ ተፈራ ስም 72 ካሬ ላይ ያረፈ በብር 10 ሚሊዮን የተገዛ ባለ 3 ወለል ህንፃ የተገኘ መሆኑና ህንፃው የተገዛበት ገንዘብ በተመለከተ የተደረገው የፋይናንስ ምርመራ ክፍያው የተፈፀመው " ቢዳሩ ኮንስትራክሽን " ከተባለ ድርጅት ብር 4 ሚሊዮን እንዲሁም ደግሞ አቶ ተስፋሁን ሌንጄቦ ሌካ ብር 3 ሚሊዮን 500 ሺህ በተጨማሪ በዚህ ተመሳሳይ ቀን ቦኩይ ኢታንሳ የተባሉ ብር 2 ሚሊዮን 500 ሺህ በዶ/ር ጫላ ዋታ ባለቤት ወ/ሮ ፃሃይ ኃይሉ ስም ወደ ተከፈተ የሂሳብ ቁጥር ገቢ ተደርጎ ይኸው ገንዘብ በቀጥታ ለህንፃው ግዥ መዋሉ ታውቋል።
ገንዘቡ ለባለቤታቸው ለወ/ሮ ፀሃይ ኃይሉ ተፈራ ገቢ አድራጊዎች ማንነት ለማጣራት በተደረገው ምርመራ መሰረት በ " ቢዳሩ ኮንስትራክሽን " በቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ገንዘብ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አአ 05069 የሆነ በብር 7 ሚሊዮን 785 ሺህ 157 ከ30 ሳንቲም የተገዛለት መሆኑና ተስፋሁን ሌንጄቦ የተባለው ደግሞ ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ለሚያሰራቸው ግንባታ መሰረተ ልማት እና ኢንፍራስትራክቸር ዝርጋታ ስራ በቀጥታ በደብዳቤ ትዕዛዝ 55 ሚሊዮን 133 ሺህ 893 ብር ስራ የተሠጠው ነው።
- በዶክተር ጫላ ዋታ ስማቸው የተመዘገበ አ/አ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ አንድ ሙሉ ክፍያው የተፈፀመ ኮንዶሚኒየም ቤት በልጃቸው ስም 200 ሺህ ብር በራሳቸው ስም የተገዛ የ1 ሚሊዮን ብር ሼር የተገኘ መሆኑ ተረጋግጧል።
ዶ/ር ጫላ ዋታ ምን አሉ ? ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-04-04

Telegraph
Tikvah Ethiopia
#ዝርዝር የቀድሞ የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት የነበሩት ዶ/ር ጫላ ዋታ ዛሬ ያለመከሰስ መብታቸው ተገፏል። የምክር ቤቱ የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስለ ዶ/ር ጫላ ዋታ ምን አለ ? የመንግስት ግዥ ህግ ከሚፈቅደው አሰራር ውጭ በመሄድ የውስጥ ገቢ ማስገኛ በሚል " ቢኤችዩ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነሪንግ ጄነራል ሌቭል 1 ፒኤልሲ " የተባለ አማካሪ ድርጅት በማቋቋም በስማቸው ንግድ ፍቃድ በማውጣት ከቡሌሆራ…