TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ግንባታ ላይ ያለው አደይ አበባ ስታዲየም አጥር ስር የሚደረግ የመኪና ዝርፊያ!!
Audio
AudioLab
ያዳምጡ⬆️

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


ቦሌ ትምህርት ቤት አከባቢ የሚስተዋለው የመኪና ሥርቆት በቪዲዮ ተቀርፆ በሶሻል ሚዲያ በመሰራጨቱ ዛሬ ላይ ፓሊስ በአከባቢው ተገኝቶ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
AudioLab
ያዳምጡ⬆️

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


ሰሞኑን ተከስቶ ለነበረው ግጭት በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት በበጎፈቃደኝነት የተለያዩ ድጋፎች ሲደረግ ቆይቷል፡፡ ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ይህን ተግባር በዋናነት ሲያስተባብር የነበረውን ያሬድ ሹመቴን በቀጥታ የስልክ መስመር አናግሮታል፡፡ ያዳምጡ!

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
ያዳምጡ⬆️

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


ሴቭ ዘኔሽን አሶሴሽን ባወጣው ዘገባ ኢትዮጵያ ውስጥ በወር 405 በላይ ዜጎች ህይወታቸውን በመኪና አደጋ ያጣሉ ባለፈው ዓመት 4597 ዜጎች በዚሁ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
AudioLab
ያዳምጡ⬆️

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


በችግሩ ልክ ያልተወራለት የአንበጣ መንጋ በሚቀጥለው ዓመት በሚመዘገበው የምርት መጠን ላይ ከፍተኛ ጫና ሊያሳድር ይችላል፡፡

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዋሽንግቶን ዲሲ🛬

በአሜሪካ የገንዘብ ተቋም ኃላፊ ስቴቨን መንቺን ባደረጉት ግብዣ መሰረት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከግብጽና ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በሚደረገው ውይይት ለመሳተፍ ወደ አሜሪካ ያቀናውና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው የልዑካን ቡድን ዛሬ ረፋድ ላይ ዋሽንግተን ገብቷል። የልዑካን ቡድኑ ዋሽንግተን ዱልስ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በአምባሳደር ፍጹም አረጋና በኤምባሲው ዲፕሎማቶች አቀባበል ተደርጎለታል።በዋሽንግተን ዲሲ በሚካሄደው ውይይት ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ያላትን አቋም የምታስረዳ ይሆናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention

የአንበጣ መንጋው ከ4ሺህ ሄክታር በሚበልጥ የደረሰ ሰብል ላይ ጉዳት አደረሰ!

በደቡብ ወሎ ዞን የተከሰተው የአንበጣ መንጋ ከ4 ሺህ ሄክታር በላይ የደረሰ ሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። ሕብረተሰቡ የአንበጣ መንጋውን በባህላዊ መንገድ ከመከላከል ጎን ጎን የደረሱ ሰብሎችን ፈጥኖ በመሰብሰብ ንቁ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑ ተመልክቷል።

የመምሪያው ምክትል ኃላፊ አቶ አሊ ሰይድ እንደገለጹት የአንበጣ መንጋ በየጊዜው ከአፋር ክልል ወደዞኑ የሚገባ በመሆኑ ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ውጤት እንዳያመጣ አድርጎታል፡፡

"የመልክዓ ምድሩ አቀማመጡ አስቸጋሪ በመሆኑ በአውሮፕላን ኬሚካል ለመርጨት አልቻልንም" ያሉት ምክትል ኃላፊው በባህላዊ መንገድ ብቻ የሚደረገው የመከላከል ስራ ከአንበጣው በፍጥነት መዛመት ባህሪ ጋር ተያይዞ ለውጥ አለማምጣቱን ተናግረዋል።

እስካሁንም በቃሉ፣ ወረባቦና አርጎባ ወረዳዎች ባሉ11 ቀበሌዎች ላይ ብቻ የነበረው የአንበጣ መንጋ ሳምንት ባለሞላ ጊዜ ውስጥ ወደ 25 ቀበሌዎች በመስፋፋት ከ4 ሺህ ሄክታር በሚበልጥ መሬት በለማ ሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱን ገልጸዋል፡፡

(ENA)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኤርፖርት ጉምሩክ ህገወጥ የስናይፐር የጦር መሳሪያ አክሰሰሪዎች ተያዙ!

ኤርፖርት ጉምሩክ የግል መገልገያ እቃዎችን ሽፋን በማድረግ በአረቢያን መጅሊስ ውስጥ ተደብቆ የመጡ የስናይፐር የጦር መሣሪያ ቁሳቁስ በፍተሻ መያዙ ተነገረ፡፡

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ የግል መገልገያ እቃዎችን ሽፋን በማድረግ በአረቢያን መጅሊስ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ተደብቆ በግለሰብ ስም የመጡ የተለያዩ የስናይፐር የጦር መሣሪያ አክሰሰሪዎች በኤክስሬይ እና በእቃ ፍተሻ ኦፊሰሮች ሊያዝ የቻለ ሲሆን ተጠርጣሪው ግለሰብም በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ሠላምን ሊያደፈርሱ የሚሠሩ ህገ-ወጥ ተግባራትን ለመከላከል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የበኩሉን መወጣት አለበት።

(የገቢዎች ሚኒስቴር)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Urgent

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔን ለማከናወን ባለፉት ቀናት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ከነዚህ ዝግጅቶች መካከል ስድስት ሺህ በላይ የምርጫ አስፈጻሚዎችን አሰልጥኖ በትላንትናው እለት ስምሪት የጀመረ ሲሆን የመራጮች ምዝገባ ቁሳቁስ ስርጭትም በዛሬው እለት ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

ነገር ግን የተወሰኑ ርቀት ያላቸው የምርጫ ጣቢያዎች ቁሳቁስ አለመድረሱን ቦርዱ ስለተረዳ የመራጮች ምዝገባ መጀመሪያ ቀን በሁሉም ቦታዎች እኩል እንዲጀመር በማሰብ ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም እንዲሆን ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም ማምሻውን ባደረገው ስብሰባ ወስኗል፡፡ በመሆኑም የሚመለከታቸው አካላት እና ህብረተሰቡ የመራጮች ምዝገባ ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚጀመር አውቀው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ያሳውቃል፡፡

(የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ)

#share #ሼር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባ ወደ ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም መራዘሙን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

(የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ)

#ሼር #share

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታዊ ባለሙያዎች 23ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ በኤርትራ ዋና ከተማ በአስመራ- ተከፈተ!
#Asmera

የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታዊ ባለሙያዎች 23ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ በኤርትራ ዋና ከተማ በአስመራ- ተከፈተ። በዚህ ለ3 ቀናት በሚቆየው ስብሰባ ከ250 በላይ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የመጡ ተወካዮችና አጋር የኢኮኖሚ ድርጅቶች፡ በቀጠናው አዲስ ውህደትና ትብብር ለመፍጠር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ።

(የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዓለም አቀፉ የስፖርት ጋዜጠኛ በቲክቫህ ስፖርት!

#TikvahSportFamily #FirewAsrat

ውድ የTIKVAH SPORT ቤተሰቦች ከፊትችን አርብ ጀምሮ የረጅም ጊዜ የቤተሰባችን አባል የሆነው በተለያዩ አለም አቀፍ እንዲሁም አህጉራዊ ዌብ ሳይቶች ላይ SOKA 25 EAST JW SPORT 1 ኬንያ ለጋናው FOOTY GHANA እንዲሁም የሩሲያው RFL በኢትዮጵያ ስፖርት ፀሀፊ ፍሬው አስራት በየሳምንቱ ያልተሰሙ እና ሊሰሙ ይገባቸዋል የሚባሉ ስፖርታዊ ሀተታዎችን ወደ እናንተ ውድ ቤተሰቦቻችን ባማረ አቀራረብ ማድረሱን ይጀምራል ።

ሰዓት፦ ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ

Join👇@tikvahethsport

https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg

@tikvahethiopiaBot👈አስተያየት መቀበያ!
#EthiopianAirlines #CBE

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ባሉበት ቦታ ሆነው ትኬት መቁረጥና ሌሎች የአገልግሎት ክፍያዎችን መፈጸም የሚያስችል የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር መሆኑን ገለጸ፡፡ አዲሱን የአገልግሎት አሰጣጥ መዘርጋቱን አስመልክቶ አየር መንገዱ እና ንግድ ባንክ በጋራ በመሆን በስካላይት ሆቴል መግለጫ ይሰጣሉ፡፡ በመግለጫውም የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስኪያጅ እና የንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት የሚገኙ ይሆናል ተብሏል፡፡ የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ የአየር መንገዱን አገልግሎት ቀልጣፋና ተገልጋዮችንም ከማያስፈልግ እንግልት ይታደጋል ተብሏል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Ethiopia #Tigray

በቃፍታ ሸራሮ ብሔራዊ ፓርክ ከትላንት በስቲያ ጀምሮ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱ ተገለፀ፡፡ እስካሁን ድረስ ቃጠሎው እንዳልቆመ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ቃፍታ ሸራሮ; በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር የሚገኝ ብሔራዊ ፓርክ ነው፡፡

ምንጭ፦ ሚሊዮን ኃይለስላሴ(ጀርመን ድምፅ ራድዮ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SIDAMA #HAWASSA

ህዳር 10 ቀን የሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ሰላማዊ፣ ነፃ፣ ዴሞክራሲያዊና በህዝብ ዘንድ ተዓማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ሀይሉ ሊሰራ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡ በህዝበ ውሳኔ ወቅት የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመፍታት ረገድ የፍትህ አካላትና የህዝብ ታዛቢዎች ሚናን በተመለከተ በሀዋሳ ከተማ ለታዛቢዎችና ለፀጥታ አካላት በትላንትናው እለት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethioia
#HAWASSA የሲዳማ ብሔር በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ምላሽ የሚያገኝበት ህዝበ ውሳኔ ቅስቀሳ ስራ በይፋ መጀመሩ ይታወቃል፡፡ ይህን ተከትሎ "ሲዳማ በአብሮነት የሚኖሩ ሌሎች ህዝቦችን በማቀፍ በክልልነት የመደራጀት ጥያቄውን በህዝበ ውሳኔ ለማረጋገጥ ይሰራል!" በሚል መሪ ቃል የሀይቅ ዳር ክፍለከተማ ቤሌማ የኪነ-ጥበብ ቡድን የቅስቀሳ ስራ አከናውኗል፡፡

PHOTO: የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጉባዔ ፕሬዚዳንት ብጹዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ሱራፌል ለመላው ካቶሊካውያን የጸሎት ቀን አወጁ፡፡ ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም የመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል ሲከበር በዕለቱ ሁሉም የቤተክርስቲያኗ ቁምስናዎችና ጸሎት ቤቶች ስለኢትዮጵያ ሰላም፣ ስለሞቱ፣ ስለተጎዱ፣ ስለተፈናቀሉ ወገኖች በጋራ በመሆን ለመጸለይ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ የጸሎት ቀን አውጀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአፋርና ሶማሌ የህዝብ ለህዝብ መድረክ!

በሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን የሃገር ሽማግሌዎችና አመራሮች ባለፈው ሳምንት የሰላም ሚኒስቴር ባዘጋጀው የአፋርና ሶማሌ የህዝብ ለህዝብ መድረክ ሶማሌዎች ተሳታፊ አልነበርንም ሲሉ ከሰሱ።

የሶማሌ ነዋሪዎች በሚበዙባት አና በአፋር ክልል ስር በምትገኘው አወዛጋቢዋ የአዳይቱ ወይም ገዳማይቱ ከተማ ላይ በተዘጋጀው መድረክ ላይ የፖለቲካ አመራሮችም፣ የኢሳ ጎሳ ኡጋዝም ሆነ የሃገር ሽማግሌዎች ተሳታፊ አልነበሩም፥ በተቃራኒው በዕለቱ በርካታ የኢሳ ሶማሌዎች ከተማዋን ለቅቀው እንዲወጡ መደረጋቸውንና የተወሰኑትም ታስረው እንደነበር አስታውቀዋል። የሰላም ሚኒስቴር ግን መድረኩ በሁለቱ ክልሎች መካከል ሳይሆን አፋር ክልል ውስጥ ባሉ አፋሮችና ኢሳዎች መካከል የተዘጋጀ ነው ብሏል።

ኮንፈረንሱ የተካሄደባት የአዳይቱ ከተማ አፋርና ሶማሌ ክልል በይገባኛል ከሚወዛገቡባቸው ሶስቱ ቀበሌዎች አንዷ ነች።

(የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአየር ንብረት ለውጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከሚያስፈልግበት ደረጃ መድረሱን ተመራማሪዎች አስታወቁ!

ከ11 ሺህ በላይ ዓለማቀፍ ተመራማሪዎች ባወጡት ጥናት እንዳመለከቱት ዓለም ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያስፈልጋታል፡፡

ለ40 ዓመታት የተደረገ ጥናት እንዳመላከተው መንግሥታት ለአየር ንብረት ለውጥ የሰጡት ምላሽ በጣም አነስተኛ ነው፡፡ በዚህ የተነሳም የሰው ልጅ የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው ፍጹም ተፅዕኖ የከፋ አደጋ ውስጥ ወድቋል፡፡
ተመራማሪዎቹ ከፊት ለፊት እየመጣ ያለውን ሥጋት የመግለጽና የማስጠንቀቅ የሞራል ኃላፊነት እንዳለባቸው በመግለጽ ነው መረጃን ይፋ ያደረጉት፡፡

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-06

(BBC) (AMMA)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በመንጋ ላይ መንጋ እየተጨመረ ዘመቻውን አዳጋች አድርጎታል!

በደቡብ ወሎ ዞን በቃሉ ወረዳ 6ኛ ቀኑን ያስቆጠረው የአንበጣ መከላከል ዘመቻ በዛሬው እለትም ተጠናክሮ የቀጠለ ቢሆንም በመንጋ ላይ መንጋ እየተጨመረ ዘመቻውን አዳጋች አድርጎታል። በመሆኑም በባህላዊ መንገድና በኬሚካል ከመከላከሉ ጎን ለጎን የሠብል ማሰባሠቡም ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia