"አሁን ላይ ሀገሪቱ ባለችበት ሁኔታ ምርጫ ማካሄድ እጅግ አደገኛ ነው ብዬ አስባለሁ። ጠ/ሚሩ እንዲሁም አንዳንድ ምርጫውን እናሸንፋለን ብለው የሚያስቡ ፓርቲዎች ምርጫው እንዲካሄድ እንደሚፈልጉ አውቃለሁ። ምርጫውን ማሸነፍ ይቻላል፣ ሀገር ግን ይጎዳል።" አክቲቪስ ጃዋር መሃመድ
በዛሬው ዕለት የAssociated Press አለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ከአክቲቪስት ጃዋር መሃመድ ጋር ቃለመጠይቅ አድርጎ ነበር። በቃለመጠይቁ ጃዋር ካነሳቸው ሃሳቦች መካከል፦
•እስካሁን ሊገባኝ ያልቻለው ለምን በለሊት ጥበቃ ማንሳት እንደተፈለገ ነው። ከፌደራል ፖሊስም ሆነ ከደህንነት ተቋማት ጋር የነበረኝ ግንኙነት ጥሩ የሚባል ነበር።
•የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ትናንት "ጥበቃዎቹ እንዲነሱ የተፈለገው የፀጥታ ችግር ስለሌለ ነው" ብሎ ነበር። እውነታው ግን ከሁለት ሳምንት በፊት እንቅስቃሴያችንን እንድንቀንስ እና በርካታ ህዝብ ከሚሰበሰብበት ቦታ ከመሄድ እንድንታቀብ ተነግሮን ነበር። እንደውም ተጨማሪ ሀይል ለመጨመር ሀሳብ እንዳላቸው ነግረውን ነበር። ስለዚህ ይህ እየተባለ የፀጥታ አካላቱን ለማንሳት መፈለጋቸው ግር የሚል ነበር።
•ለምን ይህ እንደተከሰተ ሊናገር የሚፈልግ የለም። ጣት መጠቋቆም ብቻ ነው ያለው፣ ይህም የሰው ህይወት እንዲጠፋ ምክንያት ሆኗል።
•ከጠ/ሚሩ ጋርም ሆነ ከሌሎች አመራሮች ጋር ቁጭ ብለን ማውራት እንችላለን። እኔ ለዛ ዝግጁ ነኝ።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-24-5
Via ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት (Associated Press)
@tsegabwolde @tikvahethiopia

የ16 ሰው ህይወት አልፏል!
አክቲቪስት ጃዋር መሐመድ በኦሮሚያ ለድጋፍና ተቃውሞ የወጡ ዜጎች እንዲረጋጉ መልዕክት ማስተላለፉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ዛሬ በመኖሪያ ቤቱ ለተሰባሰቡ ደጋፊዎቹ ባስተላለፈው መልዕክት፣ በከተሞች የተዘጉ መንገዶችን ክፈቱ፣ ከከተሞች መሰናክሎችን አንሱ፣ ከተጣላችኋቸው ጋር ታረቁ ሲል ለወጣቶች ጥሪ አድርጓል፡። በሁከቱ እስካሁን 16 ሰዎች ተገድለዋል ብሏል ዘገባው፡፡
Via ሮይተርስ/wazema radio/

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከምርጥ 10 የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ሆነ!
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ ውስጥ ካሉ ምርጥ 10 ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ መሆኑን የዓለም ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ አውጪ ተቋም ጥናት አመልክቷል። ተቋሙ ዓለማችን ላይ ያሉ ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎችን በ13 መስፈርቶች አወዳድሮ ደረጃ ያወጣል።
ከመስፈርቶቹም መካከል ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ ጥናት የማድረግ ብቃት፣ የቀጠና ደረጃን የጠበቀ ጥናት የማድረግ ብቃት፣ የማሳተም ብቃት፣ የመጽሐፍ አቅርቦት፣ ኮንፈረንሶችን የማካሄድ እና የዩኒቨርሲቲው ‘ሳይት’ የመደረግ ብቃት ይገኙበታል።
እያንዳንዱ ተቋም የተመዘነው ጥናት በማድረግ ብቃቱ እና በቀጠናው እና በዓለም ዙሪያ ያሉ የአካዳሚክ ማኅበረሰቦች በሰጡት ነጥብ እንደሆነ ተገልጿል።
በደረጃው መሰረት ከ1ኛ እስከ 5ኛ የተቀመጡት የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች ሲሆኑ የግብፁ ካይሮ ዩኒቨርሲቲ በ6ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጧል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም ከደቡብ አፍሪካ፣ ግብፅ፣ ሞሮኮና ኡጋንዳ ዩኒቨርሲቲዎች ቀጥሎ በ10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና ዩኒቨርሲቲው ላስመዘገበው ውጤት ለዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
Via EBC

በሁለት ቀኑ ግጭት የሟቾች ቁጥር 27 ደርሷል- BBC
በአክቲቪስት #ጀዋር_መሐመድ መኖሪያ ቤት አጋጠመ የተባለውን ክስተት ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ከትናንት ጀምሮ ሲካሄዱ ከቆዩት የተቃውሞ ሰልፎች በተያያዘ የሟቾች ቁጥር 27 ደርሷል። ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ ተደርጎባቸው ሰው ከሞተባቸው አከባቢዎች መካከል አምቦ፣ ድሬ ዳዋ እና ዶዶላ ይገኙበታል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-24-7

#አምቦ
ትናንት በአምቦ ከተማ ከተገደሉት ሶስት ሰዎች በተጨማሪ ዛሬ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። ዛሬ በጥይት ከተገደሉት መካከል የ80 ዓመቱ አዛውንት አቶ ሞሮዳ ሞሳ የሚባሉ ይገኙበታል በማለት ነዋሪዎች ተናግረዋል። አቶ ሞረዳ ልጃቸውን ፍለጋ በወጡበት ከጸጥታ አስከባሪ ኃይል በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን የከተማው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በአምቦ ዛሬ ከተገደሉት ሁለት ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ሰዎቸ በጥይት ተመትተዋል።
የአምቦ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር አቶ ደበበ ፈጠነ፤ "ዛሬ 14 ሰዎች በጥይት ተመተው እኛ ጋር መጥተዋል። ሁለቱ ህይታቸው አልፏል። 9 ሰዎች ደግሞ ተኝተው እየታከሙ ሲሆን የተቀሩት ቀላል ህክምና ተደርጎላቸው ወደየቤታቸው ተመልሰዋል" በማለት ያስረዳሉ። አቶ ደበበ ወደ ሆስፒታላቸው የመጡት ሰዎች በሙሉ ወንዶች መሆናቸውን እና ዕድሜያቸውም ከ17-80 እንደሚገመት ተናግረዋል። በዚህም በአምቦ ትናንት 3፤ ዛሬ 2 በድምሩ የሟቾች ቁጥር 5 ደርሷል።
#BBC

#ምስራቅ_ሃረርጌ
በሁለቱ ቀናት በምስራቅ ሃረርጌ በተካሄዱት #ሰልፎች የሟቾች ቁጥር 6 መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል። በዞኑ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ አየለ ዴሬሳ በምስራቅ ሃረርጌ በሚገኙ ከተሞች ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደው እንደነበረ ተናግረው፤ በሁለት ከተሞች በተፈጠረው ግጭት የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን እና በተቀሩት ከተሞች ግን የተካሄዱት የተቃውሞ ሰልፎች በሰላም መጠናቀቃቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
አቶ አየለ፤ ትናንት 5ቱ ሰዎች የተገደሉት ጉሮ ጉቱ በምትባል ከተማ ወደ ብሄር በተቀየር ግጭት ስለመሆኑ ይናገራሉ። "አንድ ባለሃብት የደህንነት ስጋት ተሰምቶት ሁለት ሰዎችን በጥይት መትቶ ገደለ። ከዚያም በቂም በቀል ግለሰቡ እና ሁለት የቤተሰብ አባላቱ ተገደሉ" ሲሉ ሁኔታውን ያስረዳሉ። የአወዳይ ከተማ ነዋሪ የሆነ ወጣት ከመከላከያ ሠራዊት በተተኮሰ ጥይት ስለመገደሉ የአወዳይ ከተማ ከንቲባ ጃፋር ሙሐመድ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።

#ጅማ
ዛሬም በጅማ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ነበር። በከተማዋ ውጥረት ከመንገሱ ባሻገር በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን አንድ የከተማዋ ነዋሪ ለጀርመን ራድዮ ጣቢያ ተናግረዋል። ወታደሮችም የፌዴራል ፖሊሶችም የኦሮሚያ ፖሊሶችም አድማ በታኞችም አሉ፤ በከተማዋ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል ሲሉ የከተማው ነዋሪ ገልፀዋል።
#DW

#ድሬደዋ
በድሬደዋ ከተማ ትናንት 1 ሰው የተገደለ ሲሆን ዛሬ ደግሞ 4 ሰዎች ተገድለዋል። የድል ጮራ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አብዱራሃማን አቡበከር ዛሬ ሰባት ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታላቸው እንደመጡ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ለህክምና ከመጡት ሰዎች መካከል 4ቱ ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል። ዶ/ር አብዱራሃማን "ሰዎቹ በጥይት እና በሌላ ነገር ነው ጉዳት ደርሶባቸው የመጡት" ሲሉ ተናግረዋል።

#ዶዶላ #ቢሾፍቱ #ሀረር
በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ ትናንት እና ዛሬ በነበሩ ግጭቶች በጠቅላላው 6 ሰዎች መገደላቸውን ታውቋል። ዛሬ በነበረ ግጭት 4 ሰዎች ሞተው ወደ ዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል መምጣታቸውን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ቶላ ቢዮ ተናግረዋል። ትናንት ደግሞ ሁለት ሰዎች ተገድለው ነበር። በአካባቢው ከጠዋት ጀምሮ ሠልፍ እንደነበር የተናገሩት ሜዲካል ዳይሬክተሩ ከሰዓት በኋላ ግን ይህ ሠልፍ መልኩን መቀየሩን ይናገራሉ። ሁኔታው አስፈሪ ስለነበር ለሕይወታቸው የሰጉ ሰዎች በአካባቢው በምትገኘው ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው አንደሚገኙ ተናግረዋል። በሐረር ከተማ በትናንትናው ዕለት 3 ሰዎች መገደላቸውን ቢቢሲ ከነዋሪዎች ሰምቻለሁ ብሎ ዘግቧል። በቢሾፍቱ ከተማ ዛሬም በቀጠለው አለመረጋጋት የሰዎች ህይወት ማለፉን የቢሾፍቱ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ተናገርዋል። ዛሬ ከተማይቱ በተኩስ ስትናጥ እንደዋለች፣ በየቦታው መንገዶች ሲዘጉ እንደነበርና ወታደሮች መንገድ ለማስከፈት ሲንቀሳቀሱ መዋላቸውን ገልፀዋል። አመሻሹን ግን ሁኔታዎች ረገብ ብለዋል።

#DIREDAWA
ድሬዳዋ ሰላም ከራቃት ቆይቷል። ነገር ግን ከትላንትናው ዕለት ጀምሮ ይህን ሁለት ቀን ከተማዋ ባስ ብሎባታል፤ መረጋጋት ተስኗታል፤ ባንክ ቤቶች፣ የንግድ ተቋማት ተዘግተዋል። በበርካታ የከተማይቱ አካባቢዎች የትራንስፖርት እንቅስቃሴም ተቋርጧል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰራተኛ የሆነ የቤተሰባችን አባል በርካታ የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ከተፈጠረው ሁከት ጋር በተያያዘ ስራ እየሰሩ እንዳልሆነ ነግሮናል። የባንኩ ደንበኞች ገንዘብ እንዲያወጣላቸው እየጠየቁት ቢሆንም ከተማው ውስጥ ያለው የሰላም መጥፋት፣ ሁከት እና አለመረጋጋት ያን ለማድረግ እንደማያስችል ገልፆልናል። ሁሉም ሰው የሰላምን ዋጋ መረዳት ይችል ዘንድም ተከታዩን መልዕክት አስተላልፏል፦
"Dear CBE customers, the value of money you withdraw and deposite doesn't depend only on our country's economy, but also on it's peace and stability. so manifest peace or your money is just a paper"

Audio
AudioLab
የተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እንድሪስ መልዕክት ለወጣቶች፦
- የበላዩ የበታቹን ማወያየት አለበት፣ ማዳመጥ፣ መስማት ይገባል፡፡ ጥሩ ሀሳብ ከሆነ መከተል ነው፡፡ የበታቹ ደግሞ የበላዩን ሊያከብር ሊሰማ ይገባል፡፡ እስልምናው ይህንን ያዛል፡፡
- ጥቅም የሚገኘው ከአንድነት ነው፣ ጥቅም የሚገኘው ከሰላም ነው፣ ጥቅም የሚገኘው ከመከበር ነው፣ ጥቅም የሚገኘው ከመተባበር ከመረዳዳት ከመሰማማት ነው፡፡
- የሚጠቅመው መቀራረብ መመካከር መረዳዳት አላግባብ እንደሆነ መመለስ መጸጸት ወደፊት አንድነቱን ማጠንከር ሰላሙን ማጎልበት ማጠንከር ነው፡፡
#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ
@tikvahetiopia @tsegabwolde

#አሰላ
በአሰላ ከተማ ከተፈጠረው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ለሁለት ቀን ተዘግተው የቆዩ መንገዶች መከፈት ጀምረዋል። የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎችም በከተማው ውስጥ ይታያሉ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአሰላ ከተማ ከተፈጠረው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ለሁለት ቀን ተዘግተው የቆዩ መንገዶች መከፈት ጀምረዋል። የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎችም በከተማው ውስጥ ይታያሉ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AMBO
በአምቦ ከተማ ሁኔታዎች ዛሬ ርግብ ያሉ ይመስላሉ። የአምቦ ቲክቫህ ቤተሰቦች እንደገለፁት ከሆነ በከተማይቱ ተዘግተው የነበሩ መንገዶች እየተከፈቱ ነው። የንግድ እንቅስቃሴው ግን ዛሬም ተቀዛቅዟል።

#ETHIOPIA
በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የተዘጉ መንገዶች ከትላንት ጀምሮ እየተከፈቱ ይገኛል። ችግር የነበረባቸው ከተሞች ላይ መንገዶች እንዲፀዱ እየተደረገ ይገኛል። በዛሬው ዕለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሚደርሱ የስጋት እና የግጭት መልዕክቶችም እጅግ በጣም ቀንሰዋል። ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ግን የሀይማኖት ግጭት እንዲነሳ፣ በህዝቦች መካከልም የማያባራ እልቂት እንዲፈጠረ እንቅስቃሴ ሲደረግ እየተመለከትን ነው። የሀይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች አሁንም ሀገራችን እንድትረጋጋ መስራት ይጠበቅባችኃል።
የመንገዶችን ሁኔታ እየተከታተልን እናሳውቃለን!

"1 ተማሪ ለ1 ቤተሰብ" በጎንደር ዩኒቨርሲቲ!
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በወሩ መጨረሻ በይፋ የሚጀምረው የ‹‹1 ተማሪ ለ1 ቤተሰብ ፕሮጀክት›› ለዩኒቨርሲቲው አዲስ ገቢ ተማሪዎች ደስታን ፈጥሯል፡፡
ተማሪዎቹ ለዘመናት የዘለቀውን የሕዝብ ትስስር ያጠነክራል ያሉት ይኸው ፕሮጀክት 5 ሺሕ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እያንዳንዳቸው ከጎንደር ከተማ ነዋሪዎች አንድ ቤተሰብ እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነው፡፡
በዩኒቨርሲቲው ፕሮጀክት የተደመሙት ተማሪዎቹ ይህ ተግባር የዜጎችን የእርስ በርስ ግንኙነት ስለሚያጠናክር በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም እንዲለመድ መክረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በበኩሉ ተማሪዎቹ በእረፍት፣ በበዓል ቀናትና በሌሎችም ጊዜያት ከአዲሱ ቤተሰባቸው ጋር በመገናኘት ምክርና ሐሳብ ከመለዋወጥ ባለፈ በልጅና ቤተሰብ መካከል የሚኖርን ፍቅር እንዲያገኙ ታስቦ መቀረፁን ተናግሯል፡፡
በመደበኛ፣ በማታና በክረምት የትምህርት መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የሚከታተሉ 30 ሺሕ ተማሪዎች ያሉት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለበርካታ ዓመታት የሰላሙ ዩኒቨርሰቲ የሚል አድናቆትን ሲያገኝ ኖሯል፡፡
ምንጭ፦ አሃዱ ሬድዮ

#BISHOFTU
የቢሾፍቱ መንገድ እንደተከፈተ የቢሾፍቱ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል። በየመንገዱ ላይ ያሉት ድንጋዮች ሙሉ በመሉ ስላልተነሱ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉም መክረዋል። የማዘጋጃ ጽዳቶች የትናንት የተቃጠሉ ጎማዎችን ከአስፓልት ላይ እያጸዱ ናቸው። የንግድ ቤቶች፣ ሆቴሎች ግን አሁንም እንደተቀዛቀዙ ናቸው።

#SEBETA | የሰበታ ከተማ የፀጥታ ሁኔታ ወደነበረበት እየተመለሰ ይመስላል። መንገዶች ከትላንት ጀምሮ ተከፍተዋል። የትራንስፖርት እንቅስቃሴም ከትላንት ዛሬ ጨምሯል። የንግድ ተቋማት ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADAMA
አዳማ ከተማ ወደ ሠላማዊ እንቅስቃሴ እየተመለሰች ነው። ምግብ ቤቶች፣ ካፍቴሪያዎች እና የቢዝነስ እንቅስቃሴዎች ከባለፉት ቀናት በተሻለ መልኩ ይታያሉ። ህዝቡ በሠላም ከተማ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ነው:: ሆኖም ግን አሁንም ባንኮች ዝግ ናቸው በዚህ የከተማው ነዋሪ እየተጉላላ ነው።
Via IBRO/አዳማ ቲክቫህ ቤተሰብ/

#MELES_CAMPUS
ኹሓ ከተማ የሚገኘው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ "መለስ ካምፓስ" አንደኛ እመት ተማሪዎቹን መቀበል ጀምሯል። የኹሓ ከተማ ማህበረሰብ አባላትም በተለያዩ ዝግጅቶች ተማሪዎቹን "እንኳን ደህና መጣቹህ" እያሉ ነው።
Via Prof. Kindeya G/Hiwot
PHOTO: Tikvah Family

#AlemGena | ዓለም ገና ከተማ ዛሬ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እየተመለሰች ነው። የፀጥታው ሁኔታ ካለፉት ቀናት የተሻለ ነው። የትራንስፖርት እና የንግድ እንቅስቃሴ ተጀምሯል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መከላከያ ሰራዊት!
የመከላከያ ሰራዊት የፀጥታ መደፍረስ በተከሰተባቸው የኦሮሚያ ክልል ፣ ሀረር እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አካባቢዎች ከአባ ገዳዎች፣ ከሃይማኖት መሪዎች፣ ወጣቶች እና ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የማረጋጋት ስራ እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የክልሉ መንግስት ያቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ ሰራዊቱ የፀጥታ ችግር በተከሰተባቸው በተለይም በአምቦ፣ ቢሾፍቱ፣ ባሌ ሮቢ፣ አዳማ፣ ሞጆ እንዲሁም በድሬዳዋ እና ሀረር መሰማራቱን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫም በእነዚህ አካባቢዎች ከኦሮሚያ ክልል እና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳር የፀጥታ አካላት፣ ከአካባቢው ነዋሪዎች፣ ወጣቶች እና አባገዳዎች ጋር በመሆን ችግሮችን የማስቆም ስራ እየተከናወነ መሆኑን የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ሜጄር ጄኔራል መሀመድ ተሰማ ተናግረዋል፡፡ ይህን ተከትሎም የተዘጉ መንገዶችን የማስከፈት ስራ እየተከናወነ የሚገኘ ሲሆን የንግድ ተቋማትም ወደ ስራ እየተመለሱ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡
https://telegra.ph/ETH-10-25
Via FBC