TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#HARAR የደመራና የመስቀል በዓል በደመቀና በሰላማዊ ሁኔታ እንዲከበር አስፈላጊ ዝግጅት ማድረጉን የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethioia
#HARAR

ከሐረር ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ወደመሀል አገር ሲዘዋወሩ የነበሩ የተለያዩ መድኃኒችን መያዙን የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የኦፕሬሽን ኃይል አመራር የሆኑት ምክትል ኢንስፔክተር ወንደሰን ካሳሁን እንደገለጹት ባለፉት ሳምንታት በህገ ወጥ መንገድ ወደመሀል አገር ሲጓጓዙ የነበሩ መድኃኒቶች የተያዙት በክልሉ ሐማሬሳ የመቆጣጠሪያ ስፍራ ነው። የጸጥታ ኃይሉ ከህብረተሰቡ ጋር በተደራጀ መልኩ ባከናወናቸው ሥራዎች ግምታቸው 100 ሺህ ብር የሚጠጋ የተለያዩ ህገ ወጥ መድኃኒቶች መያዛቸውን አመልክተዋል። በ21 የተለያዩ ካርቶኖች ተቀምጠው ሊተላለፉ ከነበሩ መድኃኒቶች መካከል በመርፌ፣ በደረቅና በፈሳሽ መልክ የሚወሰዱ የተለያዩ መድኃኒቶች እንዲሁም ሲሪንጅ ይገኙበታል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahehiopia
#HARAR #SEMERA

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የመደመር ፍልስፍና መጽሐፍ በአፋር እና ሐረሪ ክልሎች ደረጃ ነገ በሰመራና ሐረር ከተሞች እንደሚመረቅ ተገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HARAR

በሀረር ከተማ በነበረው የ"መደመር" መፅሃፍ ምርቃ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አቶ ንጉሱ ጥላሁን እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ተገኝተው ነበር።

PHOTO: Ablity/TIKVAH FAMILY/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Harar በተመሳሳይ በሀረር ከተማ ጥዋት የነበረው ከፍተኛ ውጥረት ረገብ እያለ የመጣ ይመስላል፤ የቲክቫህ ሀረር ቤተሰቦች ሁኔታዎች ከጥዋቱ አንፃር መሻሻል ማሳየታቸውን ገልፀው ወጣቱ ለሰላም ቅድሚያ እንዲሰጥ ተማፅነዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HARAR

ሀረር ከተማ አሁን ረገብ ብላለች። ጠዋት የከተማው ውሥጥ ከፍተኛ ውጥረት ነበር። ሱቆች ግን ዝግ ናቸው። መንገዶች ግን እንዲከፈቱ እየተደረገ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HARAR

በሐረር ከተማና አካባቢው ሰላምና መረጋጋት በመስፈን ላይ ነው። ረቡዕና ሀሙስ የነበረው ውጥረት ጋብ ብሎ ሕይወት መደበኛ መሥመሯን መያዝ ጀምራለች። በከተማዋ በሁለቱ ቀናት  በነበረው ግጭት በሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። የከተማዋ የታክሲ ትራንስፖርት አገልግሎት ጀምሯል። እንዲሁም ከሐረር – ጅግጅጋ የትራንስፖርት እንቅሰቃሴ መጀመሩንም ተጀምሯል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HARAR

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በሀረር ህዝባዊ ውይይት አደረጉ!


ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከመከላከያ ሚንስትሩ አቶ ለማ መገርሳ ጋር በመሆን ከሀረሪ ክልል፣ ከምስራቅ እና ምእራብ ሀረርጌ ዞኖች እንዲሁም ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ጋር የሰላም ኮንፈረንስ አካሂደዋል፡፡ በጨለንቆ አዳራሽ በተካሄደው ህዝባዊ ውይይት ላይ ከተሳታፊዎች ለጠቅላይ ሚንስትሩ እና መከላከያ ሚንስትሩ ከተሳታፊዎች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የምስራቅ ኢትዮጵያ ህዝቦች እንደከዚህ ቀደሙ አንድነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸውም ነው ከመድረኩ የተገለፀው፡፡ የፍቅር እና የጀግኖች ምሳሌ የሆነው የሀረር ህዝብም ሰላሙን በጋራ መጠበቅ እንዳለበት ጠቅላይ ሚንስትሩ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ፡- ኦቢኤን(OBN)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HARAR

ሐረር ከተማ ከትላንት ጀምሮ ገበያውም፣ ሥራውም፣ ትምህርቱም ተከፍተው ከተማዋ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ ተመልሳለች፤ የከተማይቱ ነዋሪም ወደ መደበኛ ህይወቱ ተመልሷል።

Via BETELHEM NEGASH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HARAR

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዛሬው ዕለት "ሂላል" በሚል ስያሜ የሸርዓ መርህን መሠረት በማድረግ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የሆነ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ቅርንጫፍ በሐረር ከተማ ከፍቷል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንትና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባጫ ጊና በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዛሬ 60 ዓመት በፊት በሐረር ከተማ የመጀመሪያ ቅርንጫፉን ከፍቶ ሥራ መጀመሩን አስታውሰው፣ በዛሬው ዕለት ደግሞ የሸርዓ መርህን መሠረት አድርጎ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የሆነ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ቅርንጫፍ መክፈቱን ገልፀዋል፡፡

(CBE)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#HARAR

በሀረር ከተማ የሚገኙ የንግድ ማዕከል ባለቤቶች ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የንግድ ስራው በመቀዛቀዙ ለተከራዮቻቸውን የወራት ቤት ኪራይ ስረዛ አድርገዋል።

የአውሃኪም የንግድ ማዕከል ባለቤት አቶ አብዱልሃኪም መሀመድ በሀረሪ ክልል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በክልሉ የሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ አረጋዊያንና አቅመ ደካሞችን የክልሉ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርጉ በጠየቃቸው መሰረት 100 ሺ ብር ለግሰዋል።

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የንግድ ስራ መቀዛቀዝ በመታየቱና ችግሩን ለመጋራት በማሰብ በንግድ ማዕከላቸው ውስጥ ያከራያኋቸውን 10 ተከራይ ነጋዴዎችን ሁለት ወራት ከኪራይ ነጻ እንዲሰሩ አድርገዋል።

የኦሬንታል ትሬዲንግ የንግድ ማዕከል ባለቤት አቶ ኑሜር አብዱላዚዝ በንግድ ማዕከሉ ውስጥ ለሚሰሩ ለ26 ግለሰቦች የአንድ ወር የቤት ኪራይ ነጻ ሆነው ስራቸውን እንዲያከናውኑ አድርገዋል። በወር አጠቃላይ የማገኘው 480 ሺህ ብር ነው።

ምንጭ፦ የሀረሪ ክልል ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HARAR

በዛሬዉ እለት በሀረሪ ክልል በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አንድ ሰው መገኘቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ አሳውቀዋል።

ግለሰቡ ወደ 'ህክምና ማእከል' ተወስዶ ህክምና እያገኘ እንደሆነ አቶ ኦርዲን ገልፀዋል። ከግለሰቡ ጋር #ንክኪ የነበራቸዉ ሰዎችም ወደ #ኳራንቲን እንዲገቡ የማድረግ ስራ እየተሰራ እንደሆነ አሳውቀዋል።

አቶ ኦርዲን መንግስት ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አስፈላጊውን ሁሉ የሚያደርግ መሆኑን ያረጋገጡ ሲሆን የክልሉ ህዝብ ከመንግሥት ጎን በመቆም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አሳስበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Iftar የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነስርዓት በተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ነው። አርብ በደሴ ለሁለተኛ ጊዜ ታላቅ የሆነ የጎዳና ላይ ኢፍጧር መካሄዱ ይታወሳል። ትላንት ደግሞ በቡታጅራ ለመጀመሪያ ጊዜ ታላቅ ኢፍጧር ከማርስ ታወር ህንፃ - መናኸሪያ ድረስ ተካሂዷል (ፎቶው ከላይ ተያይዟል) ። ዝግጅቱን ያዘጋጀው ኢኽላስ በጎ አድራጎት ማህበር መሆኑን አዘጋጆቹ ገልፀውልናል። በአሁን ሰዓት ደግሞ በኮምቦልቻ…
#Iftar

#Assosa #Kombolcha #AA #Harar #Metu #Tullubolo

ዛሬ በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ላይ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ስነስርዓት ተካሂዷል።

በተለይም በታሪካዊቷ እና ጥንታዊቷ ሀረር ከተማ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን በተገኘበት ነው የአፍጥር ስነ ስርኣቱ የተካሄደው።

በኮምቦልቻ ከተማ ፥ ዛሬ ሁለተኛው የጎዳና ላይ ኢፍጣር " ኑ አብረን እናፍጥር " በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል። በስነስርዓቱ ላይ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ባለፈ የሌሎች እምነት ተከታዮች የተገኙ ሲሆን ስነስርኣቱ እጅግ በደመቀ ሁኔታ ተጠናቋል።

በመዲናችን አዲስ አበባ ደግሞ በነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት አስተባባሪነት ዛሬ በ11 ጎዳናዎች ላይ የኢፍጣር ስነስርዓት ተካሂዶ በሰላም መጠናቀቁን አዘጋጆች አሳውቀውናል።

በተጨማሪ ዛሬ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ስነስርዓት ከተካሄደባቸው ከተሞች መካከል አሶሳ አንዷ ስትሆን ፤ ስነ ስርዓቱ በበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች አስተባባሪነት ነው የተካሄደው። በመርሃ ግብሩ ላይ ወላጅ አልባ እና አቅመ ደካሞች፣ አረጋዊያን እና ደጋፊ የሌላቸው ወገኖች ከከተማው ሙስሊም ህብረተሰብ ጋር በጋራ አፍጥረዋል።

በአፋር ክልል ዱብቲ ከተማም ታላቅ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ስነስርዓት ተካሂዷል ፤ " አንድነታችንን እያጠናከርን ኑ በጋራ እናፍጥር " በሚል መሪ ሀሳብ ነው የተካሄደው።

በመቱ እና በቱሉቦሎም ዛሬ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ተካሂዷል።

@tikvahethiopia