TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update BBC-ቤንሻንጉል⬇️

በቤንሻንጉል ጉምዝ በተፈጠረ ግጭት ከ50 ሺህ ሰዎች በላይ #ሲፈናቀሉ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ተሰማ።

መስከረም 16/2011 ዓ.ም የካማሼ ዞን አመራሮች ከምዕራብ ኦሮሚያ አስተዳደር ጥምር ኮሚቴ ጋር የነበራቸውን ስብሰባ አጠናቅቀው እየተመለሱ በነበሩ የዞን፣ የወረዳ አመራሮችና የፀጥታ ኃይሎች ላይ በተከፈተው ተኩስ የ4 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በተወሰኑ ከኦሮሚያ ጋር በሚዋሰኑ ስፍራዎች በተከሰተ ግጭት ሰዎች #መሞታቸውን፣ መፈናቀላቸውን ቤቶች መቃጠላቸውን የቤንሻንጉል ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አበራ ባይታ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በተለይ በበሎይ ጅጋንፎይ ወረዳ ስር ሳይ ዳለቻ ቀበሌ ግጭት የነበረ ሲሆን በግጭቱም 75 ቤቶች ተቃጥለዋል ብለዋል። በዚሁ ወረዳ ጅጋንፎይ ቀበሌ በጭበጭ በምትባል አካባቢ ላይ ቤቶች መቃጠላቸውን ጠቅሰው ሌሎች ቀበሌዎችም ላይ ተመሳሳይ ግጭቶች መከሰሰታቸውን ተናግረዋል።

በበሎይ ጅጋንፎ ሶቤይ ከተማ ላይ በርካታ ሰዎች ተፈናቅለዋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ በሶጌ ዙሪያ ባሉ ቀበሌዎች ልቢጋ፣ ሳይ ዳላቻ፣ ታንካራ ቀበሌዎች በርካታ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን አስረድተዋል።

"በተንካራ 105 ቤቶች ተቃጥለዋል 3 ሰዎችም ህይወታቸው አልፏል" ያሉት መስተዳድሩ በበጭበጭ 1 ሰው መሞቱንና አንገርባጃ ቀበሌ 2 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው አስረድተዋል። እንደ ክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ገለፃ ወደ ኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ እና በስጋት ምክንያት ወደ ጫካ የገቡ ሰዎች ያሉ ሲሆን ቁጥራቸው ምን ያህል ነው የሚለውን ግን የተጠናቀረ መረጃ የለኝም በማለት ሳይናገሩ ቀርተዋል።

የተፈናቀሉት ሰዎች ከቤንሻንጉል ብቻ ሳይሆን ክልሉን ከሚያዋስኑት የኦሮሚያ ቀበሌዎችም እንደሆነ የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ሳስጋ ወረዳ ዱራበሎ፣ ካምፕ፣ በሎበሬዳ፣ ስምንተኛ ከሚባሉት ቀበሌዎች በስጋት ምክንያት ወደ ነቀምትና በሎበሬዳ ወደሚገኙ ማዕከሎች #ተፈናቅለው እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ የሆኑት አቶ ታከለ ቶሎሳ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በቤንሻንጉል ክልል የኦሮሚያ አዋሳኝ ቀበሌዎች በተከሰተው ግጭት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 12 ደርሷል። ከዚህ በተጨማሪም 14 ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን እነዚህም በሳስጋ ወረዳ ጤና ጣቢያና በነቀምት ሆስፒታል ህክምና እያገኙ መሆናቸውን ገልፀዋል።

እንደ ኃላፊው ገለፃ ከሆነ ቀያቸውን ጥለው ወደ ኦሮሚያ የተሰደዱ ሰዎች ቁጥር 50 ሺህ ደርሷል። እነዚህ ሰዎች የተፈናቀሉት ከበሎይ ጅጋንፎና ያሶ ሲሆን ከኦሮሚያ አዋሳኝ ወረዳዎች ደግሞ ሀሮ ሊሙ፣ ሶጌና ሳስጋ አካባቢዎች ነው።

አቶ ታከለ ጨምረውም ከእነዚህ አካባቢዎች የሚፈናቀሉ የኦሮሞ እና የአማራ ተወላጆችች ቁጥር በየእለቱ እየጨመረ መሆኑን ገልፀዋል። የተፈናቀሉት ሰዎች ሳስጋ ወረዳ፣ ነቀምት ከተማ፣ ሀሮ ሊሙ ወረዳና ጉቶ ጊዳ ወረዳ ውስጥ ኡኬ ከተማ ተጠልለው እንደሚገኙ ጨምረው አስረድተዋል።

በምሥራቅ ወለጋ የሀሮ ሊሙ ወረዳ ኮሙኑኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ በበኩላቸው አቶ #ዱጋሳ_ጃለታ ከቤንሻንጉል ክልል 7 ቀበሌዎች 20 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን ለቢቢሲ የተናገሩ ሲሆን እስካሁን ባላቸው መረጃ በወረዳው ብቻ 5 ሰዎች ሞተዋል።

2 #ነፍሰጡር እናቶች መንገድ ላይ መውለዳቸውን የተናገሩት አቶ ዱጋሳ ህፃናት፣ እናቶችና አቅመ ደካሞች የመኪና መንገድ ባለመኖሩ የተነሳ ለመሸሽ አዳጋች እንደሆነባቸውም ጨምረው አስረድተዋል።

በቤንሻንጉል ክልል #ግጭት በተከሰተባቸው በበሎይ ጅጋንፎይ ወረዳ #ሦስት አካባቢዎች እንዲሁም በካማሼ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሰፍረው እንደሚገኙ የተናገሩት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በተለያየ ጊዜ ምርት በሚደርስበት አካባቢ በክፍፍል ወቅት በተደጋጋሚ ግጭቶች እንደሚነሱ ነገር ግን እነዚህን ወስዶ #ብሄር ተኮር ግጭት ነው ማለት እንደማይቻል አስረድተዋል።

የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ የሆኑት አቶ ታከለ ቶሎሳ በበኩላቸው እስካሁን ድረስ 40 ሰዎች ከቤንሽንጉል 5 ሰዎች ደግሞ ከኦሮሚያ #በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ለተፈናቀሉ ሰዎች የአካባቢው ማህበረሰብ #እርዳታ እያደረገላቸው መሆኑን ከመንግሥት ደግሞ አስፈላጊው ድጋፍ እየተጠበቀ እንደሆነ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ BBC የአማርኛው አገልግሎት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
*በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ኮርተናል*

*እንዲህ ነው ሰብዓዊነት! እንዲህ ነው ኢትዮጵያዊነት*

(ሼር ይደረግ)

ከቤኒሻንጉል ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የአዲስ አበባ እና አካባቢው ነዋሪዎች አስቸኳይ #እርዳታ እንድናሰባስብ በጠየቅነው መሰረት፤ በዛሬው እለት በርካታ ገር ልብ ያላቸው ወገኖቻችን የተለያዩ እርዳታዎችን በመያዝ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተገኝተዋል። ቸር አምላክ ብድራችሁን ይክፈል።

የእርዳታ ማሰባሰብ ስራው በነገው እለትም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 11:30 ድረስ ይቀጥላል። ነገ የእርስዎ ተራ ነው! እንጠብቅዎታለን!

ለማስታወስ ያህል፦

#የማይበላሹ_ምግቦች
መኮረኒ
ሩዝ
ፉርኖ ዱቄት
ዘይት
ሴሪፋም /ፋፋ/
ብስኩት /ጋቤጣ/

#የንጽህና_ቁሳቁሶች
ሳሙና
ኦሞ
ሳኒታይዘር
የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ /ሞዴስ/

#አልባሳት
ብርድ ልብስ
ነጠላ ጫማ
የተለያዩ አልባሳት (ያገለገሉም ቢሆን)

ለበለጠ መረጃ፦ መሐመድ ካሳን ወይም ያሬድ ሹመቴን በቀጣዩ ስልክ ማግኘት ይችላሉ። 0930 36 52 44 በድጋሚ ለበጎ ምግባር አድራጊዎች በሙሉ ያለንን የከበረ ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን። ቸር አምላክ ይስጥልን!!

#ቅድሚያ_ለሰብዓዊነት

(ደጋግመው ሼር እንዲያደርጉ እንማፀናለን)

ከያሬድ ሹመቴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በዲላ ከተማ ልዩ ቦታው ሞላ ጎልጃ ወረድ ብሎ የድሮው ቱቱፈላ ፔንሲዮን አካባቢ የተሰጣ ልብስ በማስገባት ላይ በነበሩ የቤተሰብ አባላት ላይ በደረሰ የኤሌክትሪክ አደጋ፣ አንድ እናት ከሶስት ልጆቿ ጋር #መሞቷ ተሰምቷል። አምስተኛ የቤተሰብ አባል በደረሰበት ከከፍተኛ ቃጠሎ በዲላ ሆስፒታል የህክምና #እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል።

🔹ከሟቾቹ አንዷ በነገው ዕለት ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ልታቀና የተዘጋጀች ነበረች።

©ማስተዋል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሞያሌ🔝

ከህዳር 2 እስከ 7 በሞያሌ በደረሰው ጥቃት ቤታቸዉ የተቃጠለባቸዉ የከተማዋ ነዋሪዎች #ድጋፍ አጥተው እየተቸገሩ መሆናቸውን ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ ከመንግሥት አካል መጥተው ያናገራቸው አካል አለመኖሩንም ለአሜርካ ድምፅ ገልፀዋል። የኦሮሚያ አደጋ መከላከል ኮሚሽን ለተጎጂዎቹ በሳምንት ውስጥ #እርዳታ ለማድረስ እየሰራ መሆኑን ተናግሯል፡፡

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሶሪያ ስደተኞች‼️

በኢትዮጵያ ያሉ #የሶሪያ_ስደተኞችን ለመደገፍ እየተሰራ ነው። በኢትዮጵያ #በልመና የተሰማሩ የሶሪያ ስደተኞችን ለመደገፍ እርዳታ እየተጠየቀ ነው፡፡ በሶሪያ ቀውስ ተፈናቅለው በኢትዮጵያ የሚገኙ ሶሪያውያን ቁጥር ከ300 በላይ የሚልቅ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 108 የሚሆኑት በኢትዮጵያ ህጋዊ ጥገኝነት ጠይቀው እየኖሩ ነው ተብሏል፡፡ የሶሪያ ስደተኞች በየጎዳና የሚያደርጉትን ልመና ትተው ድጋፍ እንዲደረግላቸው መንግስት እየሰራ መሆኑን ታውቋል፡፡ ስደተኞቹን ለመደገፍም #እርዳታ እየተጠየቀ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታራሚዎች እስር ቤት ቆፍረዉ አመለጡ‼️
.
.
ትናንት የካቲት 20 ቀን 2011 ዓ. ም ዳባት ከተማ በሚገኝ እስር ቤት በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው በእስር ላይ የነበሩ ታራሚዎች የእስር ቤቱን ግድግዳ #በመቆፈር ማምለጣቸውን የሰሜን ጎንደር ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ምክትል ኮማንደር #ደሴ_ሙሉዬ ለቢቢሲ ተናገረዋል።

እንደ ኮማንደሩ ገለጻ እስር ቤቱ ስላረጀ በቀላሉ የሚሰበርና የሚቆፈር በመሆኑ ታራሚዎቹ ሰብረው መውጣት ችለዋል።

ካመለጡት እስረኞች መካከል ሁለቱ #በግድያ የተጠረጠሩና ጉዳያቸው በምርመራ ሂደት ላይ ያነበረ መሆኑን ምክትል ኮማንደሩ ገልጸዋል። ሌሎቹ አስራ አምስት እስረኞች ግን በሌሎች ወንጀሎች የተጠረጠሩ ናቸው።

እስር ቤቱ ውስጥ በአጠቃላይ 25 እስረኞች የነበሩ ቢሆንም ሌሎቹ ስምንት ሰዎች እንዳላመለጡ ያብራሩት ምክትል ኮማንደር ደሴ፤ "ስምንቱ ሰዎች የማምለጥ እድል ቢኖራቸውም ሕግን በማክበር በእስር ቤቱ ቆይተዋል" ብለዋል።

ምክትል ኮማንደር ደሴ "እስረኞቹ ከተለያዩ ቀበሌዎች የመጡ በመሆናቸው በአንድ ላይ የመሆን እድል የለም። #የተባበሩት ከእስር ማምለጥን ግብ አድርገው ነው" ሲሉ አስረድተዋል።

በግድያ ከተጠረጠሩት ውጪ ሌሎቹ አርሶ አደሮች እንደሆኑ ጨምረው ተናግረዋል። ታራሚዎቹ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት ባስመዘገቡት አድራሻ መሰረት ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው በመሄድ እንደሚያዙ ተናግረዋል። በወቅቱ ተረኛ የነበሩ የፖሊስ አባላትም ሃላፊነትን ባለመወጣት እንደሚጠየቁም አክለዋል።

እስረኞቹ እንዲያመልጡ ከውጭ #እርዳታ ስለመደረጉ የተጠየቁት ምክትል ኮማንደር ደሴ፤ "እስር ቤቱ የተቆፈረው ከውስጥ ነው። ምንም አይነት የውጪ እርዳታ አልተጨመረበትም" ብለዋል።

ያላመለጡት ስምንት ታራሚዎች ነገሩን ባሉት መሰረት፤ ያመለጡትን እስረኞች ያስተባበረው በዳባት ከተማ በወንጀል ተጠርጥሮ የታሰረ ወጣት ነው።

በእስረኛው ሃሳብ አመንጪነት ያረጀውን ግድግዳ በመስበርና ትንንሽ የዲንጋይ ካቦችን በመናድ ሊያመልጡ መቻላቸውን ምክትል ኮማንደር ደሴ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update 9 ፐርሰንቱ የኢትዮጵያ ህዝብ እርዳታ ፈላጊ ሆኗል ተባለ። መንግስት ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳመለከተው 8.8 ሚልዮን ኢትዮጵያውያን የሰብአዊ #እርዳታ ይሻሉ ብሏል። ከፍተኛው እርዳታ ፈላጊ በኦሮሚያ ክልል (3.88 ሚልዮን) ሲሆን የሶማሌ ክልል 1.8 ሚልዮን ተረጂዎች አሉበት። በአማራ ክልል ደሞ ወደ 980,000 እርዳታ ፈላጊዎች እንዳሉ ገልጿል። ለዚህም መንግስት የ1.3 ቢልዮን ዶላር ገንዘብ #ያስፈልገኛል ብሎ ለእርዳታ ድርጅቶች እና ለጋሽ ሀገራት ጥሪ አቅርቧል። ከእርዳታ ፈላጊዎች ውስጥ 3.1 ሚልዮኑ ተፈናቃዮች ሲሆኑ ይህም በብሄር ተኮር ግጭት የተሰደዱ ናቸው ተብሏል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት(https://www.facebook.com/Elias-Meseret-517243322140049/)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጌዲኦ

በጌዲኦ ዞን #ገደብ እና #ጎቲቲ ወረዳዎች በርካታ ተፈናቃዮች ያለ ምግብ እና ህክምና #እርዳታ በስቃይ አሉ። በህክምና እጦት 15 ህጻናት #የአይናቸውን_ብርሃን አተዋል። አብዛኞቹ በመጠለያ እና በምግብ እጦት #በመሰቃየት ላይ ናቸዉ። የተራድኦ ድርጅቶች እርዳታ ማቅረብ #አልቻልንም ብለዋል። ወቅቱ የዝናብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ቸግሩን የከፋ አድርጎታል።

Via Bisrat Melese
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥንቃቄ ይደረግ‼️

ከወለጋ #እንደተፈናቀሉ_በማስመሰል #በጅማ_ከተማ ህብረተሰቡን በማጭበርበር እርዳታ ሲያሰባስቡ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሁለት ግለሰቦች በእስራትና በገንዘብ መቀጣታቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

የጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንደገለጸው ግለሰቦቹ ከወለጋ እንደተፈናቀሉና ቤታቸው ንብረታቸው እንደተወሰደ በመናገር በሀሰት ከህብረተሰቡ ለአምስት ቀን #እርዳታ ሲያሰባስቡ ቆይተዋል።

ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ በግለሰቦቹ ላይ ባደረገው ክትትል የካቲት 22/ 2011ዓ.ም. በጅማ ቢሺሼ የገበያ ማዕከል እንደያዛቸው የመምሪያው የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ኢንስፔክተር ገዛኸኝ አውጋቸው ተናግረዋል።

“በወንጀል ድርጊቱ ተሳትፈዋል የተባሉት ሁለቱ ግለሰቦች ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ መሆኑ በተደረገባቸው ምርመራ ተረጋግጧል” ብለዋል።

በሃሰት ካሰባሰቡት ገንዘብ ውስጥ አንደኛው መኪናውን እንድታሰራለት 5 ሺህ 300 ብር ለባለቤቱ መላኩንና ሌላኛው ደግሞ 3 ሺ 23 ብር ለዘመዶቹ መላኩን በሰጡት የእምነት ቃል አረጋግጠዋል።

ከዚህ ገንዘብ በተጨማሪም ፖሊስ በግለሰቦቹ እጅ አራት ሺህ ብር ጥሬ ገንዘብ በኢግዚቢትነት መያዙንም አመልክተዋል።

በወንጀል ተከሰው ጉዳያቸውን ሲከታተል የቆየው የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰሞኑን በዋለው ችሎች እያንዳንዳቸው በአንድ ዓመት ከስምንት ወራት ጽኑ እስራትና በ500 ብር እንዲቀጡ የወሰነባቸው መሆኑን ኢንስፔክተሩ ገልጸዋል።

ግለሰቦች #ክስቸውን_እንዲከላከሉ እደሉ ቢሰጣቸውም #ባለመቻላቸው የቅጣት ውሳኔው ጸንቶባቸዋል፡፡

ምንጭ፦ ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia