TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዛሬ ጥዋት በለገጣፎ በኩል ወደ አዲስ አበባ የሚያስገባው መንገድ ተዘግቶ ነበር፤ ብዙም ሳይቆይ በኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል፣ በትራፊክ ፖሊስ እንዲሁም በህብረተሰቡ እገዛ መንገዱን ማስከፈት የተቻለ ቢሆንም አሁንም በድጋሚ መንገዱ እንደተዘጋ በአካባቢው የሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል።

PHOTO: YAB/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድጋሚ የተዘጋው መንገድ - TIKVAH-ETH⬆️

PHOTO: YAB
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HARARI

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ በነበረው 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችና አዋጆችን በማፅደቅ ተጠናቋል። በዚህ መሰረትም ምክር ቤቱ ለ2012 በጀት ዓመት ለክልሉ ስራ ማስፈጸሚያ የሚውል 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በጀት አፅድቋል። ከዚህ ባለፈም ምክር ቤቱ ወይዘሮ ሚስራ አብደላን የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባኤ እንዲሁም አቶ ሰለሞን ኩቹ ሮባን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ልማት ቢሮ ሃላፊነት አድርጎ ሾሟል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፍቅር ጋርመንት ባለቤት የ15 ሺህ ተማሪዎችን ዩኒፎርም ባለማድረሳቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የደንብ ልብስ ለማሰራት ያወጣውን ጨረታ ካሸነፉት 18 ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የፍቅር ሌዘርና ጋርመንት ኢንዱስትሪ ስራ አስኪያጅና ባለቤት ከጥራት በታች የሆነ ጨርቅ ከውጭ አምጥተዋል በሚል በተፈጠረ አለመግባባት ተከትሎ ከተማ አስተዳደሩ ውሉን በማቋረጥ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል።

Via አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን የሰላም የኖቤል ሽልማት በማስመልከት በነገው ዕለት በመላ ኦሮሚያ የደስታ መግለጫ ሰልፎች የሚደረጉ መሆኑን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ነገ ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ/ም ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ስብሰባ በመስቀል አደባባይ የለም" - የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

በማህበራዊ ሚዲያዎች ነገ ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ ሰልፍ እንደሚደረግ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በሰልፉ ምክንያት የሚዘጉ መንገዶችን መኖራቸውን ገለፀ በሚል የኮሚሽኑን ሎጎና የኃላፊዎችን ስም በመጠቀም የተላለፈው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ነገ ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ/ም ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ስብሰባ በመስቀል አደባባይ የሌለና ምንም የሚዘጋ መንገድ አለመኖሩን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ መደበኛ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

መሰል ሀሰተኛና የተዛቡ መረጃዎች በህብረተሰቡ የእለት ከእለት እንስቃሴ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የሚሳድሩ መሆኑን ኮሚሽኑ በማስታወስ ህብረተሰቡ ከተሳሳተ መረጃ ራሱን መጠበቅ እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

Addis Abeba Police Commission

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews

በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ የሚዘጉ መንገዶች ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ሀሰተኛ ነው። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለከተማው ነዋሪዎች ባሰራጨው መረጃ በነገው ዕለት በመስቀል አደባባይ የሚደረግ ስብሰባ፣ ሰልፍም ሆነ የሚዘጋ መንገድ የለም ብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቢሾፍቱ በልምምድ ላይ የነበረ አንድ የኢትዮጵያ የጦር አውሮፕላን ተከስክሶ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል። አውሮፕላኑ ዛሬ ጠዋት ቢሾፍቱ ከሚገኘው የአየር ሃይል ካምፕ በመነሳት በልምምድ ላይ እያለ በምስራቅ ሸዋ ዞን አደአ ወረዳ ኡኬ ደንካካ በተሰኘ ቦታ መከስከሱን የምስራቅ ሸዋ ዞን ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አበራ ያሚ ለዶቸ ቨለ አረጋግጠዋል። በአደጋው የሁለት አብራሪዎች ህይወት ማለፉንም አቶ…
"አብራሪዎቹ ልምድና ብቃት ያላቸው ነበሩ" ብ/ጄ ይልማ መርዳሳ

የኢፌድሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ አደጋውን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ አደጋው ያጋጠመው የጦር ጀቱ ለልምምድ ከተነሳ በኋላ የግራ ሞተሩ በመጥፋቱ ነው ብለዋል። ብርጋዴር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ እንዳሉት በአደጋው ህይወታቸው ያለፈው ሁለት አብራሪዎች ልምድና ብቃት ያላቸው እንደነበሩ ጠቅሰዋል። በአብራሪዎቹ ህልፈት የኢፌድሪ አየር ሀይል የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ታሪክ ተሰራ! ኤድሉድ ኪፕ ቾጌ 1:59:40 መሮጥ ቻለ!

የአራት ጊዜ የለንደን ማራቶን ሻምፒዮኑ ኤሉድ ኪፕ ቾጌ በማራቶን ታሪክ ሰራ። የማራቶን ዉድድርን ከ ሁለት ሰዓታ በታች የገባ የመጀመሪያው አትሌት ሆኖ ተመዝግቧል። ዉድድሩን 1:59:40 በሆነ ሰዓት በመግባት በራሱ የተያዘውን የማራቶን ሪከርድ ሰብሯል።

Via @tikvahethsport /TIKVAH SPORT/

@tikvahethsport @GoitomH @kidusyoftahe
#ደጀን

በርካታ አዳዲስ የዩኒቨርሲቲ ገቢ ተማሪዎች መንገድ በመዘጋቱ እየተንገላቱ ይገኛሉ። ተማሪዎቹ ከቤተሰብ በተለዩበት የመጀመሪያ ቀን ይህ ስላጋጠማቸው እጅግ በጣም እንዳዘኑ ለTIKVAH-ETH በላኩት መልዕክት ገልፀዋል። መንግሥት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል። በተጨማሪ ለደጀን ከተማ ህዝብ ያላቸው አክብሮት እና ምስጋናም ገልፀዋል። ከትላንት ጀምሮ ህዝቡ በፍቅር እየተንከባከበን ሳይሰስት እያበላን እያጠጣን ነው ያሉት ተማሪዎቹ ለከተማው ነዋሪ ያላቸውን ከፍተኛ አክብሮት ይድረስልን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተጨማሪ እናቶች፣ አባቶች፣ የዕድሜ ባለፀጎች እንዲሁም ሌሎች ዜጎች እንግልት እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ገልፀው መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬ በቦሌ አየር መንገድ ካርጎ ተርሚናል እስካሁን የነበረው የቦይንግ 737 ET 302 የመንገደኞች እና የአውሮፕላኑ ሰራተኞች ቅሪተ-አካል ዛሬ የDNA እና የForensic ማጣሪያውን ጨርሰው ለተጎጂ ቤተሰቦች በመሸኘት ላይ ነው።

Via Signorina solomon/TIKVAH ETH FAMILY/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረ "ዘመን ባስ" ተገልብጦ በደረሰው አደጋ የ4 ሰው ህይወት ማለፉን ተመልክቻለሁ ሲል አንድ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል ገልጾልናል። በሰዓቱ ወደ ሀረር እየተጓዝኩ ነበር ያለን የቤተሰባችን አባል እኔ እያለሁ አራት ሰው መሞቱን አይቻለሁ ብሏል። ተጨማሪ የፎቶ መረጃዎችን አጋርቶናል። Via Cheery/TIKVAH ETH FAMILY/ @tsegabwolde…
በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ቀርሳ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 20 ሰዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ። የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ደሳለኝ ጉታ ለኢዜአ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው በወረዳው ቁፋን ዚቅ ቀበሌ ትላንት ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ነው። ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ ይጓዝ የነበረ ኮድ 3 – 97422 ኢት የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ መንገዱን ስቶ በመገልበጡ አደጋው መድረሱን ተናግረዋል። በአደጋው ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች አስክሬናቸው ለቤተሰቦቻቸው መሰጡትን ተናግረዋል። እንደ ዋና ኢኒስፔክተሩ ገለጻ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም በድሬዳዋ ድልጮራ ሆስፒታል ህክምና እንዲያገኙ ተደርጓል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትራፊክ አደጋ የ17 ሰዎች ህይወት አለፈ!

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ትናንት ከቀኑ 11፡30 አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ17 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ በርካቶችም ቆስለዋል፡፡

የሰቆጣ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ደጀን ወዳጅ ለአብመድ እንደገለጹት ከወልደያ ወደ ሰቆጣ ይጓዝ የነበረ መለስተኛ አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከጭነቱ ልክ በላይ በርካታ ሰዎችን እንደጫነ አደጋው ደርሷል፡፡

በወረዳው ዲብርሳይል (07) ቀበሌ ላይ በተከሰተው አደጋ 17 ሰዎች መሞታቸውን ያስታወቁት ኢንስፔክተር ደጀን ‹‹አራት እናቶች ከነልጆቻቸው፣ አንዲት እናት ከሦስት ልጆቻቸው፤ አባት ከልጆቹ ጋር ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ባልና ሚስትም የነበሩ ሲሆን ባል ከነልጁ ሕይወቱ አልፏል፤ ሚስት ከአንድ ልጇ ጋር ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ይገኛሉ›› ብለዋል፡፡

https://telegra.ph/ETH-10-12-3

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UnityPark|በደማቅ ሁኔታ ተመርቆ የተከፈተው የአንድነት ፓርክ በ2 ሺህ የሃገር መከላከያ እና በ2 ሺህ የፖሊስ ሰራዊት አባላትን በማስጎብኘት ስራውን በይፋ ጀምሯል፡፡

አንድነት ፓርክ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

የአዲስ አበባ ፖሊስ 'ነገ ለሚደረግ ሰልፍ በማስተባበር ላይ ናችሁ' ያላቸውን በርካታ ወጣቶች አሰረ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት/ባልደራስ/ ሰብሳቢ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አስታውቋል። ታሰሩ የተባሉት ወጣቶች ቁጥር ለጊዜው አልታወቀም። ነገር ግን ወጣቶቹ በተለያዩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያዎች እንደታሰሩ ነው የተገለፀው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆናቸውን ተከትሎ ባስተላለፉት የደስታ መልዕክት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኤርትራ ጋር ሰላም እንዲኖር አድርገዋል ብለዋል፡፡ ዶ/ር ቴድሮስ ኢትዮጵያዊ በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል ብለዋል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ከአማራ ክልል የፀጥታ ኃላፊዎች ጋር #አጎራባች አካባቢዎችን በተመለከተ አዳማ ስብሰባ ላይ ነን"- አቶ ለማ ሆርዶፋ

በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን የጸጥታ ኃላፊ አቶ ለማ ሆርዶፋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ የተዘጋበትን ምክንያት ለማጣራት አመራሮችን ወደ ሥፍራው እንደላኩ ገልፀው፤ ዛሬ ጠዋትም በጉዳዩ ላይ ተነጋግረውበት አንድም መኪና መቆም እንደማይችል አቅጣጫ አስቀምጠን መኪና በሰላማዊ መልኩ እያለፈ እንደሆነ መረጃ እንዳላቸው ገልፀዋል።

መንገደኞች አሁንም መንገዱ እንደተዘጋ እንደሚናገሩ ከቢቢሲ ለተነሳላቸው ጥያቄ ኃላፊው፤ "በአሁኑ ሰዓት ራሱ መኪና እያለፈ ነው፤ መንገድ ላይ ምንም ችግር እንደሌለ ተጨባጭ መረጃ አለኝ " ብለዋል። በየትኛውም አቅጣጫ ወደ አዲስ አበባ የሚገባ መኪና በሠላም እየተንቀሳቀሰ እንዳለም አስረግጠዋል። ትናንት ጠዋት ላይ መንገድ መዘጋቱን ያስታወሱት ኃላፊው "ከምስራቅ ጎጃም ዞን የፀጥታ ኃላፊዎች ጋር ተነጋግረን፤ ወዲያውኑ አቅጣጫ አስቀምጠን ችግሩ ተፈቷል" ብለዋል።

ኃላፊው የሚያጣሩ ሁለት አመራሮችን ወደ ጎሃ ፅዮን መላካቸውን ከመግለፅ ባለፈ እስካሁን ምክንያቱ ተጣርቶ፤ በማንና ለምን እንደተዘጋ ግልፅ መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል። መንገዱ ስለመዘጋቱ የፀጥታ ኃይሉ እጅ ሳይኖርበት አይቀርም መባሉን ለተነሳላቸው ኃላፊው "ይህንን ኃላፊነት ወስጄ አጣራለሁ፤ ችግር የለውም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ከአማራ ክልል የፀጥታ ኃላፊዎች ጋር አጎራባች አካባቢዎችን በተመለከተ አዳማ ስብሰባ ላይ እንደሚገኙ የገለፁት ኃላፊው አክለውም፤ በደብረ ብርሃን በኩልም ወደ አዲስ አበባ የሚያስገባው መንገድ ተዘግቷል መባሉንም "ውሸት ነው" በማለት ሰላም መሆኑን እንደሚያውቁ ገልፀዋል።

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደጀን ወረዳ አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ የሆኑት አቶ ካሳ አስፋው በአሁኑ ሰዓት ኦሮሚያ ክልል ያለው መንገድ ስላልተከፈተ ደጀን ከተማ ላይ በርካታ መኪኖችና መንገደኞች በከተማዋ እንዳሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-12-4

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MesobTower የመሶብ ታዎር ሌግዤሪ ሆቴል ግንባታ ፕሮጀክት ለማስጀመር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ። ባለመሶብ ታዎር ሌግዤሪ ሆቴል የግንባታ ፕሮጀክት ሕጋዊ ሰውነት ኖሮት የሚንቀሳቀስበትን እና ወደ ግንባታ ሥራ የሚያስገባውን የመግባቢያ ሰነድ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከሀሳብ አመንጪ ኢንጅነሮች ጋር በዛሬው ዕለት በስካይ ላይት ሆቴል ተፈራርሟል።

መሶብ ታዎር፦

•የጎን ስፋቱ 90 ሜትር
•ከፍታው 290 ሜትር፣
•ከመሬት በታች ባለ6 እና
•ከመሬት በላይ ባለ70 ወለል ሕንፃ ያለው ነው፡፡

ለፕሮጀክቱ ግንባታ የ20 ቢሊየን ብር ካፒታል ኢንቨስትመንት እንደሚያስፈልገው ዛሬ በተካሄደው የፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቱርክ በሶሪያዊ ሰሜናዊ ክፍል በኩርዶች ቁጥጥር ስር ያሉ ስፍራዎች ላይ በፈፀመችው ጥቃት በርካቶች መገደላቸው ተሰማ። ቢያንስ 11 ንፁኀን ዜጎች መሞታቸው የተነገረ ሲሆን እንዲሁም በኩርዶች የሚመራው እና ከቱርክ መገንጠል የሚደግፈው ቡድን ወታደሮችም መሞታቸው ታውቋል። የቱርክ ወታደራዊ ኃይል አንድ ወታደር እንደተገደለበትና ሶስት ደግሞ እንደቆሰሉበት አስታውቋል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ቤታቸውን ጥለው የተሰደዱ ሲሆን የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥቃቱ እንዲቆም እየጠየቀ ይገኛል።

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቡኖ በደሌ ዞን ጮራ ወረዳ ሁለት ክላሽንኮቭ ጠብ መንጃና 1ሺ948 ጥይቶች በህገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር ነበር የተባለ ግለሰብ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ። እነዚህ የጦር መሳሪያዎች የተያዙት  ትላንት ጠዋት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 – 61128 ኦሮ በሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ከጋምቤላ ወደ አዲስ አበባ ሲጓጓዝ  ነው።

በጮራ ወረዳ  ፖሊስ ጽህፈት ቤት የአካባቢ ፀጥታ ማረጋገጥ ስራ ሂደት መሪ ሳጅን ዋቅጋሪ ጋዲሳ እንደገለፁት የጦር መሳሪያዎቹ በወረዳው ቁምባቢ ተብሎ በሚታወቀው የፍተሻ ቦታ የጸጥታ አካላት ባደረጉት ፍተሻ ማግኘት ችለዋል። የተገኘውም በጆንያ ተጠቅልለው በተሽከርካሪው ሞተር ውስጥ ተደብቀው ለማለፍ  ሲሞክሩ ነው። የጦር መሳሪዎቹን በህገ ወጥ መንገድ  ሲያጓጉዝ ነበር የተባለው አሽከርካሪ ተይዞ  ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ ሳጅን ዋጋሪ አስረድተዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia