#Dubai በዱባይ የሚገኘው ሰማይ ጠቀሱ 'ቡርጂ ከሊፋ' ህንፃ የጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድን የኖቤል የሰላም ሽልማት ማሸነፍን አስመልክቶ ከላይ በምታዩት መልኩ ህንፃው ተውቧል! ፎቶውን ያጋራን በአሁን ሰዓት ዱባይ የሚገኝ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Dubai #Ethiopia
የዱባይ ቱሪዝም የምስራቅ አፍሪካ ከተሞች ኤግዚቢሽን በኢትዮጵያ ተካሄደ።
ዱባይ ቱሪዝም የምስራቅ አፍሪካ ከተሞች ኤግዚቢሽን ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል ተካሂዷል።
ኤግዚቢሽኑ በኢትዮጵያ ካሉ የዘርፉ ባለድሻዎች ጋር በቅርበት በመስራት ዱባይ በውድ ዋጋ ብቻ ሳይሆን በተመጣጣኝ ክፍያ መጎብኘት የሚቻልባቸውን መንገዶች ማመላከት ዓላማ አድርጎ መካሄዱ ነው የተገለጸው።
በዚህ ዝግጅት ከዱባይ ቱሪዝም ጋር ወደ አዲስ አበባ ከ25 የማያንሱ ድርጅቶች ተወካዮቻቸውን የላኩ ሲሆን በዛሬው ዕለት ሥራቸውን በማቅረብ በኢትዮጵያ ካሉ የአስጎብኚ ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር ትውውቅ አድርገዋል።
ዛሬ ከተካሄደው የዱባይን የቱሪዝም ገብያ ከማስተዋወቅ ባለፈ በትላንትናው ዕለት በኢትዮጵያ ለሚገኙ ለቁጥራቸው 200 ለሚጠጉ በኢትዮጵያ ለሚገኙ አስጎብኚ ድርጅቶች ሥልጠና ተሰጥቷል።
ከሁለት ቀኑ መርሐግብር በተጨማሪ በዛሬው የመዝጊያ መርሐግብርም በዕለቱ ከተገኙ የቢዝነስ አጋሮች እንዲሁም የአስጎብኚ ድርጅቶች ዕጣ በማውጣት የነጻ ጉዞ ዕድሎች እንደሚመቻችላቸው አዘጋጆቹ ጠቁመዋል።
ይህና መሰል የትውውቅ መድረክ ከዚህ ቀደም ሳይኖር #ኢትዮጵያ ከሰሀራ በታች ከሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ወደ ዱባይ በሚደረግ የንግድና የቱሪዝም ጉዞ ከናይጄሪያ ቀጥላ ሁለተኛ ሀገር ናት።
በቀጣይም በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ሰፊ ሥራዎች ለመስራት ታቅዷል።
ፎቶ : ዛሬ በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል የተካሄደው የትውውቅ መድረክ
@tikvahethiopia