TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ📸የኢሬቻ በዓል በዛሬው ዕለት በሃዋሳ ከተማ እየተከበረ እንደሚገኝ SMN ዘግቧል። #Irrecha #HAWASSA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና!

በተሽከርካሪ አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ!

በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ዛሬ ሌሊት በተከሰተ የተሽከርካሪ አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ኢንስፔክተር መሃመድ አሊ እንደገለጹት ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በደረሰው የትራፊክ አደጋ ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ በ14 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል። ከሟቾቹ መካከል የደብረብርሃን ከተማ ትራፊክ ፖሊስ አባልን ጨምሮ ሦስት የአንድ ሰው ቤተሰቦችና ሁለት ህጻናት እንደሚገኙበት ኢንስፔክተር መሃመድ አስታውቀዋል።

ጉዳት የደረባቸውን ሰዎች ወደ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታና አጣዬ የመጀመ ደረጃ ሆስታል በማጓጓዝ ህክምና እንዲያገኙ እየተደረገ ነው ተብሏል። አደጋው የደረሰው 24 ሰዎችን አሳፍሮ ከአዲስ አባ ወደ ደሴ ሲጓዝ የነበር ኮድ3- ኤ71430 አአ ሀይሩፍ ከተቃራኒ አቅጫ ይጓዝ ከነበረ ኢት- ኮድ 3- 91889 ከሆነ ተሳቢ መኪና ጋር በመጋጨቱ መሆኑ ተመልክቷል።

የተሳቢዉ አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን የሀይሩፉ አሽከርካሪ በህይወት መኖሩ አለመኖሩን ለማረጋገጥ የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል። የአደጋው መንስኤም መንገዱ ጠመዝዛ ከመሆኑ አንጻር ከፍጥነት በላይ በማሽከርከር ሳይሆን እንደማይቀር አስታውቃል። የሌሊት ጉዞ ህገ ወጥ መሆኑን በተደጋጋሚ ቢገለጸም አሽከርካሪዎችም ሆኑ ህብረተሰቡ ከእንደዚህ ዓይነት ህገ ወጥ ድርጊት በመቆጠብ ህይወትንና ንብረትን ለማዳን የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቦሮ-ሽናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የ«ጋሪ-ዎሮ» በዓል ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ነው፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WashingtonDC

በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ የሚገኙ ሁለት ገዳማትን ጨምሮ 40 አብያተ ክርስቲያናት በ40 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድነት ሆነው የመስቀል ደመራን በዓልን ማክበራቸው ተገለጸ፡፡

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በበዓሉ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት አብያተ ክርስቲያናቱ በዓሉን በአንድነትና በድምቀት በማክበራቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

‹‹አብሮነቱ ተጠናክሮ ቀጥሎ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ ወግኖቻችንን አንድነት ይበልጥ በማጎልበት ኢትዮጵያን ታላቅ እናድርግ›› የሚል ጥሪም አምባሳደር ፍጹም አቅርበዋል።

ምንጭ፡- በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመስቀል ደመራ በዓል በዛሬው ዕለት በተለያዩ ከተሞች በደማቅ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓት እየተከበረ ይገኛል። በዛሬው ዕለት የመስቀል ደመራ በዓል ከሚከበርባቸው ከተሞች መካከል ጎንደር፣ ሞጣ፣ እስቴ መካነ ኢየሱስ፣ ገንዳ ውኃ፣ ደባርቅ፣ ደብረ ታቦር፣ ሰቆጣ ይጠቀሳሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዉስጥ ሱሪ (በፓንት) ዉስጥ ተደብቆ ሊወጣ የነበረ 12 ሺህ ዶላር ተያዘ!

አንድ ግለሰብ 12 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በፓንቱ ውስጥ ደብቆ ከሀገር ሊያስወጣ ሲሞክር በቶጎጫሌ ኬላ ፈታሾች እጅ ከፍንጅ ተይዟል፡፡ ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ተጠርጣሪው ይህንኑ ተግባር ለመፈጸም ሲጠቀምባቸው የነበሩ የ3 የተለያዩ ባንክ ደብተሮችም አብረው ተይዘዋል።

ምንጭ፦ የገቢዎች ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HAWASSA የኢሬቻ በዓል በሃዋሳ ከተማ ተከብሮ ውሏል። በበዓሉ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች ተገኝተው ነበር። የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ እንዲሁም የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ አቶ አደም በበዓሉ ላይ ተገኝተው መልዕክት ኣአስተላልፈዋል። የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ በቀናት በኃላ በአዲስ አበባ በሚከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ የሲዳማ ብሄር ተወላጆች ለመገኘት ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የግሸን ደብረ ከርቤ ሙዚየም የምረቃ ሥነ ስርዓት በአሁን ሰዓት እየተከናወነ ነው። በሥነ-ስርዓቱ የደቡብ ወሎ ዞንና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል አቡነ አትናቲዮስን ጨምሮ የዞንና የፌዴራል የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ሙዚዬሙ በግሸን ደብረ ከርቤ የሚገኙ ጥንታዊ ቅርሶችን በዘመናዊ መንገድ ለመሰነድና ለጎብኝዎች ምቹ ለማድረግ እንደሚያግዝ ታስቦ የተገነባ ነው።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BBC

የትናንቱ የመስቀል ደመራ አከባበር ውዝግብ በቢሺፍቱ ከተማ!

ትናንት ከኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ተነስተው፤ ወደ ደመራ ለመሄድ መንገድ ላይ ሳሉ፤ "ያልተፈቀደ ሰንደቅ አላማ ይዛችኋል" በሚል ማለፍ መከልከላቸውን የቢሾፍቱ ኪዳነ ምሕረት አገልጋዮችና ምዕመናን ለቢቢሲ ተናገሩ።

የዓደአ ወረዳ ቤተክህነት ጸሀፊ መጋቤ ጥበብ እውነቱ ጥላሁን፤ ከደመራው ዕለት ቀደም ብለው ከከተማው አስተዳደር ጋር በበዓሉ አከባበር ዙሪያ ለመነጋገር ስብሰባ ቢያደርጉም ባለመግባባት እንደተለያዩ ያስታውሳሉ።

የኢሬቻ እና የመስቀል በዓል በሰላም እንዲያልፍ ከአድባራት ኃላፊዎች፣ ከምንጣፍ አንጣፊ ማኅበራት እና ከሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ጋር በመሆን ውይይት ተካሂዶ እንደነበር የሚያስታውሱት ጸሀፊው፤ "ልሙጥ ባንዲራ መያዝ ትችላላችሁ፣ አትችሉም" የሚለው ውይይት ላይ የሌሎች እምነት ተከታይ ኃላፊዎች መሳተፋቸው እንዳላስደሰታቸው ይናገራሉ።

ከዚህ ስብሰባ በኋላ ግን፤ የከተማው ከንቲባ ጠርተዋቸው ይቅርታ እንደጠየቋቸውና በሰንደቅ አላማ ጉዳይ ተነጋግረው፤ ልሙጥ (ኮከብ የሌለው) ባንዲራ መያዝ በሕግ ስለማይፈቀድ፤ ይዘው መውጣት እንደሌለባቸው መስማማታቸውን ይናገራሉ። የበዓል ማድመቂያ ሪቫኖችን ግን በአደባባይ ላይ አስረው በዓሉ በድምቀት እንዲከበር እንደተስማሙ ያክላሉ።

መላከ ሰላም አባ ሩፋኤል በቢሾፍቱ የደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሲሆኑ፤ የመስቀል በዓልን ለማክበር በቢሾፍቱ የሚገኙ አድባራት በአጠቃላይ ወደ መስቀል አደባባይ እንደሚወጡ አስታውሰው፤ ሁሉም ቤተክርስቲያናት በወጣላቸው መርሃ ግብር መሰረት ወደ መስቀል አደባባይ መምጣታቸውን ይገልፃሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/BBC-09-28
https://www.bbc.com/amharic/49862568
ፎቶ📸በዛሬው ዕለት በውቢቷ ሃዋሳ ከተማ በተከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተው ነበር። #HAWASSA #IRRECHA2019

PHOTO : OROMIA MEDIA NETWORK

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዮዮ_ጊፋታ

የአማራ ክልል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ በዮዮ ጊፋታ (የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል) ለመሳተፍ ወላይታ ገብቷል። ልዑኩ በወላይታ ቆይታው የሁለቱን ሕዝቦች ትስስር የሚያጠናክሩ ተግባራትን እንደሚያከናውን ታውቋል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በመስቀል በዓል ወቅት በየአካባቢው እርድ እንደሚከናወን ይታወቃል፤ በዚህ ወቅት ለምግብነት የማያሆኑ የእንስሳት ሰውነት ክፍሎች በየሜዳው ይጣላሉ ይህ ፍፁም ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ነው። እየቆየ ሲሄድም በሚፈጥረው ከባድ ሽታ ለሰዎች #ህመም ምክንያትም ይሆናል። ህብረተሳቡ ከበዓሉ ጎን ለጎን በእርድ ወቅት ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል። አካባቢውንም ከብክለት ሊጠብቅ ይገባል።" መስፍን አየለ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DIREDAWA

የዓለም የቱሪዝም ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ በድሬዳዋ ከተማ በዛሬው እለት መከበር ጀምሯል። የዓለም የቱሪዝም ሳምንት “ቱሪዝም ለስራ ዕድል ፈጠራና ለተሻለ ህይወት !”በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ40ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ32ኛ ጊዜ ነው በመከበር ላይ የሚገኘው።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ የህወሓት ታግይ አቦይ ስብሃት ነጋ ከአውሎ ሚዲያ ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ነው። ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ሰፋ ያላ ምላሽ ሰጥተዋል።

አቦይ ስብሃት ከተናገሩት መካከል፦

"27 ዓመት ጨለማ ነበረ፣ የጥፋት ዘመን ነበረ፤ ውሸት። በ27 ዓመት ውስጥ በአገሪቱ ውስጥ ለተፈጠሩ ጥፋቶች በሙሉ ተጠያቂው ህወሓት ነው፤ ውሸት። ባለፉት 27 ዓመታት ውስጥ ኢህአዴግ በአገሪቱ ያስመዘገባቸው ድሎች #quantitatively & #qualitatively የታወቁ ናቸው። እኔ አሁን ይሄ ይሄ ብየ አልዘረዝርም፤ የሚታወቅ ስለሆነ። ግን ለምሳሌ ኢህአዴግ አገሪትዋ ሲረከብ (per capital income) ወደ 90 ዶላር አከባቢ ነበረ፤ ወደ 800 ዶላር ማድረስ ተችለዋል። የትምህርት ቤት፣ መንገድ ወዘተ ማስፋፋትም እንደዚሁ። በሰላም፣ በህዝበች መፋቀር የተመዘገበው ድል ወዘተ የሚታወቅ ነው።

የAwlo Media አዘጋጅ ጋዜጠኛ በቃሉ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ሙሉውን ቃለ መጠይቅ እንድታዩት የዩትዩብ ሊንኩን አጋርቷችኃል👇
https://www.youtube.com/watch?v=Ri0rYJ5HPjQ
ሌላኛው ደግሞ በዛሬው ዕለት አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከአቶ ጁነዲን ሳዶ ጋር ያደረገው ቆይታ፦

“ ለ14 ዓመታት ያህል ኦነግ ነው ብሎ አቶ ጌታቸው አሰፋ ይከታተለኝ ነበር፤ እርሱ የኦሮሞ ብሔርን ማየት አይፈልግም፤ ኦሮሞ ከሆንክ አንተ ለእርሱ ኦነግ ነህ ማለት ነው ” አቶ ጁነዲን ሳዶ
.
.
•ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በነበሩበት ጊዜ ምንም የማያወላዳ የህወሃት የበላይነት አለ። ይህ በፖሊሲ ደረጃ ነው።

• በምርጫ 97 የኢህአዴግ ደረት ትንሽ አበጥ ያለበት ሁኔታ ነበርና ለተቃዋሚዎች ትኩረት አልተሰጠም።

• ከሃይማኖት ጋር ተያይዞ የሚነሱብኝ ጉዳዮች የፖለቲካ ሥራ ነው የተሰራባቸው። የፖለቲካ ሥራውን የሰሩት ሰዎች ደግሞ ከፌዴራል መንግሥቱ ውስጥ ከኢህአዴግም ከኦህዴድም ውስጥ ናቸው።

• የደህንነት መስሪያ ቤቱ ነበር የተሳሳቱ መረጃዎችን በሕዝቡ መካከል ሲያሰራጭ የነበረው። በግል ከአቶ ጌታቸው አሰፋ ጋር አንስማማም።

• አሃበሽ የሚባል ባዕድ ሃይማኖት እንዲገባ ያደረገው እሱ ነው ይላሉ።

• መስኪድ አሰራ ስለሚባለው እኔ በሕይወቴ እስከአሁን ያሰራሁት አንድ መስኪድ ብቻ ነው። እናቴ ስታርፍ አርሲ የተወለድኩበት ቦታ ላይ በአርሲ ባህል «በጌጌሳ» ገንዘብ አሰባስቤ ነው የሰራሁት፤ በልመና።

• ለ14 ዓመታት ያህል ኦነግ ነው ብሎ አቶ ጌታቸው አሰፋ ይከታተለኝ ነበር። እርሱ የኦሮሞ ብሔርን ማየት አይፈልግም ኦሮሞ ከሆንክ አንተ ኦነግ ነህ ማለት ነው ለእርሱ።

• ኦነጎች በበኩላቸው መንግሥት ውስጥ በመሆኔ የሚቀሰቅስብን እና የሚያስቸግረን እሱ ነው ብለው እኔን የሚጠሉበት ሁኔታ አለ። ይሁንና አቶ ጌታቸው አሰፋ ኦነግ ነው ብሎ ፋይል ከፍቶብኝ ስልኬን እያስጠለፈ በርካታ ችግር አድርሶብኛል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-28-3

ፎቶ: ፋይል
@tikvahethiopia
በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ህዝብ ተወካይ የነበሩት ወይዘሮ ኑራ እንድሪስ ከዚህ አለን በሞት መለየታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያላትን ማንኛውንም ጥያቄ በውይይት በአጭር ጊዜ ለመፍታት የከተማ አስተዳደሩ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።

ምክትል ከንቲባው ትላንት በሀዋሳ ከተማ በደመቀ ሁኔታ በተከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል ካነሷቸው ነጥቦች መካከል፦

•የመስቀል በዓል የፍቅርና የይቅርታ በዓል እንደሆነ ገልፀዋል።

•በሀገሪቱ የመጣው ለውጥ እንዳይቀለበስና እንዳይደናቀፍ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አማንያን የበኩላቸውን ድጋፍና አስተጽፆ እንዲያበረክቱ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

•ሀዋሳ ከተማ ቀድሞ የምትታወቅበት የፍቅር፣ የሰላምና የመቻቻል ከተማነቷን ዳግም እንዳገኘች አንስተዋል።

•ከተማዋ አሁን ላለችበት ሁኔት የህዝቡና ነዋሪዎች ጥረት እንደሆነ አንስተው በከተማ አስተዳደሩ የተሰሩ ስራዎችም ጉልህ ሚና እንደነበራቸው ገልፀዋል።

•ከተማዋ አሁን ባለችበት እንድትቀጥልም ከነዋሪዎችና ከመላው ህዝብ ጋር የከተማ አስተዳደሩ በትኩረት የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

•ምክትል ከንቲባው አዲሱ ዓመትና የመስቀል በዓል የሰላም፣ የልማት የብልጽግና እንዲሆን ምኞታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

#SRTA
#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvagethipia
#DOHA

የሴቶች 10,000 ሜትር ዉድድር ተጀምሯል። ኢትዮጵያ በለተሰንበት ግደይ ፣ ሰንበሬ ተፈሪ እና ነጻነት ጉደታ በመድረኩ ተወክላላች።

መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን !!!!

@tikvahethsport

Join👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg
#UPDATE በዶሃ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ10,000 ሜትር ፍፃሜ በተካሄደዉ ወድድር ኢትዮጵያ የብር ሜዳልያ በለተሰንበት ግደይ አማካኝነት አግኝተናል። ወድድሩን ትዉልደ ኢትዮጵያዊቷ በአሁኑ ሰዓት ለሆላንድ የምትሮጠዉ ሲፋን ሀሰን ስታሸነፍ ኬንያዊቷ ቲሮፕ ለተሰንበትን በመከተል ሶስተኛ ወጥታለች።

ለተመዘገበዉ ድል እንኳን ደስ አለን!

Join TIKVAH-SPORT👇
https://t.iss.one/tikvahethsport
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ድንገት የገባው በሬ⬆️