TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FakeNewsAlert
/ከጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት/

አቶ አረጋዊ በርሄ "መቐለ ላይ ታሰሩ" ተብሎ በአንዳንድ ሚድያዎች የተዘገበው ዘገባ የሀሰት መሆኑ ታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

አቶ ንጉሱ ጥላሁን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ተሾሙ በሚል የተሰራጨው መረጃ #ሀሰት መሆኑ ተገለጸ፡፡ በዛሬው እለት አቶ ንጉሱ ጥላሁን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሁነው እንደተሾሙ በማህበራዊ የትስስር ገጾች በስፋት የተሰራጨው መረጃ #ስህተት መሆኑን አሐዱ ራድዮ እና ቴሌቪዥን ከአቅርብ ምንጮቼ አረጋግጫለሁ ብሏል። አቶ ንግሱ ጥላሁን የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ባለመሆናቸው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የመሆን እድላቸው ጠባብ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፦ አሀዱ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን
🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

በበርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ የቀድሞው የአማራ ክልል ኮሚንኬሽን ቢሮ ሀላፊ የነበሩት አቶ አሰማኸኝ አስረስ ባህርዳር በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በር ላይ በጥይት ተደብድበው #ተገደሉ እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ እና ህዝብ ለማሸበር ሆን ተብሎ የተደርገ የፈጠራ ወሬ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ #ሰራተኞች የእድገት መሰላልና የደሞዝ ስኬል ማሻሻያ ተደረገ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ላይ የግዳያ ሙከራ ተደርገበት በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

በጅማ ከተማ በዛሬው ዕለት ምንም አይነት የድጋፍ ሰልፍ እንዳልነበረ የቲክቫህ ጅማ ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡ የተለያዩ የቆዩ ፎቶዎችን በመጠቀም በጅማ ከተማ ሰልፍ ተደርጓል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ውሸት ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ "ሁለት ተማሪዎች ሞቱ" ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ውሸት መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። ምንም የሞተ ተማሪ የለም፤ በውሸት መረጃም እንዳትሸበሩ ሲል ዩኒቨርሲቲው መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሁለት ተማሪዎች ህይወት ጠፋ እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል!

(ጅማ ዩኒቨርሲቲ)

ውድ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታተዮቻችን!

ከሰሞኑ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከተፈጠረው ክስተት ጋር ተያይዞ ዩኒቨረሲቲያችን ያለውን አቋም መግለጹንና ቁጣቸውን ሲገልጹ የነበሩ ተማሪዎቻችን ለማረጋጋት ከፍተኛ ስራ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጅ አንዳንድ የማህበራዊ ገጾች በዩኒቨርሲቲያችን ያለውን ዕውነታ ቀና ባለሆነ መንገድ በመዘገብ ውዥንብር እየፈጠሩ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘ ሁለት ተማሪዎች እንደሞቱ ተደርጎ ሲዘገብ አመሽቷል፡፡ ነገር ግን ጉዳዩ ከዕውነት የራቀና አንድም የተማሪ ህይወት ያልጠፋ መሆኑን እየገለጽን ዩኒቨርሲቲያችን በዛሬው ዕለት ከአባገዳዎች፣ ከሐይማኖት አባቶች፣ ነባር መመህራን፣ ተማሪዎች እና የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ተማሪዎቹን የማረጋጋትና ሰላማዊ መማር ማስተማር እንቅስቃሴ እንዲጀመር ሰፊ ጥረት ሲያደረግ የዋለ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

(ጅማ ዩኒቨርሲቲ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

(ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ)

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ ችግር የሞተ ተማሪ እና የተደፈረች ተማሪ አለች ተብሎ በማህበራዊ ድህረ-ገጽ ላይ እየተወራ ያለው ዜና ሀሰት መሆኑን እየገለጽን የሞተም የተደፈረም ተማሪ እንደሌለ እናሳውቃለን።

(ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ)

በዚህ አጋጣሚ የዩኒቨርሲቲው ተማሪ የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰቦች እንደገለፁት በተፈጠረው አለመረጋጋት ሳቢያ በርካታ ተማሪዎች እየተንገላቱ እንደሆነ ገልፀውልናል። ግቢው ብቻ ሳይሆን ውጪውም የተረጋጋ ባለመሆኑ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት እንደገባቸው ተናግረዋል። የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲያደርጉን እየጠየቁ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethioia
#FakeNewsAlert

በወለጋ ዩንቨርስቲ የሞተ ተማሪ የለም!

በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተፈጠረ ችግርም ሆነ የሞተ ተማሪ የለም ሲል ዩኒቨርስቲው ገልጾ ተከታዩን መልዕክት አስተላልፏል፡-

በማህበራዊ ድህረ-ገጾች ላይ በወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ ችግር የሞተ ተማሪ አለ ተብሎ የሚሰራጨው ዜና ከእውነት የራቀና መሰረተ ቢስ ወሬ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው በአጽኖት ለማሳወቅ ይወዳል። በመሆኑም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የምትገኙ ተማሪዎች በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተከሰተ ችግርም ሆነ የሞተ ተማሪ አለመኖሩን እንድታውቁ ብሎም በሀሰት ወሬዎች እንዳትሸበሩ ለማሳወቅ እንወዳለን። የዚህ ዓይነቱን መሰረት የለሽ ወሬዎችን የሚያሰራጩ አካላትም ከዚህ እኩይ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ በአጽኖት ያሳውቃል።

"ሰላም ለትምህርት፤ ትምህርት ለሰላም!"

(ወለጋ ዩኒቨርሲቲ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

ምክትል ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን አልታመሙም!

በአንዳንድ የፌስቡክ ገፆች ምክትል ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን ታመዋል እየተባለ የተለጠፈው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት ገለፀ። ጋዜጠኛው በፌስቡክ ገፁ ይፋ ባደረገው መረጃ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአዴፓ ስብሰባን ለመካፈል ባህርዳር ከተማ እንዳቀኑ አረጋግጫለሁ ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከሀሰተኛ ገፆች ተጠንቀቁ!! 29,000 like ያለው ይህ በEritrean Press ስም መረጃዎችን የሚያሰራጭ ገፅ ሃሰተኛ ነው!! @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

ከቀናት በፊት 29,000 ገደማ Like ያለው በ "Eritrean Press" ስም የተከፈተው የፌስቡክ ገፅ ሀሰተኛ ዜናዎችን እያሰራጨ እንደሚገኝ ገልፀንላችሁ ነበር። ይኸው ገፅ በዛሬው ዕለት "ኢዜማ እና ብልፅግና ፓርቲ" ለመዋሃድ ንግግር ጀምረዋል የሚል ሃሰተኛ ዜና ይዞ ወጥቷል። ትክክለኛው Eritrean Press የፌስቡክ ገፅ ከ250,000 በላይ Like ያለው ነው። ውድ ቤተሰቦቻችን ከሀሰተኛ መረጃዎች እንድትጠነቀቁ እንመክራለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia