ቦንጋ⬆️
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ቦንጋ ከተማ ከነዋሪዎች ጋር በመወያየት ላይ ይገኛሉ። ጠቅላይ ማኒስትሩ ከካፋ ዞን ከተውጣጡ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ነው እየተወያዩ የሚገኙት።
የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው እና የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳም በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅድሚያ ሊቀበሏቸው በከተማዋ ስታዲየም ለተሰበሰበው የከተማዋ ነዋሪዎች ንግግር አድረገዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia

መቐለ⬆️
ዛሬ መስከረም 4/2012 ዓ.ም፣ #ኢዜማ በመቐለ ከተማ ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል።
Via ኢዜማ

ፎቶ📸ለስራ ጉብኝት ካፋ ዞን የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በመወያየት ላይ ናቸው። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ ለማ መገርሳ እና የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው አብረዋቸው ይገኛሉ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቴፒ...
"ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በርካታ #ስራዎችን እየሰሩ እንደሚገኙ እናውቃለን። ሀገራቸውን በቅንነት የሚያገለግሉ መሪ መሆናቸውን እናውቃለን። ለምን የቴፒን ጉዳይ በዚህ ደረጃ ዝም እንዳሉ አልገባንም። ቴፒ ያለው ችግር በዘላቂነት ሊፈታ ይገባል። ይህ ደግሞ ጊዜ የሚሰጠው አይደለም። ስለሆነም ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ እጅግ የምንወዳቸው አቶ ለማ መገርሳ ፊታቸውን ወደቴፒ አዙረው ከተማዋን ከችግር አላቀው እረፍት እንዲሰጡን እንማፀናለን።"

ግብፅ❓
"...አሁን ቢሆን እንድትገነባ አንፈቅድላትም" አብዱል ፋታህ አልሲሲ
የግብጹ ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን የጀመረችው አሁን ቢሆን እንድትገነባ አንፈቅድላትም ነበር አሉ። ፕሬዘዳንቱ ኢትዮጵያ ከ8 ዓመት በፊት የተካሄደውን የግብጽ አቢዮት ተጠቅማበታለች ሲሉ ተናግረዋል።
ፕሬዘዳንቱ ይሄንን ያሉት በትላንትናው እለት በካይሮ በተደረገ ብሔራዊ የወጣቶች መድረክ ላይ ነው። ግብጻዊያን ከ8 ዓመት በፊት የሆስኒ ሙባረክን አገዛዝ ለመገርሰስ ወደ አደባባይ በወጡበት ወቅት ኢትዮጵያ ይሄነን አጋጣሚ በመጠቀም የህዳሴውን ግድብ መጀመሯን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ የጀመረችው አሁን ቢሆን ኖሮ እንከለክላት ነበር ሲሉ ለተሰብሳቢዎቹ መናገራቸውን የአገሪቱ የህትመት ሚዲያ አህራም ኦን ላየን የተሰኘው የእንግሊዘኛ ጋዜጣ አስነብቧል። ግብጽ በአብዮቱ ጊዜ የሰራችው ስህተት ዋጋ እያስከፈላት ነው ያሉት ፕሬዘዳንት አልሲሲ ተመሳሳይ ስህተት ለመስራት የሚፈልጉ ግብጻያን ወጣቶች እንዳሉም ተናግረዋል።
#ETHIO_FM
https://telegra.ph/ETH-09-15

"በጎ ፈቃደኞችን እንፈልጋለን" ትምህርት ሚኒስቴር!
በትምህርት ሚኒስቴር ስር በሚገኘው የእኛ ለእኛ ሀገር አቀፍ የበጎ ፈቃደኝነት ሥራ የመጀመሪያው ምዕራፍ ወደ መጠናቀቁ ደርሷል፡፡ በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው አከባቢዎች ለመድረስ ታስቦ በክረምቱ መርኃ-ግብር በተሰራው ሥራ ለበርካታ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ፣ መጽሐፍት፣ አልባሳት ከበጎ ፈቃደኞች አሰባስቦ አሁን ላይ ወደ ስርጭቱ ሊገባ መሆኑ ታውቋል፡፡ አስተባባሪዎቹ እንደገለጹት መስከረም 5 ሰኞ የተሰበሰቡት እቃዎች በሙሉ ከአዲስ አበባ በበጎ ፈቃደኞች ተጭነው ማምሻውን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ጉዟቸውን ይጀምራሉ፡፡ የጉዞ መስመሮቹም መነሻ ቦታው ከትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ግቢ ውስጥ (አዲስ አበባ) ሆኖ መዳረሻው፡-
1. ጎንደር የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ግቢ
2. አሶሳ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ ግቢ
4. ሀዋሳ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ግቢ
5. ጅጅግጅጋ የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ግቢ
ይህ የመጀመሪያው ምዕራፍ ሲሆን በቀጣይ ደግሞ ችግር ላጋጠማቸው ትምህርት ቤቶች በአፋጣኝ ማከፋፈል እንደሚጀመር ተገልጻል፡፡
የቲክቫህ ቤተሰቦችም እነዚህ ድጋፎች ሲደርሱ በየክልሉ ትምህርት ቢሮ በመገኘት እቃውን ከመኪና ላይ በማውረድና በቦታው በመገኘት የተሰበሰበው ድጋፍ በአግባቡ መድረሱን እንድትመለከቱ ለመልካም ዓላማ ተጋብዘናችኋል፡፡
በአከባቢው ያላችሁና መሳተፍ ለምትፈልጉ፦
1⃣ በሀዋሳና ጎንደር ያላችሁ 👉 +251911485705 ደውላችሁ ተመዝገቡ፡፡
2⃣ ጅግጅጋና አሶሳ ያላችሁ 👉+251944260072 ደውላችሁ ተመዝገቡ፡፡
ለበለጠ መረጃ @emush21 ላይ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ከትምህርት ሚኒስቴር በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች!

#BONGA
ዛሬ መስከረም 4 ቀን 2012 ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከምክትል ጠ/ሚር ደመቀ መኮንንና ከመከላከያ ሚንስትር ለማ መገርሳ ጋር በመሆን በከፋ ዞን ቦንጋ በመገኘት ከህዝብ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሂደዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-15-2

በወላይታ ዞን ከ 6 መቶ ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተለያዩ ፋብሪካዎች ሊገነቡ ነው!
በወላይታ ዞን ከ 6 መቶ ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተለያዩ ፋብሪካዎች እንደሚገነቡ የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ የወላይታ ኢንዱስትሪ አብዮት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በሶዶ ከተማ ተካሂዷል፡፡ በወላይታ ዞን የሚገነቡ የተለያዩ ፋብሪካዎች ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ከዞኑ አስተዳደር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ለሚገነቡ ፋብሪካዎች የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፣ የወላይታ ልማት ማህበርና የዞኑ ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት በመተባበር የአዋጭነት ጥናቱን አካሂደዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/በወላይታ-ዞን-ከ-6-መቶ-ሚሊየን-ብር-በላይ-በሆነ-ወጪ-የተለያዩ-ፋብሪካዎች-እንደሚገነቡ-ነው-09-15
Via Wolaita Zone Administration Public Relation Office

#JIMMA
በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ በመግባት ብጥብጥና ሁከት ሊያስነሱ ነበር የተባሉ ወጣቶች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን፣ የከተማው አስተዳደር አስታውቋል፡፡ ወጣቶቹ የተያዙት በአይሱዙ ቅጥቅጥ አውቶብስ ተጭነው ወደ ከተማው ሊገቡ ሲሉ ማክሰኞ ጳጉሜን 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ኬላ ላይ በፀጥታ ኃይል መሆኑን ለሪፖርተር ጋዜጣ የገለጹት፣ የከተማው የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈራ ሽብሩ ናቸው፡፡
ሕዝብን ከሕዝብ ጋር ለማጋጨት ወጥነው ሲንቀሳቀሱ የከተማው መግቢያ ላይ የተያዙትን ወጣቶች በተመለከተ አስቀድሞ ለፀጥታ ኃይል የደረሰ መረጃ በመኖሩ፣ በቀላሉ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አቶ ተፈራ አስረድተዋል፡፡
‹‹ከተማዋን የጦርነት አውድማ›› ለማድረግ የሚፈልጉ ኃይሎች ለወጣቶቹ ገንዘብ ከፍለው እንዳሰማሯቸው ገልጸዋል፡፡ በቅጥቅጥ አውቶብስ ተጭነው ወደ ከተማዋ ሊገቡ ሲሉ የተያዙት እነዚህ ወጣቶች በቁጥጥር ሥር ሲውሉ በእጃቸው የያዙት ዱላም ሆነ ሌላ መሣሪያ እንዳልነበረ፣ ከእነሱ አንደበት በተወሰደ መረጃ መሠረት ግን ከተማው ውስጥ ከገቡ በኋላ አስፈላጊውን መሣሪያ በተሰጣቸው ገንዘብ ለመግዛት ተስማምተው ጉዞ መጀመራቸውን አስረድተዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-15-3

#update ቱኒዚያ ነፃ የተባለውን ሁለተኛውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እያካሄደች ነው ፤የአሁኑ ምርጫ እኤአ በ2011 በአረብ አብዮት ከስልጣን ከተወገዱት ቢን አሊ በኋላ ለሁለተኛ ግዜ የተካሄደ ነው፡፡ #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BONGA
የክልል እንሁን ጥያቄ ከከፋ ዞን ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ቀረበ!
ዛሬ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ ከከፋ ዞን ነዋሪዎች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ከተነሱላቸው ጥያቄዎች መካከል ክልል እንሁን የሚለው ጥያቄ አንዱና ተደጋጋሚው ነበር።
"በየደረጃው ለሚገኙ የመንግሥት አካላት የክልል የመሆንን ጥያቄ አቅርበናል" ያሉት አንድ ተሳታፊ "ለፍርድ ቤት አገልግሎት ሃዋሳ ለመድረስ 800 ኪ.ሜትሮችን ነው የምንጓዘው። ይህ ብቻም ሳይሆን የዞኑ ባለስልጣናት ለስብሰባ ወደ ሃሳዋሳ ሲያቀኑ ብዙ ወጪ ነው የሚያወጡት" ብለዋል።
"የከፋ ህዝብ ባለፉት ስርዓቶች ብዙ ጉዳቶችን ያስተናገደ ህዝብ ነው። የከፋ ዞን የክልል የመሆን ጥያቄ የህዝብ ጥያቄ ነው" ሲሉ አንድ ሌለኛው ተሳታፊ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በተደጋጋሚ ክልል እንሁን ለሚሉ ጥያቄዎች ሲመልሱ "ክልል ብትሆኑ ጥያቄዎቻችሁ ሁሉ ምላሽ ያገኛሉ ብላችሁ ካሰባችሁ ስህተት ነው" ብለዋል።
"ለምሳሌ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች ክልል ሆነው ሳለ እናንተ የምታነሱትን ጥያቄ እነሱም ያነሳሉ" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ "በአሁኑ ሰዓት የከፋን ህዝብ እየስተዳደረ ያለው ሌላ አይደለም። እራሳችሁን በራሳችሁ እያስተዳደራችሁ ትገኛላችሁ" ብለዋል።
ይሁን እንጂ የክልል እንሁን ጥያቄው ሰላማዊ በሆነ መንገድ እና ከክልሉ መንግሥት ጋር ተመክሮ ወደ ፌደራል የሚመጣ ጉዳይ ከሆነ ምንም አሳሳቢ የሚሆን አይደለም ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ። የከፋ ህዝብ ያመነበት ጥያቄ ከሆነ ማንም ሊያስቆመው የሚችለው ጥያቄ አለመሆኑን ጠቅለይ ሚንስትሩ ተናግረዋል።
#BBC
ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-15-4

#update በምሁራን ተጠንቶ የቀረበው የትግራይ ክልል የቱሪዝም ልማት ሰነድ በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገለጸ። ሰነዱ በክልሉ በተመረጡ አራት የቱሪዝም መስህብ ስፍራዎች በሙከራ ደረጃ እስከመጪው ህዳር ወር ድረስ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት ተደርጓል። በመቐለ ከተማ ትናንት በሰነዱ አፈጻጸም ዙሪያ የውይይት መድረክ ተካሄዷል። #ኢዜአ
ፎቶ📸ፋይል/ፕሮፌሰር ክንደያ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸ፋይል/ፕሮፌሰር ክንደያ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ መስከረም 24 ቀን በአዲስ አበባ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓልን አስመልክተው ከአባገዳዎች፣ ቄሮዎችና ከፎሌ ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል። አሁን ላይ በዓሉን አስመልክቶ እየተደረጉ ባሉ ቅድመ ዝግጅቶች ዙሪያ ተወያይተዋል።
የከተማ አስተዳደሩም የኢሬቻ በዓል ከምንጊዜውም በላይ በደማቅ ሁኔታ እንዲከበር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ተናግረዋል። አባገዳዎቹ በበኩላቸው በዓሉ ደማቅ እና ስኬታማ ሆኖ እንዲከበር ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ማቅረባቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። የኢሬቻ በዓል የፊታችን መስከረም 24 ቀን በአዲስ አበባ በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ይሆናል።
Via #FBC

“በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ታሪክ እንደ 2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ብዙ ልጆቻችንን ያጣንበት ዓመት ታይቶ አይታወቅም፡፡” የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
በተያዘው የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲዎች ሰላማዊ መማር ማስተማርን እውን ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በተያዘው የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲዎች ሰላማዊ መማር ማስተማርን እውን ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን ደስ አላችሁ!
#TIKVAH_ETH በሁለት ዓመት ከአንድ ወር ከሃያ አንድ ቀን ከመላው ሀገሪቱ እንዲሁም ከተለያዩ የውጭ ሀገራት ከ400,000 በላይ የቤተሰብ አባላት ማፍራት ችሏል።
_______________________________________
ሰው በሰውነቱ ብቻ የሚከበርባት ሀገር እንድትኖረን እንመኛለን፤ መመኘት ብቻ አይደለም ለዚህ እውን መሆን ያለእረፍት እንሰራለን፡፡
TIKVAH-ETHIOPIA❤️ተስፋ ኢትዮጵያ
አንዱ የአንዱን ባህል፣ ቋንቋና ሃይማኖት ማክበር ከቻለ፤ ከጥላቻ እና ከቂም በቀል ነጻ የሆነ አስተሳሰብ መፍጠር ከተቻለ፤ ልዩነቶችን በውይይት መፍታት ከተቻለ፤ ለመልካም ነገር ለመተባበር ደግሞ ልዩነታችን መሰናክል ካልሆነ #ተስፋ_አለን የኛ ኢትዮጲያ ለሁላችንም የምትመች ሀገር ትሆናለች፡፡ TIKVAH-ETH ውስጥ የተሰባሰብነው እርስ በእርሳችን በመከባበር እና በመዋደድ የተሻለች ሀገር ገንብተን ለመጭው ትውልድ ለማስረከብ ነው።
ሁላችሁንም እናከብራችኃለን!
ረጅም ርቀት አብረን እንጓዛለን!
ሰላም፤ ፍቅር፤ ተስፋ!
TIKVAH-ETH
እንኳን ደስ አለን፤ እንኳን ደስ አላችሁ!

ለወጣቱ አቀንቃኝ እርዳታ ተጠየቀ!
ተወዳጁ ሙዚቀኛ ሙሌ ሐመልማሎ በተለይም ከኤፍሬም አማረ ጋር "ተሸንፊያለሁ" በሚለው ስራው በስፋት የሚታወቀው አርቲስት ሙሉአለም በደረሰበት የኩላሊት ህመም ዲያለሲስ እንዲያደርግ በሀኪሞች ተነግሮታል። እንደሚታወቀው ይህ ሂደት ከፍተኛ ገንዘብን የሚጠይቅ ሲሆን በአርቲስቱ አቅም ደግሞ እስከ መጨረሻው መግፋት የማይቻል በመሆኑ ሁሉም ሰው ድጋፉን ያሳየው ዘንድ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን...
ይህ ወጣት አርቲስት ብዙ የሚጠበቅበት ገና ሙዚቃን ጀመርኳት እያለ እሩቅ በሚያስብበት በዚህ ሰዓት እንዲህ ባለው አደጋ ተደናቅፎ እንዳይቀር ሁላችንም በመረባረብ የበኩላችንን ማድረግ ይኖርብናል። አርቲስት የህዝብ ሀብት ነው። ህይወቱን እና ጊዜውን ለህዝብ ሰቶ የሚሰራ ጥበበኛ መጠለያው መሸሸጊያው ይኼው ያገለገለው ህዝብ ነውና ሁላችን ወደ ህዝብ እንጮሃለን..? ድጋፋችሁን ሽተን ደጃቹን የምንረግጥ ድርጅቶችም ትተባበሩን ዘንድ በዙሁ አጋጣሚ ለመጠየቅ እንገደዳለን።
ከፀሎት ጀምሮ ሁላችንም በምንችለው አቅም ከአርቲስቱ ጎን በመሆን እንርዳው (ጓደኞቹ) Mulualem Takele 1000182044184 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ምንጭ፦ Access Addis

አመስግኑልን!
በድሬ በጎ ፈቃደኛ የጤና ባለሙያዎች "ሳይማር ያስተማረንን ወገናችን እናክም" በሚል መሪ ቃል በሁለት ዙር ተዘጋጅቶ የነበረው ወገንን የመርዳት መርሀ ግብር በዛሬው እለት ተጠናቋል። በመጀመሪያው ዙር #34 እንዲሁም በሁለተኛው ዙር #38 የጤና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል። በዚህም የጎሮ፣ የገንደ ቆሬ፣ የለገሀሬ፣ የአዲስ ከተማ፣ የገንደ ገራዳ ጤና ጣቢያዎች እንዲሁም የሳቢያን ሆስፒታል ህክምናው ከተሰጡባቸው ጤና ተቋማት መካከል ናቸው።
https://telegra.ph/DIRE-09-15
Via ዶክተር ሚኪ ሻውል

#CAIRO
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የኢትዮጵያ፣ የግብጽ እና የሱዳን የሶስትዮሽ የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ በግብጽ ካይሮ ዛሬ መስከረም 4 ቀን 2012 ዓ.ም በመካሄድ ላይ ነው።
ስብሰባው በዋናነት የሶስቱ ሀገራት የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባለፈው ዓመት መስከረም እና የካቲት 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ካደረጉት እና የግድቡን የውሃ አሞላል እና አለቃቅ በተመለከተ ከተደረገው ውይይት የቀጠለ ነው።
https://telegra.ph/ETH-09-15-5

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢዜማ አመራሮች በመቐለ ነዋሪዎች ምን ተጠየቁ?
የ2012 ምርጫ በተያዘለት ቀነገደብ እንዲካሄድ ለምርጫው የሚያስፈልጉ ዝግጅቶች መጠናቀቅ እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ/ኢዜማ/ አስታወቀ። ፓርቲው ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን በትግራይ ህዝብ ላይ ያወጀውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል አውግዞታል።
____________________________________________
•ስለሚመጣው ምርጫ ምንድነው አቋማችሁ?
•ስለምርጫ መራዘም የናተ ግልፅ የሆነ አቋም ምንድነው?
•ኢሳት ከዚህ በፊት ስላወጀው የዘር ማጥፋት ዘመቻ የኢዜማ አቋም ምንድነው?
በተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የተሰጠውን ምላሽ ከላይ ባለው ቪድዮ መከታተል ትችላላችሁ!
Via DW አማርኛ