TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#US : በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አሜሪካ በCOVAX በኩል ለኢትዮጵያ ያበረከተችው 1,555,590 ዶዝ የPfizer የCOVID-19 ክትባት ኢትዮጵያ መድረሱን አሳውቋል::

እኤአ ከሃምሌ 2021 ጀምሮ አሜሪካ ለኢትዮጵያ የሚሰጠችው የኮቪድ-19 ክትባት መጠን ወደ አራት ሚሊዮን ገደማ መድረሱን ኤምባሲው ጠቁሟል ፤ ይህም COVID-19 ለመከላከል በአንድ ሀገር አማካኝነት ለኢትዮጵያ የተበረከተ ከፍትኛው ክትባት መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopia
#US : በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራውያን በሚኖሩባት የቨርጂኒያ ምርጫ የሪፐብሊካን ዕጩ ግሌን ዮንከን አሸነፉ።

ግሌን ዮንከን ምርጫውን ማሸነፋቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል።

ቀድም ብሎ በዚህ ግዛት ላይ ዲሞክራቶች ከተሸነፉ የጆ ባይደን ቅቡልነት ማጣት አንድ ማሳያ እንደሆነ ተንታኞች ሲናገሩ ነበር።

ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ጆ ባይደን ቨርጂኒያን በ10 ነጥብ የበላይነት አሸንፈው ነበር።

ከቨርጂኒያ ሌላ በኒው ጀርሲም በዲሞክቶችና በሪፐብሊካን መካከል ጥብቅ ፉክክር እየተደረገ ነው።

ጆ ባይደን ወደ ዋይት ሐውስ ከገቡ ወዲህ ፦
- የዋጋ ግሽበት መባባስ፣
- የተቀዛቀዘው የምጣኔ ሀብት ቶሎ አለማንሰራራት - ዝርክርክ የተባለው የአሜሪካ ከአፍጋኒስታን የወጣችበት መንገድ በሕዝብ ዘንድ ለዲሞክራቶች የነበረው ተስፋና እምነትን ሸርሽሯል እየተባለ መሆኑን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

መረጃው ከኤኤፍፒ እና ቢቢሲ የተውጣጣ ነው።

@tikvahethiopia
#US #Eritrea

አሜሪካ በኤርትራ ያሉ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ አሳሰበች።

አሜሪካ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና መንግስታቸው የህሊና እስረኞችን እንዲፈቱ አሳስባለች።

አስመራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፥ " ፕሬዜዳንት ኢሳያስ እና መንግስታቸው በግእዝ የገና በዓል መንፈስ እና በክርስትናውም ሆነ በእስልምናው እምነት ውስጥ ይቅርታ ያለውን ትልቅ ሚና በመገንዘብ የኤርትራ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ አሜሪካ ታሳስባለች ። " ብሏል።

በአስመራ የሚገኘው አሜሪካ ኤምባሲ ስላሰራጨው መልዕክት በኤርትራ መንግስት ሆነ ባለስጣናት በኩል የተሰጠ ምላሽ/አስተያየት የለም።

@tikvahethiopia
#US_Embassy_AA

የሙሉ ጊዜ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር የሆናችሁ እና አሜሪካ ውስጥ የልውውጥ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ ይህ እድል ለእናተ ነው።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የ2022-23 የፉልብራይት የማስተማር ልቀት እና ስኬት (TEA) ፕሮግራም ማመልከቻ መቀበል እንደተጀመረ ዛሬ ገልጿል።

ስኬታማ የሆኑ አመልካቾች #ለ6_ሳምንታት የአካዳሚክ ሴሚናሮች እና የክፍል ውስጥ ምልከታ ለማድረግ ወደ አሜሪካ ይጓዛሉ።

በአሜሪካ ቆይታቸው ከአስተናጋጅ ዩኒቨርሲቲ እና ከአካባቢው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከሚገኙ መምህራን እና ተማሪዎች ጋር ወደ የልምድ ልውውጥ ያደርጋሉ።

ፉልብራይት (TEA) በስቴት ዲፓርትመንት የትምህርት እና የባህል ጉዳዮች ቢሮ (ECA) የሚደገፍ ፕሮግራም ሲሆን በአሜሪካ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ በ #IREX የሚተዳደር ነው።

ለበለጠ መረጃ ፦ https://ow.ly/t4FO50HQPPe
ለማመልከት ፦ https://ow.ly/aIaK50HQPPc

የመጨረሻው ማመልከቻ ቀን እ.ኤ.አ የካቲት 27/ 2022 ወይም የካቲት 15 ቀን 2014 ዓ/ም ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት.pdf
#US

አሜሪካ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ተዋጊዎች በአማራ ክልል በነሀሴ ወር መጨረሻ እና በመስከረም መጀመሪያ 2021 የጾታዊ ጥቃትን ጨምሮ አሰቃቂ ድርጊቶች መፈፀማቸውን የሚገልፁ ሪፖርቶች በጣም እንዳሳሰባት ገልጻለች።

ሀገሪቱ ይህን ያለችው በቅርቡ የወጣውን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርትን ተከትሎት ትላንት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትቴር መስሪያ ቤቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ ነው።

ሁሉም የታጠቁ ተዋናዮች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱትን የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ጥቃት እንዲያቆሙ አሜሪካ ጥሪ አቅርባለች።

ለችግሩ ዘላቂ እልባት መስጠት እንዲቻል ለተፈጸመው ግፍ ተዓማኒነት ያለው ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት ሊኖር ይገባል የሚለው ጽኑ አቋሟ መሆኑንም ሀገሪቱ ገልፃለች።

አሜሪካ የጭካኔ ድርጊቶችን የሚገልጹት ሪፖርቶች ቀጣይነት ያለውን ወታደራዊ ግጭት በእስቸኳይ ማስቆም አስፈላጊ መሆኑን አጉልቶ ያሳያል ብላለች።

ግጭቶች እና የጭካኔ ድርጊቶች እንዲቆሙ፣ ሰብዓዊ እርዳታዎች በተሟላ ሁኔታ እንዲዳረስ እና ሰላማዊ የመፍትሔ መንግዶችን ለማፈላለግ ከግጭቱ ተዋናዮች ጋር ተቀራርባ መስራቷን እንደምትቀጥል አሳውቃለች።

@tikvahethiopia
#US #CHINA

ቻይና በአሜሪካ ውስጥ ያሉ ዜጎቿ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበች።

በአሜሪካ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ በሀገሪቱ ያለው የደህንነት ሁኔታ ለቻይናውያን ዜጎች አሳሳቢ ነው ብሏል።

በመሆኑም አሜሪካ የሚገኙ ቻይናውያን ዜጎች ለግል ደህንነታቸው ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ኤምባሲው አሳስቧል።

በአሜሪካ የሚገኙ የቻይና ዜጎች እና የእሲያ ፊት ያላቸው ሰዎች ላይ የሚንፀባረወቅ ጥላቻ እየጨመረ መሆኑን ኤምባሲው ገልጿል።

በቻይና ዜጎች እና የእሲያ ፊት ያላቸው ሰዎች ላይ ሆን ተብሎ የሚፈፀሙ " ተንኮል አዘል " ጥቃቶች የቻይና ዜጎች ላይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑንም ኤምባሲው አስታውቋል።

የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑ መካከልም በቻይና የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገላቸው በአለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎችን እና ሰራተኞችን እንደሚገኙበትም ጠቅሷል።

በቻይናውያን ዜጎች ላይ የሚፈፀሙ መሰል ጥቃቶች በአሜሪካ እየተበራከቱ መሆኑን ያስታወቀው ኤምባሲው፤ በአሜሪካ የሚገኙ የቻይና ዜጎች በሀገሪቱ ውስጥ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ለግል ደህንነታቸው ጥንቃቄ እንዲያድርጉ አሳስቧል።

መረጃውን ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ አል ዓይን ኒውስ ነው ያስነብበው።

@tikvahethiopia
#US #Uk

አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም በዩክሬን ሰማይ ላይ የበረራ ክልከላ መጣልን እንደማይደግፉት በድጋሚ ገልፀዋል።

ሀገራቱ ከሩሲያ ጋር በቀጥታ ወታደራዊ ግጭት እንዲፈጠር አንፈልግም ብለዋል።

ይህን አቋማቸውን ዳግም ያንፀባረቁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው በዋሽንግቶን ዲሲ ተገናኝተው ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የባይደን አስተዳደር ዓላማው ግጭቱ እንዲቆም እንጂ እንዲሰፋ አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል።

ብሊንከን የአሜሪካ ፓይለቶችን ወደዩክሬን አየር ክልል ማስገባት በአሜሪካ/NATO እና ሩስያ መካከል ቀጥተኛ ግጭት ይፈጥራል ብለዋል። "ይህ ደግሞ ግጭቱን ያሰፋዋል፣ ያራዝመዋል፤ አሁን ካለውም በላይ ገዳይ ያደርገዋል። ይህ ደግሞ የሀገሮቻችንም ሆነ የዩክሬን ፍላጎት አይደለም " ሲሉ አስረድተዋል።

የዩኬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤልዛቤት ትሩስ በዩክሬን ሰማይ የበረራ ክልከላ ተግባራዊ እንዲሆን የሚደረገውን ግፊት ውድቅ አድርገዋል። ሚኒስትሯ ውድቅ ያደረጉት የሰብዓዊ መተላለፊያን ለመጠበቅ የተወሰነም ቢሆን ክልከላ ማድረግን ጭምር ነው።

የበረራ ክልከላ ማድረግ በሩስያና NATO መካከል ቀጥተኛ ግጭት እንዲፈጠር ያደርጋል ያሉት ትሩስ፤ "እኛ እየተመለከትን ያለነው ያንን አይደለም፤ እየተመለከትን ያለነው ዩክሬናውያን በተቻለ መጠን በፀረ-ታንክ የጦር መሣሪያዎች እና በአየር መከላከያ ዘዴዎች ሀገራቸውን መከላከል መቻላቸውን ማረጋገጥ ነው" ብለዋል።

ይኸው የአሜሪካና ዩኬ አቋም የተንፀባረቀው የዩክሬኑ ፕሬዜዳንት ቮድሚር ዜሌንስኪ ምዕራባውያኑ የዩክሬን የአየር ክልል ላይ የበረራ ክልከላ እንዲጥሉ እየተማፀኑ ባሉበት ወቅት ነው።

ሩስያ ምዕራባውያን እንዲህ ያለውን ነገር እንዳያስቡት ማስጠንቀቋ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ፤ ኢትዮጵያን ከሌሎች አገራት ጋር የሚኖራትን የጸጥታ፣ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ግንኙነት በሌሎች ኃይሎች በጎ ፈቃድ እንዲንጠለጠልና ራሷን የማትከላከል ሽባ አገር ያደርጋታል ያሉትን ረቂቅ ህጎች [ HR.6600 እና S.3199 ] እንዳይፀድቁ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ዘመቻ እንዲያደርጉ ይፋዊ ጥሪ አቀረቡ።…
#US #ETHIOPIA

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ ፤ በ'US House of Rep.' እየታየ ካለው HR 6600 ረቂቅ ሕግ በተጨማሪ በ'US Senate S 3199' የተባለ ረቂቅ ሕግ ቀርቦ እ.ኤ.አ ማርች 23 በሴኔቱ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ለማየት ቀጠሮ መያዙን ገልፀዋል።

አምባሳደሩ ረቂቅ ሕጎቹ:-
- የኢትዮጵያን ሉዐላዊነት የሚገፉ፣
- በኮቪድ እና በኑሮ ውድነት የተጎዳውን ኢኮኖሚ በውጭ ንግድና ኢንቨስትመንት እንዳያገግም የሚያደርጉ፣
- በጦርነት ቤተሰቡን፣ ቤት ንብረቱን ያጣው ወገናችን ፈጥኖ እንዳይቋቋም የሚያደርጉ እና
- የወደሙ የትምህርት፣ የጤናና ሌሎች የመሰረተ-ልማቶች ፈጥነው እንዳይሰሩ የውጭ ብድርና እርዳታ የሚያስከለክሉ ናቸው ሲሉ አብራርተዋል።

በዚህም በአሜሪካ የሚገኙ ወገኖች ከየአካባቢያቸው ለተመረጡ ለሴኔት እና ለኮንግረስ አባላት ፦
👉ስልክ በመደወል፣
👉ደብዳቤ በመጻፍ፣
👉በኢሜል፣
👉በፒቲሽን በመፈረም፣
👉በአካልም እየተገኘ በማነጋገር እና በሌሎች አግባቦች እንዲቃወሙት በማድረግ ኢትዮጵያውያንን ታደጉ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
#US

አሜሪካ በአስከፊው ጓንታናሞ ቤይ እስር ቤት አስራው የነበረችውን አልጄሪያዊ ወደ ሀገሩ መለሰች።

አሜሪካ በሀገሯ ውስጥ የ "ቦምብ ጥቃት ለማድረስ አቅደሃል" ብላ ለ20 ዓመታት ገደማ ያሰረችውን ሱፊያን ቡርሃሚ የተባለ አልጄሪያው ወደ ሀገሩ እንዲመለስ አድርጌዋለሁ ብላለች።

በአስከፊው ጓንታናሞ ቤይ እስር ቤት አሜሪካ አስራ ያቆየችው እና አሁን መልሸዋለሁ ያለችው አልጄሪያዊ በፈረንጆቹ 2002 ፓኪስታን ውስጥ ከአንድ ነባር የአል-ቃዒዳ አባል ጋር ነበር በቁጥጥር ሥር የዋለው።

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ግለሰቡን ከዚህ በላይ ማሠር ጠቀሜታ ስለሌለው ለቅቄዋለሁ ብሏል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አልጄሪያ ሱፊያንን ስብዕና በተመላበት መንገድ እንከባከበዋለሁ ስትል ቃል ገብታለችም ብሏል።

አልጄሪያ እስካሁን ስለሱፊያን ቡርሃሚ ጉዳይ ይፋዊ አስተያየት አልሰጠችም።

በአሁን ሰዓት ጓንታናሞ ቤይ በተሰኘው በጭካኔያዊ አገዛዙ በሚታወቀው እሥር ቤት 37 ያለፍርድ የታሠሩ ሰዎች አሉ።

ጓንታናሞ ቤይ ከ2002 ጀምሮ አሜሪካ ሽብር ላይ በማደርገው ጦርነት በቁጥጥር ሥር የማውላቸውን ግለሰቦችን የማቆይበት ነው ስትል ያቋቋመች ነው።

በተለይም ከ9/11 የሽብር ጥቃት በኋላ በርካታ ተጠርጣሪዎች ተይዘው የታሰሩበት ሲሆን የአሜሪካ ደህንነት ሰዎች ተጠርጣሪዎችን ኢ-ሰብዓዊ በሆነ መንገድ አሰቃይተዋል ተብለው ይወቀሳሉ ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።

ባለፈው ወርም አሜሪካ በ9/11 ጥቃት ከአውሮፕላን ጠላፊዎች ጋር ለመቀላቀል ሞክሯል ያላቸውን ግለሰብ ከ20 ዓመት በኃላ ወደ ሀገሩ ሳዑዲ አረቢያ እንዲመለስ አድርጋለች። ይህ ሰው መሀመድ አህመድ አልቃህታኒ የሚባል ሲሆን እድሜው 46 ነው፤ ለ20 ዓመት በጓንታናሞ ከቆየ በኋላ ለአእምሮ ጤና ህክምና ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ተደርጓል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #ETHIOPIA በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ከኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። ከአሜሪካ ኤምባሲ በኩል ይፋ በሆነ መረጃ ውይይቱ ፥ በአሜሪካ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ እንዲሁም በሀገራቱ መካከል ስላለው ወሳኝ ኢኮኖሚያዊ እና የንግድ ግንኙነት ላይ ትኩረት ያደረገ…
#US

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚ ትሬሲ አን ጃኮብሰን ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነርና ምክትል ዋና ኮሚሽነር ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው ይታወሳል።

በኃላም ከገንዘብ ሚኒስትር ጋር በኢትዮጵያ እና አሜሪካ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መክረው ነበር።

ትላንት ከኢትዮጵያ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ጋር በገለልተኛ የዳኝነት ስርዓት እንዲሁም የሰብአዊ መብት አያያዝ አስፈላጊነት ላይ ተወያይተዋል።

በዛሬው ዕለት ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ጋር ተገናኝተዋል።

ሰላም እና እርቅ እንዲፈጠር እንዲሁም ለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እርዳታ እንዲደርስ ያላቸውን ተስፋ መጋራታቸውን ከአሜሪካ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት ባገኘነው መረጃ ደግሞ ፥ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የአሜሪካን ተጠባባቂ አምባሳደር ጃኮብሰንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን ይገልፃል።

አምባሳደር ኣን ጃኮብሰን ፤ ከቅዱስነታቸው ቡራኬ ለመቀበል እና ይፋዊ የሥራ ትውውቅ ለማድረግ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የተገኙ መሆናቸውን መረጃው ይገልፃል።

ቅዱስነታቸው ከአምባሳደሯ ጋር በነበራቸው ቆይታ የእንኳን ደህና መጡ መልዕክት በማስተላለፍ በኢትዮጵያ የሚቆዩበት ጊዜ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን የሚችሉበት ይሆን ዘንድ አባታዊ ተምኔታቸውን ገልጸው በቡራኬ ሸኝተዋቸዋል።

@tikvahethiopia