TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Telebirr #CBE

ኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በአጋርነት በ " ቴሌብር " ተጨማሪ የፋይናንስ አገልግሎት መሰጠት ጀመሩ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል ብድር እና ቁጠባ አገልግሎቶችን በቴሌብር አማካኝነት ለማቅረብ የሚያስችል አገልግሎት በይፋ አስጀምረዋል፡፡

አገልግሎቱ ፥ የግለሰብ ደንበኞች እና ተቋማት በቴሌብር የሚያከናውኗቸውን ግብይቶች መሰረት አድርጎ በሚሰራ የብድር ቀመር ስሌት (Credit Score) ብድር የሚያገኙበት ነው።

ከዚህም በተጨማሪ በ " ቴሌብር " ደሞዝ ተከፋይ መሆናቸውን መነሻ በማድረግ ያለ ማስያዥያ (nonCollateral) በአነስተኛ የአገልግሎት ክፍያ ብድሮችን ማግኘት ይችላሉ ተብሏል፡፡

በ2 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከ34.05 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ማፍራት የቻለው ቴሌብር ከዚህ ቀደም ከዳሽን ባንክ ጋር በዘረጋው አሰራር 3.9 ቢሊዮን ብር ማበደሩ ተገልጿል።

ዛሬ ይፋ የተደረጉት አገልግሎቶች ፦

#ስንቅ ፡- ደንበኞች ከወለድ ነጻ ወይም የተለያየ የወለድ ምጣኔ የሚታሰብባቸው የተንቀሳቃሽ እና የጊዜ ገደብ ተቀማጭ የቁጠባ አገልግሎት፣

#እንደራስ ፡- የግለሰብ ደንበኞች በቴሌብር እንደሚያከናውኑት የግብይት መጠን እስከ ብር 15,000 ድረስ የአነስተኛ ብድር አገልግሎት፣

#ድልድይ ፡- ለነጋዴዎች/ወኪሎች አነስተኛ ንግድ/ቢዝነስ እንዲጀምሩ ወይም እንዲያስፋፉ እስከ ብር 50,000 የሚደርስ ብድር እንዲያገኙ የሚያስችል አገልግሎት እንዲሁም፤

#አድራሽ ፡- ወርሃዊ ደመወዛቸው በቴሌብር ለሚከፈላቸው የግል እና የመንግስት ተቋማት ሰራተኞች ለደሞዝ መዳረሻ እስከ 50,000 ብር ድረስ ብድር እንዲያገኙ የሚያስችሉ የብድር አማራጮች ናቸው፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia